
Persecuted Chinese Pastor Issues a ‘Declaration of Faithful Disobedience’
A persecuted Reformed pastor in China champions religious freedom and explains the necessity of faithful disobedience.
[the_ad_group id=”107″]
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ፣ “ጥቁር ቀን” ከሚባሉት መካከል እንደ ጐርጐሮሳውያኑ አቈጣጠር፣ ዕለተ ቅዱስ በርጤሜዎስ (August 24, 1572) አንዱ ነው። በዚህ ዕለት በፓሪስ ከተማ ከሦስት ሺሕ በላይ የሆኑ የፈረንሳይ የተሐድሶ አማኞች (ሂውገናትስ – The Huguenots) በጅምላ ጭፍጨፋ ያለቁበት ቀን ነው። የዚህም ዘግናኝ እልቂት ጠንሳሽ የፈረንሳይ ንግሥት ካትሪን ደ ሚዲሲ (Catherine de’ Medici, 13 April 1519 – 5 January 1589) ነበረች። ታሪክ እንዲሚያስረዳን፣ ካትሪን በ1559 የሞተው የፈረንሳዩ ነጉሥ ዳግማዊ ሄነሪ ባለቤትና በተከታታይ የአገሪቱ ነገሥታት የነበሩት ዳግማዊ ፍረንሲስ፣ ቻርልስ ዘጠነኛ አና ሳልሳዊ ሄነሪ እናት ነበረች። በወቅቱ በነበረው የፈረሳይ ንጉሣዊ አገዛዝና የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አመራር ውስጥ ግልጽና ስውር የሆነ ከፍተኛ ተጽዕኖ ነበራት። ከዚህ የተነሣ ነበር፣ የባለቤቷ ዳግማዊ ሄነሪና የልጆቻቸው የንግሥና ዘመን “የካትሪን ደ ሚዲሲ” አገዛዝ ተብሎ የሚታወቀው።
በዚሁ የአገዛዝ ዘመን፣ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በፈረንሳይን የተሐድሶ አማኞች ላይ ያወጀችው ስደት ዘውዳዊ ድጋፍ አግኝቶ ነበር። ለምሳሌ፣ በቀዳማዊ ፍራንሲስ ዘመን በሰሜናዊ ምሥራቅ ፈረንሳይ በMarch 1, 1562 የተፈጸመውን የቫሲ የጅምላ ግድያ (The Massacre of Vassy) መጥቀስ ይቻላል። በዚህች ከተማ የሚኖሩት የተሐድሶ አማኞች ቍጥራቸው ትንሽ ቢሆንም፣ ሚስዮናዊ እንቅስቃሴያቸው ለሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሥጋት ነበር። በወቅቱም ዙፋንና ቤተ ክርስቲያን እንደ እጅና ጓንት የሆነ ግንኙነት ነበራቸው። አንዱ የሌላው ሕልውና ጥቅም ጠባቂ ነበር። በርግጥ ነገሥታቱ ከሃማኖታዊ ቀናዒነት በላይ የሚያሳስባቸው ዙፋናቸው ነበር።
እነዚህ ሁለት ቤተ ሃይማኖቶች፣ በብዙ የአካል፣ የመንፈስና የስሜት ስብራት ውስጥ ላለው ሕዝባችን ዐደራ አለባቸው። ሁለታችንም ቤተ ሃይማኖቶች የግልና የጋራ ንስሓ ያስፈልገናል።
እንደ ኀይል ሚዛኑ፣ በሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና በተሐድሶ አማኞች መካከል ያለውን ውጥረትም ለማብረድ ሙከራ አድርገዋል። ለዚህም የተሐድሶ አማኞች የተገደበ የአምልኮ ነጻነት ለመስጠት የወጣውን የቅዱስ ዣርማ ዐዋጅ (The Edict of Saint-Germain, January 1562) በአብነት መጥቀስ ይቻላል። ሆኖም ይህ ሃይማኖታዊ የመቻቻል ዐዋጅ እየከፋ ይሄድ የነበረውን ስደት፣ እንዲሁም ከዐሥር ዓመታት በኋላ በቅዱስ በርጤሜዎስ ዕለት የተፈጸመውን ዘግናኝ የጅምላ ግድያ ሊያስቈም አልቻልም።
በሰላማዊ መንገድና የሌላውን ክብርና ሰብእና እስካልጐዳ ድረስ፣ የየትኛውም እምነተ ተከታይ የሚያምንበትን እውነት፣ “የተሻለና ብቸኛ” አድርጐ መቀበሉን፣ ማስተማሩንና አስተምህሮውን ሰው ሁሉ እንዲያውቅለት ማሠራጨቱን በቅን ልቦና ልንቀበለው ይገባል።
ሃይማኖትንና ዘርን መሠረት ያደረጉ ጥላቻዎች በወቅቱ ካልበረዱ፣ ጥፋታቸው ቀላል አይሆንም። ታዋቂው የፈረንሳይ መኳንንትና የጦር መሪ የነበረው አድሚራል ጋስፓር ደ ኮለኒ (Gaspard de Coligny, 16 February 1519 – 24 August 1572) የተሐድሶ እምነት መቀበሉ፣ ለካትሪን ደ ሚዲሲ አገዛዝ ትልቅ ስጋት ነበር። በቻርልስ ዘጠነኛ ንግሥና ወቅት ለፈረንሳይ የተሐድሶ አማኞች ነጻነትና መብት በግልጽ ይሟገት ነበር። የካትሪንን “የማረጋጋት ዐዋጅ” (Edict of Pacification – 19 March 1563) ደግፏል። ይሁን እንጂ፣ በንጉሣዊ አገዛዝ ውስጥ የነበረው የመኳንንቶች ሽኩቻ፣ የኀይል ሚዛኑ ወደ ሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲያጋድል ስደቱም እየከፋና ዐመፅ እየለበሰ መጣ። በሮማ ካቶሊካዊት ለኳሽነት፣ በ1562 በተጀመረው የሃይማኖት የእርስ በእርስ ጦርነት ላይ ሂውገናትስን በመደገፍ በጦርነት ተሳትፏል። ነፍሱን ለማጥፋት ብዙ ሙከራዎች ተደርገዋል፤ በመጨረሻም የዕለተ ቅዱስ በርጤሜዎስ ጭፍጨፋ ላይ የመጀመሪያው ተገዳይ ነበር።
በአገራችን ፓለቲካዊና ሃይማኖታዊ ታሪክ ውስጥም በርካታ ተመሳሳይ የዐመፅ ዝክሮች አሉ። የአውሮፓ ታሪክ በእርስ በእርስ ጦርነት በደም የተለወሰ ነው። ሆኖም የተዘጋ ታሪክ ነው፤ ቢያንስ ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት በኋላ። የእኛስ የዐመፅ መንገድ ማብቂያው መቼ ይሆን? ፓለቲካዊ ሽግግሮቻችን በደም የተነከሩ፣ ግራና ቀኛቸውን የማያውቁ የብዙ ንጹሓንና ድኾች ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈ ነው። ከከፋፋይ፣ አወጋጋጅና አክሳሪ የዐመፅ ዑደት አዙሪት መውጣት ተስኖናል። ያለፉት ሁለት ዓመታት ጦርነት፣ በአሁኑ ወቅት በየቦታው ያሉ ዘር ተኰር ግድያዎች (በተለይም በኦሮሚያ ክልል)፣ እንዲሁም ክፍፍል ከራሳችንም ሆነ ከሌሎች አገራት ታሪክ መማር ያለመቻላችንን እጅግ ልብ በሚሰብር መልኩ ግልጽ አድርገው ያሳዩናል። የሰሜኑ ጦርነት፣ በጭፍን ጥላቻ ወይም ወገንተኝነት ቤተ ሃማኖቶችን ሳይቀር በውስጥም በውⶽ ከፋፍሏል። በአንድ ልብም መጸለይ ተስኖናል። የቅርቡም “የሰላም ስምምነት” ተፈጻሚነት ላይ ሥጋት ማንዣበብ ጀምሯል። ብዙ ቅጥሮች የፈረሱባት ምድር ውስጥ እንዳለን ልብ ልንል ይገባል።
ባለፉት ሠላሳ ዓመታት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያና የወንጌል አማኞች በመካከላቸውና እርስ በእርስም ያላቸው መከፋፈል፣ መንግሥትን “ሃይ” ለማለት የሚያስችል የሞራል ልዕልና ነፍጓቸው ቈይቷል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስብራት የነበረው የሲኖዶስ መከፈልና የቀድሞውን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስን ለስደት የዳረገው፣ ከስደትም መልስ ሁለት ፓትርያርኮችን በአንድ መንበር ላይ ያስቀመጠው መከፍል ዘር ተኰር ፓለቲካዊ ይዘት እንደ ነበረው የአደባባይ ምስጢር ነበር።
ባለፉት ሠላሳ ዓመታት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና የወንጌል አማኞች በመካከላቸውና እርስ በእርስም ያላቸው መከፋፈል፣ መንግሥትን “ሃይ” ለማለት የሚያስችል የሞራል ልዕልና ነፍጓቸው ቈይቷል።
የወንጌል አማኞች “በነጻነት” ሰበብ የመንግሥት የውለታ እስረኝነቱ፣ ሚዛን ወደ አጣ ግንኙነት አዝግሟል። የቤተ ክርስቲያንንና የመንግሥትን ድንበር ያደበዘዘ፣ እንዲሁም የወንጌልንና የባሕልን መስተጋብር ያጣረሰ ትሥሥር ፈጥሯል። ይህም ቁርኝት ለተልእኳዊ የማንነት ቀውስ ዳርጎናል። ርቱዕ ትምህርትን መሥዋዕት ባደረገ “አንድነት” የተወለደው ሁሉን ዐቃፊነት ለመልእክታችን ቅቡልነትን ነፍጐታል። በማኅበራዊና በፓለቲካው ረገድ ደግሞ፣ በፍትሕ ጕዳዮች ለዝምታ ኀጢአት፣ ለጭፍን ደጋፊነት ወይም ተቃዋሚነት ፈተና አሳልፎ ሰጥቶናል።
ወንድማችን ዮናታን አክሊሉ ያስነሣው ውዝግብ ከፍ ሲል በጠቀስሁት አጠቃላይ ዐውድ ሊታይ ይገባዋል ባይ ነኝ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በወንጌላውያን አማኞች መካከል ያለውን ታሪካዊ የአግላይነት ውጥረት ይበልጡን የሚያከርሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛንና ብስለት ያጡ አስተምህሮቶች እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የጐደላቸው ሥነ ምግባራዊ ቀውሶች መታየት ከመጀመሩ ሰንብተዋል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ፣ በእነዚሁ ሁለት ታላላቅ ቤተ እምነቶች ውስጥ ያለው የእርስ በእርስ መከፋፈል፣ ጐሣዊና ፖለቲካዊ ጽንፈኝነትን የተላበሰ በመሆኑ፣ የአገሪቱን ፈርጀ ብዙ መከራ የበለጠ አክብዶታል።
የቤተ ክርስቲያንንና የመንግሥትን ድንበር ያደበዘዘ፣ እንዲሁም የወንጌልንና የባሕልን መስተጋብር ያጣረሰ ትሥሥር ፈጥሯል። ይህም ቁርኝት ለተልእኳዊ የማነነት ቀውስ ዳርጎናል።
በእኔ ዕይታ የሰሞኑ ውዝግብ፣ ቀደም ሲልም በማኀበራዊ መገናኛ ብዙኃን፣ ከሁለቱም ወገን ይሰሙ የነበሩ ጥበብና ብስለት የጐደላቸው የራስ ግንዛቤዎች፣ የአስተምህሮ፣ የሥነ ምግባርና የአመራር ቀውሶች የከፋ መገለጫቸው ነው። እኔ አባል በሆንሁባት የወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ብዙ ዐንገት ያስደፉን፣ ቅቡልነትና ተኣማኒነት የነፈጉን ቀውሶች አሉን። እጅግ ተከፋፍለናል፤ ማንም በፊቱ ደስ የሚለውን የሚያደርግበት የዘመነ መሳፍንት ዐይነት የአመራር ውጥንቅጥ ውስጥ ገብተናል። ርቱዕ የሆነ የጋራ የወንጌል አማኞች ድምፅ የለንም። ስለዚህ በሚድያ ተጽእኖ ያላቸው፣ ያልተሰየሙ አገራዊ መሪዎች ተነሥተዋል። ሊወክሉን ግን አይገባም ነበር። ወዳጄ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ እንዳለው፣ “ዮናታን ገድላቱን በተመለከተ የነገረን ነገር ዐዲስ አይደለም። ብዙዎች የሚያውቁት፣ የኦርቶዶክስ ምሁራን ጭምር ቢታረም የሚል ለቤተ ክህነት አስተያየት ያቀረቡበት ጒዳይ እንደ ሆነ ይታወቃል . . . ወገን፣ የአስተምህሮ ንጽሕና ብቻ ሳይሆን፣ ገቢራዊ ፋይዳን ተከትሎ ወንጌልን መስበክ፣ ዘመኑ በብርቱ የሚፈልገው ሰማያዊ ጥበብ ነው!።” አቀራርብ ብቻ ሳይሆን የአቅራቢዎቹ ነገረ መለኮታዊ ብልሹነትና ከፍ ሲል የጠቀስኋቸው ቀውሶች ምክንያት መሆናቸው ትልቅ ችግር ነው። ጌታና ሐዋርያቱም በቍጣ ተናገርዋል፤ ሆኖም ግን በጽድቅ ነበር። እውነት፣ አክብሮት፣ ፍቅርና የውስጥ ግፊት ንጽሕናንም ይጠይቃል!
ሃይማኖታዊ መቻቻል ማለት ልዩነቶችን መካዳ፣ ልዩነትን ማፍረስ ወይም ልዩነትን ማሳነስ ማለት እንዳልሆነ ሊሠመርበት ይገባል።
ቢያንስ 1700 ዓመታት በዘለቀው ታሪኳ ውስጥ በብዙ መከራና ፈተኝ ሁኔታ ውስጥ ጸንታ የቈየቸው፣ የተከበረችዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በኢትዮጵያና ዓለም ዐቀፍ ታሪክ ውስጥ የከበረ ስፍራ አላት። በብዙ ረገድ “ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ” ናት። ሆኖም ልክ እንደ ወንጌላዊት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ የማንነትና የተልእኳዊ ራስ ግንዛቤ ፍተሻ ያስፈልጋታል። በሰፊ ልብ ከታየ፣ ዮናታን ያስነሣው ውዝግብ መግቦታዊ (providential) ነው። ሁለቱንም ቤተ ሃይማኖቶች ለእውነትኛ ነስሓ ይጣራል። ቅይጥነት (syncretism)፣ ገድላት፣ ታምራት፣ ፍካርያት፣ ድርሳናት፣ ወዘተ. ከቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ ጋር ተቈራኝተዋል። ነገረ መለኮት የተማሩ ቀሳውስት ዕጥረት፣ ከጅማሮዋ የመንግሥት እምነት ሆና መመሥረቷ፣ እንዲሁም እስከ 1959 ድረስ በእስክንድርያ መንበር ከግብፅ መተዳደሯ እንዲሁም በገዳማት መካከል ለስመ ጥርነት ይደረግ የነበረ ፉክክር የወለዷቸው ሃይማኖታዊ የፈጠራ ገድላትና ድርሳናት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። በዐጭር ቃል፣ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት ሥር የሰደደ የአመራር ብቃት ትልቅ ችግር ነበረባት። ይሁን እንጂ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ክርስትና ለማቈየት የታገሉ፣ ሰማዕት የሆኑ፣ አሁንም የሚጥሩ አባቶችም እንዳሏት ልብ ልንል ይገባል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በወንጌላውያን አማኞች መካከል ያለውን ታሪካዊ የአግላይነት ውጥረት ይበልጡን የሚያከርሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛንና ብስለት ያጡ አስተምህሮቶች እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የጐደላቸው ሥነ ምግባራዊ ቀውሶች መታየት ከጀመሩ ሰንብተዋል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ፣ በእነዚሁ ሁለት ታላላቅ ቤተ እምነቶች ውስጥ ያለው የእርስ በእርስ መከፋፈል፣ ጐሣዊና ፖለቲካዊ ጽንፈኝነትን የተላበሰ በመሆኑ፣ የአገሪቱን ፈርጀ ብዙ መከራ የበለጠ አክብዶታል።
1) ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንመለስ። የቤተ ክርስቲያን ራስ የሆነው እንዲያጸዳን ልንፈቅድለት ይገባል። “ከዚያም ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በቤተ መቅደስ ውስጥ ይሸጡና ይገዙ የነበሩትን አባረራቸው፤ የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛና የርግብ ሻጮችን መቀመጫ በመገለባበጥ፣ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፏል፤ እናንተ ግን፣ የዘራፊዎች ዋሻ አደረጋችሁት” አላቸው (ማቴዎስ 21፥12-13)። በአስተምህሮ፣ በአመራር፣ በሥነ ምግባር እንዲሁም ከመንግሥትና ከባሕል ጋር ያሉንን መስተጋብሮች ልንፈትሽና ልናጸዳ ይገባናል። ይህም እውነተኛ ንስሓንና መመለስን ይጠይቃል።
ከብዙ አክብሮት ጋር፣ ወዷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ እጅግ ለዘገዩት የቅይጥነት (syncretism)፣ ገድላት፣ ታምራት፣ ፍካርያት፣ ድርሳናት፣ ወዘተ. ውዝግቦች፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ ምላሽ መስጠት ያሻታል። በተለይም የነገረ መለኮት ሊቃውንቷ በጌታ ዘንድ ተጠያቂነት ያለበት ዐደራ አለባቸው።
2) ወንጌል በመንፈስ ቅዱስ ኀይል፣ በሕይወት ምስክርነትና በፍቅር እንጂ በሌላ ድጋፍ አይሰበክም። ቤተ ክርስቲያን በነገሥታት መካከል ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት ወኪል ናት። የግራ፣ የቀኝ፣ የባሕል፣ የመንግሥት ወይም የተፎካካሪ ተቀጥያ አይደለችም። ይህ ድንበር ሲፈርስ፣ መልእክቷም ቅቡልነት ያጣል። በተለይም የወቅቱ የወንጌላውያን እምነት ከዚህ ፈተና ራሱን ሊያጸዳ ይገባል። ቤተ ክርስቲያን በስደትም ፍሬያማ እንደ ነበረች ልብ ይሏል።
ወንጌል በመንፈስ ቅዱስ ኀይል፣ በሕይወት ምስክርነትና በፍቅር እንጂ በሌላ ድጋፍ አይሰበክም።
3) መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነትን መናገር በአስተምህሮ ርቱዕነትና በሕይወት ምስክርነት ንጽሐና የታጀበ ሊሆን ይገባዋል። በቀዳሚነት ሊመስክር የሚገባው ሕይወታችን ነው። አስተምህሮን አስመልክቶ፣ የመጨረሻው ታማኝነታችን ለቅዱስ ቃሉ የበላይነትና ለክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነት ሊሆን ይገባዋል። ይህ ሊጨመር፣ ሊቀነስ ወይም ሊሻሻል የማይችል እውነት ነው። “ነገር ግን እኛም ብንሆን ወይም የሰማይ መልአክ፣ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ እርሱ ለዘላለም የተረገመ ይሁን። ቀደም ብለን እንዳልነው፣ አሁንም ደግሜ እላለሁ፤ ማንም ከተቀበላችሁት ሌላ የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።” (ገላትያ 1፥8-9)።
4) የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን፣ ታሪኳ የቅርብ ጊዜ ቢሆንም በመከራ ውስጥ በአፋጣኝ ያደገችና ብዙ በጐ አስተዋጽኦ ያደረገች ናት። የስደቷ ምንጮች መንግሥትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሆናቸው የሚካድ አይደለም። ሆኖም መከራቸውን፣ እንደ ቅዱስ ቃሉ ለጌታ ብለው በደስታ በመቀበል፣ በእንግልታቸው ሁሉ ለክርስቶስ ወንጌል ታማኞች ሆነው ኖረዋል፤ በዝተዋል፤ ሰፍተዋል። በነጻነትም ያለ ነጻነትም፤ መብት ሲነፈግም፤ መብት ሲከበርም መኖር ያለብን ለክርስቶስ ነው። “ተራው የእኛ ነው” ከሚል ፈተና ወይም ሌሎች እንዲህ እንዲሰማቸው ከሚያደርግ ፈተና ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል።
በእኔ ዕይታ የሰሞኑ ውዝግብ፣ ቀደም ሲልም በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን፣ ከሁለቱም ወገን ይሰሙ የነበሩ፣ ጥበብና ብስለት የጐዳለቸው የራስ ግንዛቤዎች፣ የአስተምህሮ፣ የሥነ ምግባርና የአመራር ቀውሶች የከፋ መገለጫቸው ነው።
5) ማንኛውም ሃይማኖት፣ የራስን እምነት በግልጽም ሆነ በአደባባይ በነጻነት ማወጅንና መኖርን ይጠይቃል። ሃይማኖታዊ መቻቻል ማለት ልዩነቶችን መካድ፣ ልዩነትን ማፍረስ ወይም ልዩነትን ማሳነስ ማለት እንዳልሆነ ሊሠመርበት ይገባል። አንድ ሰው ለሚያምንበት እምነት የሚያሳያው ወገንተኝነት ተፈጥሯዊ ነው። መለያየትንና መከፋፈልን፣ ጥላቻንና ዐመፅን እስካልቀሰቀሰ ድረስ፣ በየትኛውም የእምነት ጐራ ያለ አማኝ፣ ከእምነቱ ጋር የሚጻረረውን የሌላውን ሃይማኖታዊ ቀኖና “ትክክል አይደልም” ብሎ ማሰቡ፣ ለሃይማኖቱ ያለውን ታማኝነትና የኅሊና ነጻነት በጒልህ ያሳያል። ይህም ቅቡልነት ያለው ልዩነት ነው።
6) በአስተምህሮ ዙሪያ ያሉ የማይታረቁ ልዩነቶች ግን፣ ጠበኛ ሊያደርጉን አይገባም። በሰላማዊ መንገድና የሌላውን ክብርና ሰብእና እስካልጐዳ ድረስ፣ የየትኛውም እምነት ተከታይ የሚያምንበትን እውነት፣ “የተሻለና ብቸኛ” አድርጐ መቀበሉን፣ ማስተማሩንና አስተምህሮውን ሰው ሁሉ እንዲያውቅለት ማሠራጨቱን በቅን ልቦና ልንቀበለው ይገባል። የአስተምህሮ ልዩነቶችን በነጻነት፣ ሆኖም በፍቅር ልንናገር እንዲሁም ልንወያይባቸው ይገባል። ልዩነቶቻችን ለመቈሳሰል፣ ለመገፋፋትና ለዐመፅ ሊጋርዱን አይገባም።
ከብዙ አክብሮት ጋር፣ ወዷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ እጅግ ለዘገዩት የቅይጥነት (syncretism)፣ ገድላት፣ ታምራት፣ ፍካርያት፣ ድርሳናት፣ ወዘተ. ውዝግቦች፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ ምላሽ መስጠት ያሻታል። በተለይም የነገረ መለኮት ሊቃውንቷ በጌታ ዘንድ ተጠያቂነት ያለበት ዐደራ አለባቸው።
7) አገራችን ካንዣበበባት የክፍፍል ጽልመት ለመውጣት በምታደርገው የተግባቦት፣ የዕርቅና የፈውስ አዝጋሚ ጒዞ ውስጥ፣ የሃይማኖት ተቋማት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። አለመተማመን፣ ቂመኝነት፣ አግላይነትና መወጋገድ፣ አልሰበር ያለንን የዐመፅና የመከራ ዑደት ይበልጥ እያከረሩት ይገኛሉ። ከየትኛውም ጊዜ በላይ፣ የሃይማኖት ተቋማት ምስባካቸውን አግላይ ከሆኑ አክራሪዎችና ፓለቲካዊ ተጽእኖዎች የመጠበቅ ዐደራ ወድቈባቸዋል። ይህን መከባበርና መቻቻል ሊያደፈርሱ ከሚችሉ ድንበር ተሻጋሪም ሆነ አገር በቀል አክራሪነት የመከላከል ዐደራና ኀላፊነት አለባቸው። ሃይማኖታዊ አክራሪነት፣ አሁን ያለውን ዘር ተኰር መከፋፈል የበለጠ ያከብዳል፤ ሁላችንን ሊያጠፋ የሚችል ትልቅ አደጋ በፊታችን አለ። እነዚህ ሁለት ቤተ ሃይማኖቶች፣ በብዙ የአካል፣ የመንፈስና የስሜት ስብራት ውስጥ ላለው ሕዝባችን ዐደራ አለባቸው። ሁለታችንም ቤተ ሃይማኖቶች የግልና የጋራ ንስሓ ያስፈልገናል።
“ሕዝብህ በአንተ ሐሤት ያደርግ ዘንድ፣ መልሰህ ሕያዋን አታደርገንምን? እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አሳየን፤ ማዳንህን ለግሰን።” (መዝሙር 85፥6-7)
አሜን!
Share this article:
A persecuted Reformed pastor in China champions religious freedom and explains the necessity of faithful disobedience.
በፍቅር የተጋመዱ ጥንዶች ትሥሥራቸውን አስመልክቶ ጥያቄዎችን ማንሣታቸው አይቀርም። አንዳንዱ ጥያቄ የሚሰነዘረው ለአፍቃሪው ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ መልስ ከተፈቃሪው ይሻል። ከሚነሡት ጥያቄዎች መካከል አንደኛው “የፍቅር ጥያቄ” ነው። ራሳችንን፣ “በርግጥ አፈቅራታለሁኝ?”፣ “እሷስ ከልቧ ታፈቅረኛለች?” እንላለን። መነሾው ቢለያይም፣ በደስታ መኻል ስንቅር የሚል ጥያቄ እንደ መሆኑ ያስጠላል፤ ያስፈራልም። ሲ. ኤስ. ሊዊስም፣ “ፍቅር በሕይወታችን ካለ ጽኑና ቀጣይ ደስታ ከዐሥሩ የዘጠኙን እጅ ድርሻ ይወስዳል” እንደ ማለቱ ጥያቄው አይናቅም።
በመጻሕፍት ቅኝት ዐምድ፣ ዳዊት ሙራ በቅርቡ ለንባብ በቀረበው የጆንሰን እጅጉ መጽሐፍ ላይ የሚከተለውን ዳሰሳ አድርጓል።
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.
2 comments
ውዱ የተባረክህ ወንድማችን ዶ/ር ግርማ የሚያደምጥ ጆሮ ላለው፤ ማሰብ ለሚወድ አእምሮ፤ ማስተዋል ለሚፈልግ ልብ እጅግ ጠቃሚ ምክርን ሰጥተኸናል። በጣም እናመሰግናለን። ጌታ አምላክ በሕይወትህና በአገልግሎትህ አብዝቶ ይባርክህ። ጸጋና ሰላም ይብዛልህ!
– ለእኛም ልቦና ይስጠን – ምሕረቱን ያብዛልን።
አሜን።
አሜን! ውድ ወንድሜ አሜክስ፣ እግዚአብሔር ይባርክህ። ልዑል እግዚአብሔር ያድሰን፤ ምድራችንንም በሉዓላዊነቱ ያሳርፍ። በጸሎትህ አስበኝ።