[the_ad_group id=”107″]

ሚዲያውን ቸል አንበለው!

ለወንጌል ሥራ ስላለው ጠቃሜታ ብዙ የተባለለት የብዙኀን መገናኛ በእኛ አገር የአቅሙን ያህል እንዳልተጠቀምንበት ለብዙዎች የተሰወረ አይደለም፡፡ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች አንድም ከግንዛቤ ጉድለት፣ አንድም ደግሞ ከፍላጎት ማጣት የተነሣ ቸል ያሉት ይህ የአገልግሎት ዘርፍ አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊነቱ ጎልቶ እየታየ መጥቷል፡፡

ይህንን የተረዱ ጥቂት ግለ ሰቦችና ቤተ ክርስቲያናት የአገልግሎት ዘርፉን ተቀላቅለው ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ፡፡ “ጥቂት” የምንለው አማኝ ማኅበረ ሰቡ ካለው ቁጥር አንጻር ሲታይ አሁን ያሉት (የነበሩትን ጨምሮ) የክርስቲያን ሚዲያ አባላት እጅግ አነስተኛ ከመሆናቸው የተነሣ ነው፡፡ እነዚሁ ግለ ሰቦችና ተቋማት የበኩላቸውን ጥረት ቢያደርጉም እንኳ ሊደርሱት ከሚፈልጉት ሕዝብ አነጻር ውጤታማነታቸው ያን ያህል አመረቂ ስለመሆኑ በርግጠኝነት መናገር አይቻልም፡፡ ከዚያም ባለፈ የሠሯቸውና እየሠሯቸው ያሉ ስሐተቶች ብዙዎች የአገልግሎት ዘርፉን እንዲፈሩት፣ እንዲሸሹት ብሎም እንዲጠሉት ሳያደርገው አልቀረም፡፡

ሕንጸት መጽሔት የአገልግሎት ዘርፉን፣ በተለይም ደግሞ የቴሌቪዥን አገልግሎቱን ርእሰ ጉዳይ አድርጎ ያነሣበት ዋናው ምክንያት ዘርፉ ያለበትን ድክመት በመጠቆም የተሻለ ደረጃ የሚያደርሰውን መንገድ ለመፈለግ ነው፡፡ ባሉብን ችግሮች ላይ በግልጽ መወያየት ካልቻልን፣ ችግሮቻችንን መቅረፍም ሆነ የተሻለ አገልግሎት መስጠት አንችልም ብለን በጽኑ እናምናለን፡፡ ስለሆነም፣ ርእሰ ጉዳዩ ይመለከተናል የሚሉ ማናቸውም አካላት፣ የኢትዮጵያ የክርስቲያን ብዙኀን መገናኛ አገልግሎትን ለማሳደግና የተሻለ ለማድረግ ኀላፊነት በተሞላው መልኩ እገዛ ሊያደርጉለት ይገባል፡፡ በአገልግሎት ዘርፉ የተሰማራን  ወገኖችም ያሉብንን ክፍተቶች ለመሙላት እስከዛሬ የመጣንበትን መንገድ መመርመር፣ ብሎም ከስሕተቶቻችን ለመማር ራሳችንን ትኁታን የማድረጊያው ጊዜ አሁን እንደ ሆነ በማመን ልንተጋ ያስፈልገናል፡፡

ነውር የሌለው አምልኮ

በኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቤተ ክርስቲያን ከሚያዚያ 2–3፣2006 ዓ.ም.“ጉባኤ ስለ ወላጅ አጥ ልጆች በኢትዮጵያ፡- ሀገራዊ ጥሪ ለሀገራዊ መፍትሔ” በሚል መሪ ቃል ጉባኤ ተካሄዶ ነበር። ጉባኤውን ያዘጋጁት “ቤታኒ ክርስቲያን ሰርቪስስ”፣ “ሜክ ዩር ማርክ”፣ “ቅድሚያ ፋውንዴሽን”፣ “የልጆች ዕድገት ሥልጠናና ምርምር ማዕከል” እንዲሁም “አባት ለሌላቸው ብሩኅ ተስፋ” ሲሆኑ፣ ድርጅቶቹም በልጆች አገልግሎት ዙሪያ የተለያየ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተቋማት ናቸው። በዝግጅቱ ላይ 470 የሚደርሱ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ የተለያዩ ቤተ ሰቦች እና ለልጆች ልዩ ሸክም ያላቸው ወገኖች እንደታደሙ ከአዘጋጆቹ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ተጨማሪ ያንብቡ

እውን ክርስቲያኖች ሳይሞቱ ለዘላለም ሊኖሩ ይችላሉ?

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቴሌቪዥን መስኮት ብቻ እናውቃቸው የነበሩ አንዳንድ አፍሪካውያን “አገልጋዮች” በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ መታየት ጀምረዋል። በቅርቡ የተከሰቱ ሁለት ኩነቶችን እንኳ ብንመለከት “ሜጀር ሼፐርድ ፕሮፌት” ቡሽር ከማላዊ፣ “ነቢይ” ኮቦስ ቫን ሬንስበርግ ከደቡብ አፍርካ ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ልብ ይሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ

የነገረ መለኮት ነገር

ክርስትና በአፍሪካ ውስጥ በስፋት በመስፋፋት ላይ እንደ ሆነ የተለያዩ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ሆኖም ግን ʻእየተስፋፋ ያለው ክርስትና ምን ዐይነት ገጽታ አለው?ʼ የሚለው ትኩረት የሚያሻው ጥያቄ ነው። የቁጥር ዕድገት ቤተ ክርስቲያን በማኅበረ ሰቡ ውስጥ ያላትን መገኘት በማግዘፍ የሚኖራትን ሚና ያጎላዋል። በተመሳሳይ መልኩ ደግሞ ዕድገቱ የተለያዩ ተግዳሮቶችን ይዞ ይመጣል። ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ዕድሎች የማትጠቀም ወይም ለተግዳሮቶች ምላሸን የማትሰጥ ከሆነ በምትኖርበት ማኅበረ ሰብ ውስጥ ያላት ፋይዳ እጅግ አናሳ ይሆናል።

ተጨማሪ ያንብቡ

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.