[the_ad_group id=”107″]


ኢየሱስ ክርስቶስን ማየትና መጠማት


በዮሐንስ ፓይፐር (መጋቢ) ተጽፎ፣ በፈረንጅ ዓመት (ፈ.ዓ.) 2004 ተሻሽሎ የታተመውና ከላይ በርእሱ ከተገለጸው መጽሐፍ መግቢያ1፣ ለአንባቢያን በጥቂቱ ለማካፈል ፈለግሁ። እንዲህ ይላል፦

ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነበር? መልስ ለመስጠት ሙከራ የማደርገው ይህንን ጥያቄ ይሆናል። ነገር ግን ዐላማዬ እርስዎ ስለ እርሱ ገለልተኛ አቋም እንዲኖርዎት ማድረግ ኣይደለም፤ ይህንን ማድረግ ጭካኔ ነውና! ኢየሱስ ክርስቶስን ማየትና መጠማት፣ ወደ ፊት በሕይወትዎ ከሚያጋጥምዎ ማየትና መጠማት ሁሉ በጣም ከፍተኛው ነው። ዘላለማዊነት በዚህ ላይ ተንጠልጥሏል። ስለዚህ፣ የእኔ ዐላማ እርስዎ በጸና እውነተኛነት እንዲያዩትና በከፍተኛ ሐሴት እንዲጠሙት ማድረግ ነው።


ኢየሱስ ክርስቶስን ስለ “ማየት” ስናገር፣ በልቦናዎ ዓይናችን እንጂ፣ ጭንቅላትዎ ላይ በተቀመጡት ዓይኖችዎ ማየትን አይደለም። ኢየሱስ፣ ዓለምን ትቶ ወደ አብ ሊመለስ ሲል፣ “… የሰው ልጅም … በሰማይም ደመና [እስኪ መጣ] ሲመጣ” ድረስ “አታዩኝም” ብሏል (ማርቆስ 14፥62፤ ዮሐንስ 16፥17)። በዚያን ወቅት፣ ሰዎች በተፈጥሮ ዓይናቸው ሊያዩት ይችሉ ነበር። ዛሬ ግን፣ መጽሐፍ ቅዱስ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና ይላል (2ኛ ቆሮንቶስ 5፥7)። ድጋሚ መጥቶ ለሁሉም እስከሚታይበት ጊዜ ድረስ አሁን በሰማይ ነው።


ይህም ሆኖ ግን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስን በሌላ ሁኔታ ልናየው እንደምንችልም ይናገራል፤ “የልባችሁ ዓይኖች” (ኤፌሶን 1፥18) በማለት። “የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፣ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ” (2ኛ ቆሮንቶስ 4፥4) ብሎም ይናገራል። ኢየሱስ ራሱ ስለ ሁለት ማየቶች ተናግሯል፤ ሊረዱት ላልቻሉት ሕዝብ፣ “እያዩ ስለማያዩ” (ማቴዎስ 13፥13) ብሏቸዋል። አንዱ ማየት በተፈጥሯዊ ዓይን ማየት ሲሆን፣ ሌላኛው ማየት ደግሞ በመንፈሳዊ ዓይን ማየት ነው። በመንፈሳዊ ዓይናችን ስናይ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን እውነትና ውበት እንዲሁም የበዛ ዋጋ እውነተኛውን ምንነት በርግጠኛነት እናያለን። እንግዲህ፣ ዛሬ ዓይነ ስውር የሆነ ሰው፣ ዓይናማ ከሆኑ ብዙዎች በተሻለ ሁኔታ ተገልጦለት ኢየሱስ ክርስቶስን ሊያይ ይችላል።


ማንም ሰው የኢየሱስን ታሪክ ማንበብ፣ እንዲሁም እርሱን የሚያውቁት ከጻፏቸው ቃላት የእርሱን ምስል “ማየት” ይችላል። ሆኖም፣ ሁሉም ሰው እውነትና ውበትን እንዲሁም ወሰን የለሽ ዋጋን አያይም። አንዳንዶች የሚያዩት ተረትን ነው፤ አንዳንዶች ስንፍናን ያያሉ፤ አንዳንዶች ጥቃትን ያያሉ። “እያዩ ስለማያዩ”። ልክ እንድ ሕፃን የሚካኤል አንጀሎን የጥበብ ሥራ ካየ በኋላ፣ የቀልድ ብጣሽ ወረቀት ላይ የሰፈረን ቀልድ ሲመርጥ እንደ ማለት ነው።


ኢየሱስ ክርስቶስን መጠማት፣ ለሁለተኛው ዓይነት ዕይታ የሚሰጥ ምላሽ ነው። አንድን ነገር እንደ እውነተኛና ውብ፣ እንዲሁም ዋጋ ውድ እንደ ሆነ አድርገው ካዩት፣ ነገሩን ይጠሙታል። ማለትም፣ እንደ ትልቅ ሀብት ይቆጥሩታል፤ ይንከባከቡታል፣ ያደንቁታልም፤ እንዲሁም ከሁሉ አብልጠው ይወድዱታል። መንፈሳዊ ዕይታና መንፈሳዊ ጥማት በጣም ከመጣመራቸው የተነሣ፣ ክርስቶስን ካልተጠሙት ክርስቶስ ማን እንደ ሆነ አላዩትም ብለን ብንደመድም ስሕተት አይሆንም። ከሁሉ ነገሮች አብልጠው ካልወደዱት፣ እውነተኛውን የእሱን ዋጋ አልጨበጡትም።

መጋቢ ዮሐንስ ፓይፐር፣ የመጽሐፋቸው ዐላማ ሰዎች ክርስቶስን እንዲያዩና እንዲጠሙ ለመርዳት እንደ ሆነ ከገለጹ በኋላ በመቀጠል፣ “ይህም ሊሆን የሚችለው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እዚህ በነበረበት ጊዜ ያውቁት ከነበሩት የተሰጡትን ምስክርነቶች ተፈጥሯዊ በሆኑት ዓይኖችና ጆሮዎች በማየት ወይም በመስማት ብቻ ነው” ይላሉ። “በዚህ መጽሐፍ ምእራፎች ውስጥ የመጽሐፍ ጥቅሶች የተሰገሰገባቸው በዚህ ምክንያት” እንደ ሆነ አስታውቀው፣ “ሥራውን የሚሠራው የእግዚአብሔር ቃል እንጂ፣ የእኔ አይደለም። እርሱ ለልጁ ምስክርነትን ሰጥቷል፤ ምስክርነቱም የማይቋቋሙት ነው” በማለት፣ “የሚያይ ዓይንን እና የሚጠማ ልቦናን እርሱ ይስጣችሁ!” በሚሉ የበረከት ቃላት የመጽሐፋቸውን መግቢያ ይደመድሙታል።


1. John Piper, “Seeing and Savoring Jesus Christ”, Desiring God Foundation (2004).

Share this article:

አለንጋ እና ልጓም

“በአግባቡ የተገራ ፈረስ ለባለቤቱ ክብር ያመጣል። ወደ ጦር ሜዳ ቢያደርስም፣ ዋንጫ ቢያሸንፍም፣ ታርሶበት ቢያመርትም፣ ግልቢያ ቢያሳምርም ትርፉና ክብሩ ለባለቤቱ ነው! . . . ሰው እንደ ፈረስ ነው። ያለ አለንጋና ያለ ልጓም አይኖርም። ልከኛው ባለአለንጋ ግን እግዚአብሔር ነው። ሲሻውም ልጓም ይሆናል።” ጳውሎስ ፈቃዱ።

ተጨማሪ ያንብቡ

ዛሬ ያልተመቸን ሕዝቦች

ኢትዮጵያውያን በቀድሞው ዘመን ናፋቂነት የዛሬውን ዕድል እያባከንን እንደ ሆነ፣ ተካልኝ ነጋ (ፒ.ኤች.ዲ) በዚህ መጣጥፉ ይሞግታል። በተለይም በትላንት ናፍቆት ውስጥ ስለ “ጀግኖቻችን” ያለን ምልከታ፣ የዛሬውን አብሮ ነዋሪ ወንድማችንን እንዳይጎዳውም ያሳስበናል።

ተጨማሪ ያንብቡ

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.