[the_ad_group id=”107″]

እግዚአብሔር ‘ቦንኾፈር’ን እንዲያስነሣ እንጸልይን?

ከዚህ በታች ያለው “ለውጥ መጣ፤ ከመሪዎቹም ወንጌላውያን በዝተው ይገኙበታል” መባልን በሰማሁ ጊዜ ያካፈልኩት ነበር። የተወሰደው “What is the Relationship between Church and State?” ከሚለው ከነገረ መለኮት አስተማሪው ከR.C Sproul ጽሑፍ ነው።[1]

የመንግሥትና የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለእየቅል ለሆነ ተግባር ተሾመዋል። የመንግሥት መሪዎች አገርን ሊያገለግሉ፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን ሊያገለግሉ በእግዚአብሔር ተሰይመዋል። የመንግሥት መሪ የቤተ ክርስቲያን መሪውን ሥራ አይሠራም። የቤተ ክርስቲያን መሪውም የመንግሥትን ሥራ አይሠራም። እንደማሳያ ዖዝያን ይመለከቷል (2ኛ ዜና 26)።

እግዚአብሔር ለመንግሥትና ለቤተ ክርስቲያን የውክልና ሥልጣን ነው የሰጣቸው። የሥልጣን ውክልናቸው፣ እግዚአብሔር የሚከለክለውን ማድረግን ወይም የሚያዝዘውን መከልከልን አይጨምርም። የመንግሥት አርማ ሰይፍ ነው፤ የተሰጠውን ኀላፊነት ለማስፈጸም ሲያስፈልግ ኀይል መጠቀም ይችላል። የቤተ ክርስቲያን ግን መስቀል ነው። ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ለማከናወን ኀይል መጠቀም አትችልም። በቃሉ ጕልበት፣ በአገልግሎት ጕልበትና ክርስቶስን በመምሰል ጕልበት ነው ተልእኳን የምትፈጽመው። የቤተ ክርስቲያን ሥራ የክርስቶስ ምስክር መሆን ነው።

እግዚአብሔር ለመንግሥትና ለቤተ ክርስቲያን የውክልና ሥልጣን ነው የሰጣቸው። የሥልጣን ውክልናቸው፣ እግዚአብሔር የሚከለክለውን ማድረግን ወይም የሚያዝዘውን መከልከልን አይጨምርም። 

ከመንግሥት ተግባሮች ውስጥ፣ ሕዝብን ክፉ እንዳይደርስበት መከላከል፣ የሰውን ሕይወት መጠበቅና መንከባከብ፣ ዜጋ በግሉ ያፈራውን ሀብትና ንብረት መጠበቅ፣ ውሎችን መጠበቅና ማስከበር፣ ሚዛን እውነተኛ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ደምብ አውጥቶ እንስሳትንና አካባቢን መንከባከብ ይገኙባቸዋል።

መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን ጥሪያቸው ለየቅሉ ይሁን እንጂ የሚተጋገዙ ናችው። ቤተ ክርስቲያን ለመንግሥት ትጸልያለች፤ ድጋፍ ታደርጋለች። ምእመኖቿ ቀረጥ (ግብር) ይከፍላሉ። መንግሥት በቤተ እምነቶች መካከል ልዩነት ሳያደርግ የቤተ ክርስቲያንን ነጻነት ያረጋግጣል፤ ከሚያጠፏትም ይከላከልላታል።

ቤተ ክርስቲያን (ምእመናን) በተቻለው ሁሉ ለመንግሥት መሪዎች መታዘዝ ይኖርባቸዋል። ለዚህም ምክንያቱ በእግዚአብሔር መሾማቸው ነው። ይሁን እንጂ፣ የቤተ ክርስቲያን (የምእመናኑ) ቅድሚያ ታማኝነቷ  ለእግዚአብሔር ነው። ከእግዚአብሔር በውክልና ከተሰጠው ማዕቀፍ ዐልፎ ትእዛዝ ቢያወጣ፣ መንግሥትን  ቤተ ክርስቲያን (ክርስቲያኖች) ላትታዘዝ ትችላለች። እንዲያውም እንዳትታዘዝ ብቻ ሳይሆን፣ ከማዕቀፉ ወጥቶ ስላወጣው ትእዛዙ መንግሥትን እንድትወቅስ ግዴታ አለባት።

በርግጥ በእግዚአብሔር የተከለከለውንና የተፈቀደውን ለይቶ ለማወቅ፣ ነፍስን አስጨንቆ መመርመር፣ በንጹሕ ኅሊና መመዘንና ጥንቃቄ ማድረግ ያሸዋል። መንግሥት በቤተ ክርስቲያን ሥራ ውስጥ (ለምሳሌ፣ በምትወስደው የዲስፕሊን እርምጃ ወይም የምታስተምረውን ትምህርት ትክክለኛነት በማረጋጋጥ ወዘተርፈ) ጣልቃ አይገባም።

ከእግዚአብሔር በውክልና ከተሰጠው ማዕቀፍ ዐልፎ ትእዛዝ ቢያወጣ፣ መንግሥትን  ቤተ ክርስቲያን (ክርስቲያኖች) ላትታዘዝ ትችላለች። እንዲያውም እንዳትታዘዝ ብቻ ሳይሆን፣ ከማዕቀፉ ወጥቶ ስላወጣው ትእዛዙ መንግሥትን እንድትወቅስ ግዴታ አለባት። 

እንደ R. C Sproul ጽሑፍ ከሆነ፣ በመንግሥትና በቤተ ክርስቲያን መካከል የሚኖረው ግንኙነት ይህን ይመስላል። የአሰሳ ጥናት ባይኖረኝም፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እምነትም ከዚህ የራቀ እንዳልሆነ ግምት አለኝ። ከሆነ፣ በቃልም በሥራም እንደዚሁ ለመኖር እንድንችል እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልን።

መንግሥትን በሚፎካከሩ (በሚገዳደሩ) ቡድኖችና በቤተ ክርስቲያን መካከል ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት ለማወቅ ፈልጌ ለጊዜው የሚያስረዳኝ ጽሑፍ አላገኘሁም። አንድ የክርስቲያን ሬዲዮ ጣቢያ፣ ከተወከለበት ዐልፎ የሠራን የአገር መሪ ስለመቃወም “ዲትሪክ ቦንሖፈር”ን (Dietrich Bonhoeffer) ምሳሌ አድርጎ በተደጋጋሚ ሲጠቀሰው እሰማለሁ። የፕሮቴስታንት ነገረ መለኮት አዋቂና የሉተራን ቤተ ክርስቲያን ፓስተር የነበረው ይህ ሰው ሂትለርን በመቃወሙ ይታወቃል።

ሂትለርን ያሸነፉ ወገኖችና ሂትለር በሠራው ግፍ የሚሳቀቁ ሁሉ፣ በጊዜው የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ሲወቅሱ፣ “ቦንሖፍር”ን ግን በአድናቆት ያነሡታል።

በመጀሪያው የዓለም ጦርነት ጀርመን መሸነፏን ተከትሎ ኢኮኖሚዋ ደቅቆ ነበር። በጀርመን ሕዝብ ላይ ኑሮ ከበደ። አብዛኛው የጀርመን ሕዝብ በዚያን ጊዜ ብቅ ያለውን ባለ ግርማ ሞገሱን ሂትለርን ተስፋ ጣለበት። ስብራቱን የሚጠግን የጸሎት መልስ አድርጎ ወሰደው። ዲትሪክ ቦንኾፈር ግን የሂትለርን ፓሊሲና ናዚነትን ተቃወመ፤ አይሁዶችን በማትረፍ ሥራም ተካፈለ፤ በመጨረሻም በስቅላት ተገደለ። ሂትለርን ያሸነፉ ወገኖችና ሂትለር በሠራው ግፍ የሚሳቀቁ ሁሉ፣ በጊዜው የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ሲወቅሱ፣ “ቦንሖፍር”ን ግን በአድናቆት ያነሡታል።


[1] Sproul, R. C. (2014). What Is the Relationship between Church and State? (First edition, Vol. 19,). Orlando, FL; Sanford, FL: Reformation Trust; Ligonier Ministries.

Bantu Gebremariam

ባንቲ ገብረ ማርያም በፋርማሲ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በፋርማኮሎጂ የማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም በቢብሊካል ካውንስሊንግ ማስተርስ ዲፕሎማ የሠሩ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም “Comparative Theology” - “የነገረ መለኮት ንጽጽር” በሚል እንዲሁም “Forgiveness to Let Go” - “ይቅር ማለት- ለመተው ነጻነት” የተሰኙ መጻሕፍትን ወደ አማርኛ መልሰዋል። E-mail: bantge@yahoo.com

Share this article:

የምፀት ምድር

ይህ የዶ/ር ግርማ ጽሑፍ ኢትዮጵያ እጅግ ፈጣን በሆነ ተለዋዋጭ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሥሪት ውስጥ እያለፈች ያለች አገር ሆናለች። ይህ የዶ/ር ግርማ በቀለ ጽሑፍ፣ አገሪቱ በብዙ ምጸት የተሞላች ምድር ነች ያላታል።

ተጨማሪ ያንብቡ

ነውር የሌለው አምልኮ

በኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቤተ ክርስቲያን ከሚያዚያ 2–3፣2006 ዓ.ም.“ጉባኤ ስለ ወላጅ አጥ ልጆች በኢትዮጵያ፡- ሀገራዊ ጥሪ ለሀገራዊ መፍትሔ” በሚል መሪ ቃል ጉባኤ ተካሄዶ ነበር። ጉባኤውን ያዘጋጁት “ቤታኒ ክርስቲያን ሰርቪስስ”፣ “ሜክ ዩር ማርክ”፣ “ቅድሚያ ፋውንዴሽን”፣ “የልጆች ዕድገት ሥልጠናና ምርምር ማዕከል” እንዲሁም “አባት ለሌላቸው ብሩኅ ተስፋ” ሲሆኑ፣ ድርጅቶቹም በልጆች አገልግሎት ዙሪያ የተለያየ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተቋማት ናቸው። በዝግጅቱ ላይ 470 የሚደርሱ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ የተለያዩ ቤተ ሰቦች እና ለልጆች ልዩ ሸክም ያላቸው ወገኖች እንደታደሙ ከአዘጋጆቹ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ተጨማሪ ያንብቡ

1 comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

  • እንዲሰጠን እንጸልይ ወይስ እንዲሁ እንኑር? ቦንሆፌር ጥፋተኛ ነው? የእግዚአብሔር ሥርዓት የጣሰ ወይስ ሥርዓቱ ሲጣስ የጮኼ ጀግና? ቤተ ክርስቲያን ዝም ያለች ጊዜ ራሱን የሰዋ ጀግና ከሆነ እንደሱ ያሉት እንድነሡ ጸሎት ማድረግ ክፋት ይኖረው ይሆን

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.