[the_ad_group id=”107″]

የጠያራ እገዳ ስለመጠየቅ

መንግሥትና ክፉ ተጠቃሚዎች የሚያበሩት ጠያራ የበረር እገዳ እንዲደረግበት ስለመጠየቅ!

በቅርቡ በመገናኛ ብዙኀን የደረሰን ማሳሰቢያ እንዲህ ይላል፦ “የቦይንግ 737 የቡሾፍቱው አደጋ በሙሉ ቁመናው በውበት ያለ የሰው ልጅ በስድስት ደቂቃ የማንነቱ ደብዛ ጠፍቶ የአንድ ፌስታል የዐፈር ልውስ እንደሚሆን ያስተምረናል፤ እባካችሁ አደብ ገዝተን እርስ በርስ እንቻቻል።” ልክ ነው፤ እናድብ! አደጋው ብሔራዊ ብቻ ሳይሆን፣ ዓለም አቀፋዊ የልብ ስብራት ማስከተሉና በቀላል የማይረሳ አሰቃቂ መሆኑ ምንም አያጠያይቅም። ይሁን እንጂ ትምህርት ሳንወስድባቸው ያለፍናቸው አእላፋት ድርጊቶች ያሉን ሕዝቦች በመሆናችን በርግጥ የተባለውን ትምህርት ከዚህ እንወስድበታለን ወይ? ብዬ ለመጠየቅ እገደዳለሁ።

በመጀመሪያ ደረጃ፤ ሌሎች አገሮች ከዚህ አደጋ በመነሣት የወሰዱት ፈጣን ትምህርትና ርምጃ ምንድን ነው? ተሳፋሪዎች ሁሉ ሟቾች እንደ ሆኑ ማሳሰብ ሳይሆን፣ አስቸኳይ ትምህርታቸው አንድና አንድ ብቻ ነው! ይህ አውሮፕላን (ጠያራ) ከማድረስ ይልቅ በየስፍራው መከስከስ ስላበዛ ብቸኛው መፍትሔ ከመሬት እንዳይነሣ ማድረግ ነው! እንደውም አንዳንድ አገሮች አውሮፕላኑን የሸጡላቸውን አገሮች ለመክሰስ እየተዛጋጁ ነው።

እኔ በቅርቡ ዓመታት ኢትዮጵያን ለተደጋጋሚ መከስከስ የዳረጋት ሌላ ከይሲ ጠያራ ከበረራ እንዲታገድ፣ ከዚህም በፊት እንደጠየቅሁት ሁሉ አሁንም ከሚሊዮኖች ጋር ሆኜ በምሬትና በመንገፍገፍ ይታገድልን ብዬ እጠይቃለሁ!

በአሁኑ ሰዓት በየጥጋጥጉ ኢትዮጵያን እንደ አገር እየከሰከሳት ያለ በረራ “የብሔር ፌደራሊዝም” የተባለው ከይሲ ጠያራ ነው። በሱማሌ ክልል በርካታ የኦሮሞ ብሔረ ሰብ ይዞ ሲበርር ተከስክሷል፤ በአዲስ አበባም ዙሪያ በለገጣፎ አካባቢ በርካታ ነዋሪዎችን ከስክሶ አሁንም በሌሎች የከተማው አካባቢ በረራ ላይ ይገኛል። ከዚህ በፊት በቤንሻንጕል ጉሙዝ ክልል በርካታ አማራዎችን ይዞ ሲበርር በመከስከሱ፣ የፈሰሰው እንባ በአካባቢው የግፍ ፍሬ ያበቅላል ተብሎ ያሰጋል። ይህ ጠያራ በቅርቡ በደቡብ ብሔር ብሔረ ሰቦች በርካታ የጌዲኦ ሕዝብ ይዞ ተከስክሷል። በአደጋው የተጠቁትን ሕዝቦች ዐፈር ለብሰው ማየት እንጀራ ቆርሶ መጎረስ ግፍ እንዲመስለን ሁሉ እያደረገን ነው።

አየር መንገዱ ግን እስከ አሁን ድረስ በረራውን ባለማገድ በየአካባቢው ያሉ ተሳፋሪዎችን ጭኖ እንዲበርር እያደረገ ነው። ይሁን እንጂ ይህ ጠያራ በበረረባቸው አገሮች በሙሉ የከሰክከሳቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ነፍሳት ከሞት ባሻገር ካሉት ሁለት ዓለማት “ትውልድ ይዳን በእኛ ይብቃ” እያሉ እየጮኹ ነው። የዚህ በረራ ባለቤት የሆነ የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ በረራውን ደጋፊ ሕዝብ 150 ሰው ሳይሆን 100 ሚሊዮን ሰው በፌስታል ሳይገባ ባስቸኳይ የብሔር ፓለቲካ/ፌደራሊዝም የተባለውን ጢያራ በአየር እንዳይበርር፣ በምድርም እንዳይሸከረከር የእገዳ አዋጅ እንዲያወጣልን፣ ከተቻለም በየመድረሻችን የሚያደርሰን ጠያራ እንዲያዘጋጅልን፣ በመፍራትና በመርበድበድ በተደጋጋሚ መከስከስ የተጎዳን ሕዝቦች እንጠይቃለን!

ማንንም ሕዝብ በሰላም አድርሶ የማያውቀው – የብሔር ፌደራሊዝም ከበረራ ይታገድ!

“ቤተ ክርስቲያን ለአእምሮ ሕሙማን ምቹ ቦታ ናት ብሎ ለመናገር አያስደፍርም”

እውቁ የሥነ አእምሮ ሐኪምና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አታላይ ዓለም አሳሳቢነቱ ጨምሯል ስለሚባለው የአእምሮ ሕመም ከሕንጸት መጽሔት ጋር ቆይታ አድርገዋል። በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን አባል የሆኑት ፕሮፌሰር አታላይ፣ ችግሩን በተመለከተ በወንጌላውያን አማኞች መካከል ስላለው የአመለካከት ክፍተትና ሊደረጉ ስለሚገባቸው ርምጃዎች ሚክያስ በላይ እንደሚከተለው አነጋግሯቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ

ፖሊካርፕ ያኔ፣ ፖሊካርፕ ዛሬ

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን፣ የምሥራቅም የኦሪየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት፣ እንዲሁም የአንግሊካን እና የሉተራን አብያተ ክርስቲያናት በአንድ ድምጽ ”ቅዱስ” ሲሉ የሰየሙት ሰው ነው− ቅዱስ ፖሊካርፕ።

ተጨማሪ ያንብቡ

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.