
[the_ad_group id=”107″]
ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድህን እንዳታቋርጥ። ብቻ የዘራፊዎች፣ ወይ የአስመሳዮች፣ አልያም የሐሰተኞች፣ ወይም ለዓለም እና ለሥጋ የተሸጠ ስብስብ አይሁን እንጂ፣ በስሙ ወደ ተሰበሰቡ የአማኞች ኅብረት ጕባዔ መሄድህን የዘወትር ተግባርህ አድርገው።
በምትሄድበት ጕባዔ አገልግሎቱ ባይጥምህ፣ ትምህርቱ እና የሚገለጠው ጸጋ አንተ ከምትጠብቀው ደረጃ እና ይዘት ቢያንስብህ፣ ወይም የሆነ ነገሩ ባይመችህ፣ በትዕግስት እና በተስፋ መሄድህን ቀጥል እንጂ፣ በፍጹም እንዳታቈም። ከሆነልህ ሌላ በስሙ የሚሰበሰብ፣ ንጹሑን ቃል እና ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ የምትካፈልበትን ኅብረት ፈልገህ ከዚያ ሂድ። ጕባዔ መሄድ መፈለግህን ግን እንዳትተው ተጠንቀቅ። ከቤትህ እንዳትቀመጥ። ወደ እግዚአብሔር ጕባዔ ሂድ። ወደ እግዚአብሔር ቤት ሂድ።
ዘወትር ሳትታክት መሄድ፣ የምትጠብቀውን ለማግኘትህ ምስክር ላይሆን ይችላል፤ በአንጻሩ፣ የሚበልጠውን ስለ መፈለግህ እና ስለ መናፈቅህ ምኞትህን ያመለክታል። ይህም በሰማይ ዋጋ አለው።
ዘወትር ሳትታክት መሄድ፣ የምትጠብቀውን ለማግኘትህ ምስክር ላይሆን ይችላል፤ በአንጻሩ፣ የሚበልጠውን ስለ መፈለግህ እና ስለ መናፈቅህ ምኞትህን ያመለክታል። ይህም በሰማይ ዋጋ አለው። በስሙ መሰባሰብ የእምነታችን ምስክርነት መሆኑን ማስታወስ ጠቃሚ ነው። በጕባዔ ስንገኝ ስለ ኢየሱስ ለሆነው ዕውቅና የመስጠታችን ተግባር ነው፤ የአማኙ አንዱ መለያውም ይህ ነው። በክርስትና እምነት ታሪክ እንዳየነው፣ ተቃዋሚዎች ሆኑ እንዲሁ ጠያቂዎች፣ “…በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ?” (የሐሥ 4፥7) ያሉበት ጊዜ ነበር፤ ወደ ፊትም ይኖራል። የምንሰበሰበው በኢየሱስ ስም ነው!
ርግጥ ነው፤ በክርስትና ስም የተሰበሰበ ጕባዔ ሁሉ ለኢየሱስ መንፈስ መገኘት ቅድሚያ የሰጠ ወይም ለተስፋ ቃሉ ተገቢውን ዋጋ የቸረ እንዳልሆነ አይካድም። ለስሙ የቀኑ፣ መገኘቱን የሚናፍቁ፣ ጸጋው እንደሆነላቸው የሚጠባበቁ ጕባዔዎች አሉ። ሌሎች ደግሞ ለስሙ እና ለመንፈሱ የደነዘዙ፣ ያንቀላፉ፣ ከነጭራሹም የኢየሱስን ዋናነት የገፉ “የክርስቲያን” ጕባዔዎች አሉ። እንዲሁም አሳቾች፣ ለገንዘብ እና ለዓለም አጥማጆች፣ በእውነት “የክርስቶስ ጠላቶች” የሆኑ የክርስቲያን ስም ያላቸው ማኅበራት አሉ። ከዚህ አንጻር የምትሄድበትን ጕባዔ ይዘት እና ተቀዳሚ ትኵረት መጠየቅ እና መፈተሽ የአንተ ኀላፊነት ነው። ዋናቸው ኢየሱስ ካልሆነ ከዚያ ጕባዔ ዘወር ማለትህ ተገቢ ይመስልኛል። ሌላ ጕባዔ ፈልገህ መሄድህን ግን ቀጥል።
በኢየሱስ ስም በተሰየም ጕባዔ መካከል መገኘት መንፈሳዊ በረከት እንዳለው ተጽፎልናል። ኢየሱስ ራሱ ለተከታዮቹ ተስፋን ሰጥቷል፦ “ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።” (ማቴ 18፥20)። ደግሞም፣ “…የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ።” በመሆኑም፣ “. . . መሰብሰባችንን አንተው” (ዕብ 10፥23፡ 25) ተብለናል።
የዕብራውያን ጸሐፊ የቀደሙትን የእምነት አባቶች፣ “አምነው ሞቱ”፤ “አላገኙምና”፤ “የሚበልጠውን ይናፍቃሉ” ይላቸዋል። የዘወትር አሰልቺ ተግባራቸውን፣ የመሠዊያ ዕንጨት ድርደራ፣ የኰርማና የበግ ዕርድ ሥርዐቱንና ልማዳቸውን አላቈሙም ነበርና። ስለዚህም፣ “እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም” ይልላቸዋል፤ “ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና”።
“እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ። እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና። ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፥ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር፤ አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና።” (ዕብራውያን 11፥13-16)
Share this article:
ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር፣ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ስለ ወንጌሉ እውነት እንዲሁም እርሱ ስለ መሠረታት ቤተ ክርስቲያን ግድ የሚላቸው ሰዎች ተሰባስበው ያቋቋሙት መንፈሳዊ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ በምድራችን ላይ ያለችው ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን፣ ክርስቶስን መስላ እንድታድግ በሚደረገው የማነጽ ሂደት ውስጥ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ያለመ ነው፡፡ ስያሜውም ይህንኑ የሚገልጽ ነው፤ “ሕንጸት” የግዕዝ ቃል ሲሆን፣ “ማነጽ” ወይም “መገንባት” የሚለውን ፍቺ ይይዛል፡፡
“የእግዚአብሔር ሕዝብ” በሚል መሪ ዐሳብ፣ ዘሪቱ ከበደ የምታስነብበው ጽሑፍ ሁለተኛ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል።
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.
Add comment