[the_ad_group id=”107″]

የካታኮምብ ዋሻዎች

በሮም ከተማ በተለምዶ “ካታኮምብ” የሚባሉ የመሬት ሥር፣ የውስጥ ለውስጥ ዋሻዎች ነበሩ። የጥንት ሮማዊያን እንደ እነዚህ ያሉ ቦታዎችን የሠሯቸው ሞትን ከመጥላትና ከመፍራት የተነሣ፣ ስለ ሞት ላለማሰብ በሚል ነበር። የሞት ሐሳብን ለመሸሸ በማሰብ የሞቱ ዘመዶቻቸውን ከምድር በታች ባሉ፣ በዐይን በማያዩዋቸው “ካታኮምብ” በሚባሉ ስፋራ ውስጥ ይቀብሯቸው ነበር። 

እነዚህ ቦታዎች ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ጠንካራ ቦታ አላቸው። ጌታ ወደ ሰማይ ካረገ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ክርስትና ከሮም መንግሥት ጠንካራ መከራ ይደርስበት ነበር ይታወቃል። በመሆኑም፣ ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት ይገፉ፣ ይገለሉ እንዲሁም መከራን ይቀበሉ ነበር። በመንግሥትም ሆነ በማኅበረ ሰቡ ከሚደርስባቸው ግፊት በተወሰነ መልኩ በነጻነት የማምላክ ዕድል የነበራቸው ቦታ ቢኖር ካታኮምብ ነበር። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ አሳዳጆቻቸው ወደ ካታኮምብ ወርደው ሊያሳድዷቸው ስለማይሞክሩ ነው። የታሪክ ምሁራን እንደሚያስረዱት ሮማውያን ወዳጆቻቸውን ሲቀብሩ እንኳን ባሪያዎቻቸውን ወደ ካታኮምብ በመላክ ጕድጓድ አስቆፍረው ያስቀብሩ ነበር። እነዚህን ስፍራዎች ግን ክርስቲያኖች በአንጻራዊ ነጻነት የማምለኪያ ስፍራ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር። 

በካታኮምብ ዋሻ ግድግዳዎች ላይ የተለያዩ ክርስትናን የሚገልጡ መልእክቶች ይጻፉ ነበር። የተሣሉት ብዙዎቹ ሥዕሎች በወንጌል የተጠቀሱ ድርጊቶችን የሚያሳዩ ሲሆኑ፣ አንዳንዶቹ የጌታ ራትን፣ 5000 ሰዎችን መመገብ፣ የጌታ ምሳሌዎች፣ ጌታ ማዕበሉን ጸጥ ሲያደርግ ወዘተ. የሚያሳዩ ይገኙበታል። አብዛኞቹ ሥዕሎች ላይ የግሪክ መጀመሪያና መጨረሻ የሆኑትን “A” እና “W”፣ ጌታ የሁሉ ነገር ጀማሪና ፈጻሚ መሆኑን ለመግለጥ ተቀምጠዋል።

በካታካምቡ ውስጥ አምልኮ ይደረግ ስለ መሆኑ ከሚያመለክቱ ማስረጃዎች አንዱ፣ ድንቅ የሆነው “ጥንታዊ ብርሃን” ወይም “ድንቁ ብርሃን” የሚለው መዝሙር አንዱ ነው። የዚህ መዝሙር ሐሳብ መልእክት የሚከተለውን ይመስላል፦

ኦ ድንቅ ብርሃን፣ ኦ ልዩ ጸጋ
የአባታችን የእግዚአብሔር ፊት
ዘላለማዊ ብርሃን
ቅዱስ ብሩህ
አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በመገኘቱ ደስታ ሰጪ

እነዚህ ክርስቲያኖች ይህንና ሌሎች መዝሙሮችን ሲዘምሩ ያሉበት ቦታ ጨለማ ስለ ሆነ የእሳት ብርሃን ማብራት ነበረባቸው። በብርሃኑ ዙሪያ በመሰብሰብም መዝሙር በመዘመር ጌታን  በደስታ ያመልኩ ነበር። 

ጊዜ ተለውጦ ክርስቲያኖች ላይ የሚደረገው ሙከራ ሲቈምና ነገሥታት ጭምር ክርስትናን መከተል ሲጀምሩ፣ ካታኮምብ በጊዜ ብዛት ክርስቲያኖችም የሚቀበሩበት ቦታ ሆኗል። በዚያ ቦታ የሚቀበሩ ክርስቲያኖች በተቀበሩበት ቦታ ላይ ይጻፉ የነበሩ መልእክቶች፣ አሁን ላለን አማኞች ትምህርት የሚያስተላፉ ናቸው። አንዱን እንጥቀስ፣ ምሳሌ እንዲሆን፦

“ኩዊንትሊያ እዚህ ዐርፏል። በምድር ሳለ የእግዚአብሔር ሰው፣ በሥላሴ ላይ ጠንካራ እምነት የነበረው፣ ቅድስናን የሚወድድና ዓለማዊ ምኞትን የጠላ ሰው ነበር።”

ቃለ መጠይቅ ከአገኘሁ ይደግ ጋር

አገኘሁ ይደግ በኢትዮጵያ የወንጌላውያን አማኞች የዝማሬ አገልግሎት ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚነሡ ዘማሪያን መካከል የሚጠቀስ ነው። ዘመን ዘለቅ በሆኑት ዝማሬዎቹም ብዙዎች ተጽናንተዋል፣ ታንጸዋልም። የሕይወትን አስቸጋሪ ፈተናዎች በመቋቋም እግዚአብሔርን በጽናት ማገልገሉ ለአርኣያነት የሚያበቃው እንደ ሆነ የሚያውቁት ይናገራሉ። የዚህን ዘማሪ 25ኛ የአገልግሎትና 20ኛ የትዳር ዘመን በዓል ምክንያት በማድረግ ሕንጸት የቆይታ ዐምድ እንግዳ አድርጎታል። ጳውሎስ ፈቃዱ ከዘማሪ አገኘሁ ይደግ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ተጨማሪ ያንብቡ

ለማነጽ እንሠራለን!

ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር፣ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ስለ ወንጌሉ እውነት እንዲሁም እርሱ ስለ መሠረታት ቤተ ክርስቲያን ግድ የሚላቸው ሰዎች ተሰባስበው ያቋቋሙት መንፈሳዊ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ በምድራችን ላይ ያለችው ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን፣ ክርስቶስን መስላ እንድታድግ በሚደረገው የማነጽ ሂደት ውስጥ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ያለመ ነው፡፡ ስያሜውም ይህንኑ የሚገልጽ ነው፤ “ሕንጸት” የግዕዝ ቃል ሲሆን፣ “ማነጽ” ወይም “መገንባት” የሚለውን ፍቺ ይይዛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

Add comment

Your email address will not be published.

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.