[the_ad_group id=”107″]

በሚድን በሽታ ተይዛ በሽታው እየገደላት ያለች አገር፦ ኢትዮጵያ

(ደወል 1 ዘኢትዮጵያ)

© Amanuel Sileshi, Agence France-Presse

ይቅርታ፣ እርቅ፣ ምክክር፣ መግባባት የማንለው የለም። ግን በተግባር የሚደረግ ነገር ደግሞ የለም። ለምን? አንድ ነገር ለማድረግ ቀርቶ፣ ለመነጋገርም የማይቻልበት ደረጃ ላይ ነን። ማስረጃ ቢባል በሦስት ረድፍ ላስረዳ። አንደኛ፤ ንግግር መጀመር አይቻልም። ሁለተኛ፤ ንግግር ቢጀመር እንኳን መቀጠል አይቻልም። ሦስተኛ፤ ንግግር መቀጠል እንኳን ቢቻል፣ መጨረስ አይቻልም። በዚህ ዐይነት የመፍትሔ ዐሳብ እንዳይወለድ (እንዳይሰማ) በሦስት ደረጃዎች መላን የሚያጨነግፉ ብዙ ጩኸቶች አሉ።  

1. ንግግር እንዳይጀመር ፈንጂ ተጠመደ

ዛሬ ላይ የፈውስ ዐሳብን ማንሣት እጅግ የሚያስቸግርበት ሁኔታ እየሆነ ነው። የተናጋሪው ስም እንደ ታፔላ (ፈንጂ) ይሆናል። የሰው አስተሳሰቡ በራሱ እንዳይመዘን በማድረግ፣ የተናጋሪውን አስተሳሰብ እንዲመክን ይደረጋል። 

የተቀበረ ፈንጂ ስለማይታይ ሰላም ነው ብሎ በመሬት ላይ የሚራመድ ሰው ሁሉ ላይ አደጋ ያደርስበታል።  ዛሬ ላይ የፈውስ ዐሳብን ማንሣት እጅግ የሚያስቸግርበት ሁኔታ እየሆነ ነው። የተናጋሪው ስም እንደ ታፔላ (ፈንጂ) ይሆናል። የሰው አስተሳሰቡ በራሱ እንዳይመዘን በማድረግ፣ የተናጋሪውን አስተሳሰብ እንዲመክን ይደረጋል። አንዱ የሚናገረው ነገር ጆሮ ለመክፈት እንዳይችል ፈንጅ እንቅፋት ነው። ገና ከመነሻው ሥር እንዳይዝ የዐሳብ ፍሰት ማጥለያ (filter) ይደነቀርበታል።  ደግሞ የተወሰኑ ኮድ ቃላት እንደ ፈንጂ ያገለግላሉ። በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ተናጋሪው ዐሳቡን ሊያብራራ ይቅርና፣ የዐሳቡን ርእስ እንኳን ለመግለጽ እንዳይችል ያደርጋሉ። አንዳንዶቻችን፣ ‘ከነገሩ ጦም ዕደሩ’ ብለን በግል ሕይወታችን ላይ ብቻ እንድናተኵር ተገድደናል።  

2. ንግግር እንዳይቀጥል ቋንቋ ተደበላለቀ

በባቢሎን ከተማ ሰዎች ሰማይ የሚደርስ ሐውልት ሊሰሩ ተነሡ። ፈጣሪ ከዐላማው ጋር የሚሄድ ራእይ ስላልሆነ ቋንቋቸውን ደባለቀ። አንድ ልብ ሆነው እንዳይሠሩ፣ ቋንቋ ተደበላልቆ መግባባት እንዳይችሉ አደረጋቸው። ከዚያ ሁሉን ትተው በዓለም ዙሪያ ተበተኑ። ይህ ታሪክ በእኛ ተደገመ፤ በፈጣሪ ሳይሆን በክፉው።

ኢትዮጵያን ለማዳን ላይ ታች በማለት በተስፋ ብንጠመድም፣ ትርፍ ሳይሆን ከዕለት ዕለት ኪሳራ ሆነብን።

ኢትዮጵያ በዐብሮነት እንድንትገነባ በጎ ፍቃደኝነት እና ቅን ልቦና በኢትዮጵያ ልጆች ላይ አለ። ሁሉም የአገሩ ነገር እንቅልፍ አሳጥቶት የሚታትርና የሚጥር እንደ ሆነ ይታወቃል። ግን ሁሉም የሚያውቀው ብዙ ዘርቶ ትንሽ ማጨዱን፣ ብዙ እየለፋ የሚታፈስ ማጣቱን ነው። ኢትዮጵያን ለማዳን ላይ ታች በማለት በተስፋ ብንጠመድም፣ ትርፍ ሳይሆን ከዕለት ዕለት ኪሳራ ሆነብን። በዚህ ውስጥ አንዱ ንግግር መጀመር ከቻለ፣ የሚቀጥለው ፈተናው ደግሞ ንግግሩን መቀጠል ነው።  ምክንያቱም ቋንቋ ስለተደበላለቀ ንግግሩን ያቈመዋል። አማርኛ እየተናገርን የምንለው ግን የተለያየ ሲሆን፣ ቋንቋችን ይደበላለቃል። አፋን ኦሮሞ እየተናገርን የምንለው ግን የተለያየ ሲሆን፣ ቋንቋችን ይደበላለቃል። ሌላውም እንደዚሁ። ቃላት ትርጕማቸውን ከደበላለቁብን እንደ ባቢሎን ዘመን አልሆንምን?

3. ንግግር እንዳይጨረስ በሰበር ዜና ፋታ ጠፋ

ሁልጊዜ እሳት ላይ እንደተጣድን ነው። እፎይታ የለም፤ ለማሰብ ፋታ የለም። ሰብር ዜና እኛን የሚሰባብር ዜና ቢባል ጥሩ ነበር።

የቍም ነገር ንግግርና ሚዛን የሚደፋ ዐሳብ የሚሰማ ጆሮ ብቻ ሳይሆን የሚያስተውል አእምሮ ይፈልጋል።  ለማስተዋል ሰከን ብሎ ማዳመጥና አውጥቶ አውርዶ ውሳኔ ለመወሰን ጊዜ መውሰድን ይጠይቃል። ታዲይ ሰብር ዜና ለዚህ ፋታ አይሰጥም። ከአንዱ ሰበር ዜና ወደ ሌላኛው እየተቀባበለ ለማሰብ ፋታ እንዳይኖረን ያደርጋል። እንደ ጉም በየጊዜው እየተነነ በማይጨበጥ ነገር እያደናገረን ጊዜያችንን ብቻ ሳይሆን፣ እኛን ራሳችንን እየመዘመዘ ይበላናል። ሁልጊዜ እሳት ላይ እንደተጣድን ነው። እፎይታ የለም፤ ለማሰብ ፋታ የለም። ሰብር ዜና እኛን የሚሰባብር ዜና ቢባል ጥሩ ነበር።

የነገሩ ፍጻሜ ምንድን ነው?

የሁሉንም ጆሮ ቀልብ ይዞ አንድን ዐሳብ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ማድረስ ካልተቻለ፣ እየተነጋገርን አይደለም ማለት ነው። እስካልተነጋገርን ድረስ ደግሞ መግባባት ፈጽሞ አንችልም። ካልተግባባን ደግሞ የሚድን በሽታችንን ማከም ስለማንችል፣ በሽታችን የምንኖር እስኪመስለን እያታለለን ወደ ሞት ይወስደናል። ታዲያ ምን ይሻላል? በተከታታይ እንመለከታለን፤ በደወል 2 ዘኢትዮጵያ እንገናኝ። 

Zelalem Eshete (Dr.)

ዶ/ር ዘላለም እሸቴ በጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርሲቲ በምህንድስና መምህርነት እያገለገሉ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ ላይ መግባባትና እርቅ እንዲኖር አንዳንድ መጣጥፍ በመጻፍ ይሳተፋሉ። ጸሐፊውን በቀጥታ ለማግኘት፦ www.myEthiopia.com

Share this article:

ከአዲስ ወደ ብሉይ?

የብልፅግና ወንጌል ሰባኪያንና ተከታዮቻቸው ብሉይ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፤ ትምህርታቸውንም በአዲሱ ኪዳን ላይ ለመመሥረት በፍጹም ይቸገራሉ፤ በመሆኑም ተከታዮቻቸውን ከአዲሱና ከበለጠው፣ ወደ ቀድሞውና ደካማው ብሉይ እየጎተቱ ናቸው ሲል አፈወርቅ ኀይሉ (ዶ/ር) ይሞግታል።

ተጨማሪ ያንብቡ

የመተማመን ድልድዩን እንጠግን

ይቅርታ መጠየቅ ምን ማለት ነው? ሰዎች ይቅርታ ለመጠየቅ ለምን ይቸገራሉ? የተሠራው በደል በተበዳዩ ላይ ካሳድረው ጉዳት አንጻር፣ የበዳዩ ይቅርታ ጥየቃ የሚያጎናጸፈው ሥነ ልቦናዊ ፋይዳ ምንድን ነው?

ተጨማሪ ያንብቡ

ማንነት እና ስንክሳሩ

“አብሮነት ራሱን የቻለ ድብለቅ ነው፤ ራስ በራስ ሳይሆን እርስ በርስ። ስለዚህ የስሜት ብስለት ይጠይቃል፤ ግለ ሰቦች በስሜት በሳል ሲሆኑ የራስም ሆነ ከሌላው ጋር የሚኖራቸው ትምምን ከፍ ይላል” ሰሎሞን ጥላሁን በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ካሰፈረው

ተጨማሪ ያንብቡ

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.