
ክርስትና ወደ ኢትዮያ መቼ ገባ?
“የተላኩ” በተሰኘው ዐምድ፣ ገናዬ ዕሸቱ ከምታስነብባቸው ተከታታይ ጽሑፎች ሁለተኛው የሆነው ይህ ጽሑፍ፣ ወንጌል ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል ተብሎ የሚታመንባቸውን ዘመናትና የአገባብ ሒደቶች ቀረብ አድርጋ ታስቃኘናለች።
[the_ad_group id=”107″]
ገና ከጅምሩ የብዙዎችን ልብ ማሳረፍ የጀመረው የዶ/ር ዐቢይ “ሎሌ-መሪነት”፣ አገር ቤትና በየዓለም ማዕዘኑ በተበተነው ሕዝባችን ላይ አጥልቶ የነበረውን የክፍፍል ጽልመት በአፋጣኝ እየገፈፈ፣ ወደ አንጻራዊ አንድነትና ብሩኅ ወደ ሆነ ተስፋ እያመጣን ይገኛል። “በመደመር” ራእይ ውስጥ ፍትሕና ምሕረት ይዋሓዳሉ፤ ፍርድና ይቅርታ ይታረቃሉ። ይህ “የመደመር” ሂደት በንስሓ፣ ይቅርታና ምሕረት በሚገኝ መንጻት፣ ዘረኝነትን፣ አግላይነትን፣ ቂመኝነትና ሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መቀነስ፤ ምሕረትን ፍቅርን፣ ፍትሐዊነትን፣ መቀባበልንና የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልድ ማሳልፍን ማብዛት፤ ቸርነትን ማካፈልንና፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ ክቡረነቱና እኩልነቱ ተጠብቆ፣ በየትኛውም የአገሪቱ ግዛት የመኖርና የምድሪቱ በረከት ትሩፋት ተጠቃሚ ማደረግን ያካትታል። በዳይ ሙሉ ኀላፊትን ይወስዳል፤ ተበዳይ ይቅር ይላል። የሚያዋጣን፣ የተስፋ እንጂ የቂመኝነት ዑደት እስረኛ መሆን አይደለም! በዚህ አገራዊ የተሓድሶ አዲስ መንገድ ውስጥ፣ መፍረስ ስላለባቸው ግድዳዎች፣ በአንጻሩ ደግሞ የበለጠ መጠንከር ስላለባቸው ዐቢይ የዕርቅ ድልድዮች ትንሽ ልበል፦
2) በመንግሥትና ቤተ ክርስቲያን መካከል ባለው መስተጋብር ውስጥ፣ ቤተ ክርስቲያን “አያገባትም፣ ገለልተኛ መሆን አለባት” ከሚለው ጀምሮ፣ ማንነቷና መልእክቷ ፖለቲካዊ ልብስ እንዲለብስ ያደረጉ አመለካከቶች ይሰማሉ። እነዚህ ጠርዝ ላይ የቈሙ አመለካከቶች በብዙ መልኩ ስሑት እንደ ሆኑ እናውቃለን፡፡ በእኔ ትዝብታዊ ዕይታ ግን፣ በዶ/ር ዐቢይ የተጀመረው የገዢው ፓርቲ የራስ-ትችት፣ ይቅርታና ምሕረት የወለደው የ”መደመር” ፖለቲካ፣ እንደ ሰደድ እሳት ከመዛባቱ በፊት፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በፍትሕ ጥያቄ ላይ የመረጠችው በአብዛኛው ዝምታን ነበር። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያና የወንጌል አማኞች በመካከላቸውና እርስ በእርስም ያላቸው መከፋፈል፣ መንግሥትን “ሃይ” ለማለት የሚያስችል የሞራል ልዕልና ነፍጓቸው ቈይቷል። ይሁን እንጂ፣ ምሕረቱ የማያልቅ እግዚአብሔር ሁለተኛ ዕድል ሰጥቶናል። ወደ ኋላ በቁጭት ሳንመለከት፣ የጥላቻ ያለመተማመንና የአግላይነት ነቀዝ የበሉብንን ዓመታት በጋራ ንስሓና በግል ተሓድሶ ልናድሳቸው ይገባል። ከክርስቶስ በዐደራ የተቀበልነው የማስታረቅ አገልግሎት እኛን ከከፋፈለን፣ ሌሎችን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲሁም እርስ በእርስ ታረቁ ብለን የመመስከር ዐቅም ከየት ልናመጣ እንችላለን?
3) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የአገር ቤቱና ስደተኛው ሲኖዶሶች መካከል ዕርቅና ሰላም መወረዱ፣ የብሔርተኝነት መከፋፈል የፈጠረውን የአገሪቱን ቁስል ቶሎ እንዲሽር ይረዳል:: ይኸው የተፈጠረው አንድነትና ፈውስ በአገሪቱ ክፍሎች በሙሉ እንዲሁም በዲያስፖራው ቢዘልቅ፣ ኢትዮጵያን የበለጠ አንድ ያደርጋታል። ከዚህ በተጨማሪ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በቤተ ክህነትና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የተፈጠረው የአስተዳደርና የአስተምህሮ ልዩነት ቅዱሳት መጻሕፍትንና ኦርቶዶክሳዊ ትውፊትን ያገናዘበ ዕልባት ሊበጅለት ያስፈልጋል፡፡
4) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በወንጌላውያን አማኞች መካከል ያለውን ታሪካዊ የአግላይነት ውጥረት ይበልጡን የሚያከሩ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛንና ብስለት ያጡ አስተምህሮቶች እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የጐደላቸው ሥነ ምግባራዊ ቀውሶች መወገድ ይኖርባቸዋል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ፣ በእነዚሁ ሁለት ታላላቅ ቤተ እምነቶች ውስጥ ያለው የእርስ በእርስ መከፋፈል፣ ጐሣዊ፣ ብሔርተኛና ፖለቲካዊ ጽንፈኝነትን የተላበሰ መሆኑ፣ የአገሪቱን ፈርጀ ብዙ መከራ የበለጠ ሲያከብደው ኖሯል። በእኔ ግምት፣ በማኀበራዊ መገናኛ ብዙኀን፣ ከሁለቱም ወገን የሚሰሙ፣ ብስለት የጐዳለቸው የግለ ሰቦች ሥነ መለኮትዊ አመለካከቶች ሁለቱን ቤተ እምነቶች ሊወክሉ አይገባም። የጋራ ድንበር ላይ በመቆምና በተሻለ መቀባበልና መከባበር፣ ለአገራችን ፈውስ ዘለቄታ አብረን መሥራት ይኖርብናል። ቢያንስ 1600 ዓመት በዘለቀው ታሪኳ ውስጥ በብዙ መከራና ፈተኝ ሁኔታ ውስጥ ጸንታ የቆየቸው፣ ውድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በኢትዮጵያና ዓለም አቀፍ ታሪክ ውስጥ የከበረ ስፍራ አላት። የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን፣ ታሪኳ የቅርብ ጊዜ ቢሆንም በመከራ ውስጥ በአፋጣኝ ያደገችና ብዙ በጎ አስተጽኦ ያደረገች ናት።
5) ይህ ሃይማኖታዊ መቻቻል፣ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንንም ሊጨምር ይገባል። በክርስትናና እስልምና መካከል የማይታረቁ ሥነ መለኮታዊ ልዩነቶች እንደ ተጠበቁ ሆነው፣ በአገራችን ታሪክ ውስጥ ሁለቱ ቤተ ሃይማኖቶች አንጻራዊ በሆነ ሰላም መቻቻልና መቀባበል፣ ለዘመናት እንደኖሩ ልብ ልንል ይገባል። የጠቅላይ ሚኒስትራችን ቤተ ሰባዊ ዳራ እንኳ ለዚህ ተልቅ አብነት ነው። በጋራ ፋይዳዎች ለምሳሌ፣ የሰው ሁሉ የእኩልነትና የክቡርነት መሠርቱ በእግዚአብሔር አምሳያ መፈጠሩ፣ የሕይወት ክቡርነት፣ ፍትሕ፣ ሰላም እና ሥነ ምግባራዊ ፋይዳዎች ላይ አብሮ መሥራት ለአገሪቱ የሰላም ጐዳና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል። ይህ ሃይማኖታዊ ትብብር፣ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለተጀመረው የሰላምና የዕርቅ ግንኑኝት ከፍተኛ ጥንካሬ ይሰጣል። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የቆየው ይህ መተባባር፣ እንደገና በተሻለ መንገድ ሕይወት ሊዘራ ይገባዋል። በተለያዮ የዓለማችን ክፍሎች፣ የሚታዩ ዐመፃን የተለበሱ ሃይማኖታዊ ሽብሮች በምድራችን ላይ ዕድል ሊሰጣቸው አይገባም። አገር በቀልም ሆነ ከባዕድ ምድር የሚመጣ ተመሳሳይ እርሾ በጊዜ ሊደፋ ይገባል። ማንኛውም ዜጋ “እውነት ነው፤ ያዋጣኛል” የሚለውን የራሱን እምነት ያለ ፍርሀትና ያለ ምንም ተጽእኖ መከተል መቻል አለበት። ይህ መሠረታዊ የኀሊና ነጻነት አምላካዊ ነው። ሕገ መንግሥታዊና ሃይማኖታዊም ሊሆን ይገባዋል። ከምንጊዜውም በላይ ለዚህ በምንም መልኩ ሊሸረሸር ለማይገባው የኅሊና መብት እንደ አንድ ሕዝብ በጽናት መቆም ይኖርብናል።
6) እንደሚመስለኝ፣ ክርስቲያንና ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጋራ ልንፋለማቸው የሚገቡ ሁለት ጽንፍ የወጡ አክራሪ አመለካከቶች አሉ። አንደኛው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን፣ ሌሎች አገራት ያሉና ዐመፃን የለበሱ አክራሪ የእምነቱ ተከታዮች በሚታዩበት ዐይን መመልከት ነው። በታሪክ እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትናና እስልምና አንጻራዊ በሆነ ሰላም ተቻችለው ኖረዋል። ይህን አብሮነት በብርቱ መጠበቅ ይኖርብናል። ሁለተኛው አደጋ ጽንፈኝነት ዐመፅ የለበሰ አስተምህሮና ተግባር በኢትዮጵያ ሙስሊሞች መካከል የሚበቅልበት ለም ዐፈር ካገኘ ነው። ከእነዚህ ሁለት ጽንፋዊ አደጋዎች፣ አገራችንን ተገትን መጠበቅ ይኖርብናል።
7) አስተምህሮን በተመለከት በሁለቱ ቤተ ሃይማኖቶች መካከል የማይታረቁ ልዩነቶች እንዳሉ ልንቀበል ያስፈልጋል። ለምሳሌ፣ መጽሐፍ ቅዱስና ቁርዓን፣ ትምህርተ ሥላሴ፣ ነገረ ክርስቶሰ፣ ኀጢአት፣ እንዲሁም የሰው ልጅ ድነት ወይም በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኘው እንዴት ነው በሚሉት ጒዳዮች ላይ ዘላለማዊ ልዩነት አለን። እነዚህንና መሰል ልዩነቶቻችን፣ ብስለት፣ ወንድማዊነትና ቅንነት በሰፈነበት መልኩ፣ ልንወያይባቸው እንጂ የጥላቻና የአግላይነት ግድግዳ ልንመሠርትባቸው አይገባም። በዚህ ውይይት ውስጥ፣ ሁለት ፍልስፍናዊም ሆነ አስተምህሯዊ እውነት መሰል ተፋልሶዎች ማሰወገድ አለብን።
አንደኛው የክርስትናን መሠረታዊ አስተምህሮ የሚያደበዝዝ “ሃይማኖት ሁሉ ወደ አምላክ ያደርሳሉ” የሚለው አመለካከት ነው። ይህ አመለካከት በሃይማኖቶች መካከል ያለውን ልዩነት አንጻራዊ በማድረግ፣ ሁሉንም “የአንድ እውነት የተለያዩ ገጽታዎች” አድርጐ ይሟገታል። መቼም በሁለት ተጻራሪ መንገድ ላይ ያሉ “እውነቶች” ወደ አንድ መድረሻ አያደርሱም። ሁለቱም ሐሰት ሊሆኑ ይችላሉ፤ ሆኖም ሁለቱም በአንድ ጊዜ ትክክል ሊሆኑ አይችሉም። ስለዚህ ሁለቱን እምነቶች “የአንድ እውነት” ሁለት ገጽታዎች አድርጐ መመልከት ተኣማኒነት የጐደለው ድምዳሜ ነው። ሁለተኛውና በጣም አደገኛው በሁለቱም እምነቶች መካከል ያለውን ልዩነት በዐመፅ ኀይል አስወግዶ፣ ሰዎች በፈቃዳቸው ሳይሆን በግድ የአንዱ እምነት ተከታይ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። እንዲህ ዐይነቱ ተግባር እግዚአብሔር ለሰው የሰጠውን መሠረታዊ የኀሊና ነጻነት እንዲሁም ነጻ ፈቃድ ክፉኛ ይጻረራል። ይህ ለየትኛውም አገር በተለይም ለኢትዮጵያ አያዋጣም። አዋጩ መንገድ፣ ጥበብና ማስተዋል እንዲሁም ከማንኛውም ፍርሀትና ተጽእኖ ነጻ የሆነና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ሰላማዊና ሃይማኖታዊ ውይይት (intelligible dialogue) ነው። ደግሜ አበክሬ ላሳስብ፤ የኅሊናና የማሰብ ነጻነት፣ ሐሳብን የመግለጥና ያሹትን እምነት መከተል ወይም መለወጥ በምንም መልኩ ሊፋቅ የማይገባው (Inherent) ለሰዎች የተሰጠ አምላካዊ ነጻነት መሆኑ በድጋሚ ሊሠመረበት ይገባል። ይህን መሠረታዊ መብት ቤተ ሃይማኖቶችም፣ መንግሥትም ሊጠብቀው ይገባል።
8) በዐመፅ መፍትሔ አይመጣም፤ ምክንያቱም ዐመፅ፣ ዐመፅን ይወልዳል፤ ዑደቱም ከቂም፣ ድኽነት፣ መከራና ሥቃይ ያላረፈ ትውልድ ማትረፍ ይሆንብናል። የሚሻለው፣ ቤተ ሃይማኖችት፣ በውጠረቶች መካከል በጋራና በልበ ስፋት ጣልቃ እየገቡ ድልድይ መሆን ነው። ልክ እንደ ሙሴ “… እስራኤላውያን ሲጣሉ ደረሰ፤ ሊያስታርቃቸውም ፈልጐ፣ ‘ሰዎች፤ እናንተ እኮ ወንድማማቾች ናችሁ፤ እንዴት እርስ በርሳችሁ ትጐዳዳላችሁ?” ማለት መቻል አለባቸው (የሐዋ. 7፥26)—ክርስቶስም፣ “የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና” (ማቴ. 5፥9)፣ እንዳለው ማለቴ ነው።
9) የዶ/ር ዐቢይ ብሔራዊ ፓለቲካዊ ተሓድሶ ራእይ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በአሸባሪነት ተፈርጀው የነበሩ፣ በውጭ ያሉ ፓርቲዎች፣ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ብሔራዊ ውይይት ውስጥ፣ በሰላማዊ መንገድ አስተዋጽኦ ለማደረግ እንዲችሉ በር መክፈቱ ትልቅ ማስተዋል ነው። ይህ አዲስ በር፣ ለአገር ሁለንተናዊ ግንባታ፣ በተለይም በድኽነት ጨለማ ውስጥ ለዘመናት ለታሰረች አገራችን መፍትሔ የሚሆኑ የተሻለ የአስተዳደር፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የፖሊሲ ራእዮችን ለማቅረብ ዕድል ይሰጣል። በዚህ ለአገራችን የተሻለ በማሰብ በሚደረግ ፖለቲካዊ የውድድር ሜዳ ውስጥ፣ ግልጽነት፣ መተማመንና ቅንነትን መሠረት ያደረገ ወንድማዊ ውይይት ሊሰፍን ይገባዋል። ይህ ውይይት፣ ዘር መሠረት ያደረገው ፊዴራሊዝም ፖለቲካዊ አደረጃጃት የአዋጪነት ፍተሻ (critical examination)፣ የተአማኒነት ጥያቄ፣ የ27 ዓመት አገዛዝ፣ ብርታትና ጥፋትን ያካተተ ቅን ውይይት ሊሆን ይገባዋል። አሁን ሥር ነቀል የሆነ ፓለቲካዊ የራስ ተሓድሶ ማድረግ የጀመረውን የገዢ ፓርቲ ጨመሮ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሙሉ የውስጥ ግፊታቸው የተሻለች ኢትዮጵያን ከመገንባት ሕዝብን ከማገልገል አንጻር ብቻ ሊሆን ይገባዋል። “የተሻለ ፓለቲካዊ አመረራ ነው” እንዲሁም “ያዋጣኛል” የሚለውን ድርጀት የመምረጥ የመጨርሻ ሥልጣን የሕዝብ ሊሆን ይገባዋል። ስለዚህ ፉክክሩ፣ አገርን በተሻለ ለማገልግል እንጂ፣ ራስን ለማገልገል የሚደርግ አይረኬ የሥልጣን ጥማት ሊሆን እንደማይገባ በኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ የሰከነ ጉዳይ እንደ ሆነ ፓርቲዎች ሁሉ የተገነዘቡት ይመስለኛል። የእስከ አሁኑ የሥልጣና ርክክቦሽ፣ አድካሚና አክሳሪ የቁልቁሎሽ መንገድ መሆኑን ከታሪክ መማር አለብን!
10) ይህ የዲሞክራሲ ሂደት፣ ጥሩ በሆነው ላይ ቀጥሎ መገንባት እንጂ ማፈረስ እንዳልሆነ፣ ያላዋጣንን አካሄድ በመተው፣ እየተሻለች የምትሄድ ኢትዮጵያን በዐደራ ተርክቦ ማቆየትና በክብር ሕዝቡ በነጻ ዲሞክራዊ ያዋጣኛል ላለው አስተዳደር ማስረከብ ሊሆን ይገባል። በደም ከተነከረ ፓለቲካዊ ሽግግሮች ያጨድነው፣ ስብራትና ድኽነት፣ ልዩነትና ጥላቻን ብቻ ነው። ይህም የማያዋጣ፣ ዕድሜ አባካኝ መንገድ እንደ ሆነ በሰቆቃ ተምረናል። ስለዚህ፣ ኢትዮጵያ አሁን ላለውም ሆነ ለወደ ፊት ትውልድ የሚያስቡ ባለ ራእይ አገልጋይ መሪዎች ያስፈልጓታል። ለራሳቸው ግለኛ አጀንዳ የማይኖሩ፣ ለገዛ ወገኖቻቸው ጥቅምን ብቻ ሳይሆን ለመላው ሕዝብ፣ በተለይም ለድኾች መብትና ጥቅም፣ እንዲሁም ለሚልቀው አገራዊና ሁለንተናዊ ፈውስ የሚጋደሉ መሪዎች ያስፈልጓታል። እውነት፣ ጽድቅ፣ ፍትሕና ምሕረት የወንበራቸው መሠረት የሆነ አገር መሪዎች፣ ሕግ አውጭና አስከባሪዎች፣ ዳኞች፣ ኀይላትና ሥልጣናት፣ ወታደሮች፣ አሠሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ ባለ ሀብቶች፣ ነጋዴዎች ወዘተ. ያስፈልጓታል። ከእነርሱ የተሻሉ መሪዎች ማፍራት ረሃባቸውና ትጋታቸው የሆነ፤ በተሰጣቸው ዘመን ትውልዱንና እግዚአብሔርን ካገለገሉ በኋላ፣ የተሰጣቸውን ኀላፊነት በሕዝብ ለሚመረጡና ለዐደራ የሚበቁ መሪዎች በሰላምና በክብር ለማስረከብ፣ አፍቃሬ ሥልጣን ወይም ወገንተኝነት እንቅፋት የማይሆንባቸው ያስፈልጉናል።
11) በፍቅር፣ በምሕረትና ይቅር ባይነት ላይ የተመሠረት አንድነት እንጂ የዐመፅ ፖለቲካ እንደማያዋጣ፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። በአሁኑ ወቅት፣ የብሔርተኝነት ካባ ደርበውና ለብሔራቸው አሳቢ በመምሰል፣ በተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛዎች መርዘኛ ቀስቶች የሚወነጭፉ ጥቂት ዘረኛ ፖለቲካዊ ድርጅቶች ወይም ጥቅማቸው የተነካ፣ በግፍና ሙስና የበለጸጉ ራስ ወዳድ ባለሀብቶች አሉ። ዐላማቸው፣ በሕዝባችን መካከል ያለመተማንና ጥላቻን በመፍጠር የግል ፍላጎታቸውን ማሳካት ብቻ ነው! እነርሱ በሚታዩበት ዐይን፣ ብሔራቸውን ልንፈርጅና በጭፍን ጥላቻ ልንመለከት አይገባም። እነዚህ ጥቂት የጥፋት መልእክተኞች፣ የትኛውንም ብሔር አይወክሉም፤ እንዲወክሉም ዕድል ሊሰጣቸው አይገባም። ይህ ትንሽ ብዥታ ቀን ሳለና ሳይረፍድ “በመደመር” እውነተኛ የጸጸት መመለስ፣ አልያም ሲመሽ በፍትሕ የመቀነሰ ሂደት ይጠራል። እንደ ሕዝበ ክርስቲያን ተስፋ የምናደርገው ፍቅሩ ልዩ የሆነውን፣ መልካሙን እረኛ፣ የፍትሕና የምሕረት አምላክ ልዑል እግዚአብሔርን ነው። በቀኑ መጨረሻና የማታ ማታ ለአገራችን እውነተኛ ሰላምና ብልጽግና የሚመጣው ከራሱ ከእግዚአብሔር ነው። ከውስጥና ከውጭ የተነሡ ተግዳሮቶችን በጽናት የተቋቋመ ታሪክ እንዳለው ሕዝብ፣ በጸሎትና በአንድነት እንቁም። ከራሳችን ይልቅ፣ ለመጪው ትውልድ የተሻለች አገር እናስረክብ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤ ይጠብቅም!
Share this article:
“የተላኩ” በተሰኘው ዐምድ፣ ገናዬ ዕሸቱ ከምታስነብባቸው ተከታታይ ጽሑፎች ሁለተኛው የሆነው ይህ ጽሑፍ፣ ወንጌል ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል ተብሎ የሚታመንባቸውን ዘመናትና የአገባብ ሒደቶች ቀረብ አድርጋ ታስቃኘናለች።
“ስንቶች ለስምህ ቆመው ዘምረዋል
ስንቶች በስምህ ስብከትን ሰብከዋል
አሁን ብትመለስ ጌታ ወደ ቤትህ
ከሕይወት ጎድለዋል ጠፍተዋል ልጆችህ”
እውቁ የሥነ አእምሮ ሐኪምና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አታላይ ዓለም አሳሳቢነቱ ጨምሯል ስለሚባለው የአእምሮ ሕመም ከሕንጸት መጽሔት ጋር ቆይታ አድርገዋል። በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን አባል የሆኑት ፕሮፌሰር አታላይ፣ ችግሩን በተመለከተ በወንጌላውያን አማኞች መካከል ስላለው የአመለካከት ክፍተትና ሊደረጉ ስለሚገባቸው ርምጃዎች ሚክያስ በላይ እንደሚከተለው አነጋግሯቸዋል።
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.
Add comment