
ዓለም በ2007 እንዴት አለፈች?
የተለያዩ ክስተቶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በማያያዝ፣ “በዚህ ጊዜ ጌታ ሊመጣ ነው፤ የዓለም መጨረሻ ሊሆን ነው” የሚሉ ግምቶች ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ለመኖራቸው ታሪክ እማኝ ነው።
[the_ad_group id=”107″]
የእምነትን አመለካከት በሁለት አቅጣጫ ዐጠር ባለ ሁኔታ እንመልከት። ይህም አንደኛ፤ እምነትን ለግል ኑሮ የምንጠቀምበት አግባብና፣ ሁለተኛ እምነትን ለመንግሥቱ የምንጠቀምበት አግባብ ነው።
በግል ኑሮ ብዙ ነገር ያስፈልገናል። ስለምንበላውና የምንጠጣው የሚገድደው አባት እንዳለን ክርስቶስ አስተምሮናል። ‘አትጨነቁ፣ ግን አስቀድማችሁ መንግሥቱን ፈልጉ’ ተብለናል። ሰው የሚያስፈልገውን ካገኘ ምኞቱ ደግሞ ያስቸግረዋል። መቼም ቢሆን አንጠግብም። የብልፅግና ወንጌል ብዙ ተቀባይነት ያገኘው ለሥጋችን ስለሚመች ነው። በዚህም መንገድ ስንሄድ ሩጫችን ከዓለም አይለይም። ልዩነቱ፣ ዓለም በራስ ጥረት ፍላጎትንና ምኞትን ለማሳካት ሲሮጥ፣ እኛ ደግሞ እግዚአብሔር እንዲሮጥልን በእምነት እናዝዘዋለን። የሚገርመው ምንም ያህል ብንበለፅግ፣ ከንጉሥ ሰሎሞን የበለጠ አይሳካልንም። ንጉሥ ሰሎሞን በኑሮ ስኬት ጫፍ ሲደርስ፣ ሁሉንም ከንቱ ብሎ ደመደመ። መጨረሻው ከንቱ ለሆነ ነገር እምነትን መጠቀም አስተዋይ አለመሆንን ያሳያል።
መጨረሻው ከንቱ ለሆነ ነገር እምነትን መጠቀም አስተዋይ አለመሆንን ያሳያል።
መፍትሔው በግል ኑሮ ላይ እምነትን፣ ነጻነት እንድናገኝበት መጠቀም ነው። ልባችን በክርስቶስ ፍቅር ሲነካና እርሱን ስናውቅ ከምድር ለመላቀቅ አቅም እናገኛለን። ያኔ በመሕልየ መሓልይ ውስጥ እንደምትገኘው ሱናማይቱ ሴት፣ “በአፉ መሳም ይሳመኝ፤ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና” እንላለን። እንደ ዳዊት ፍቅሩ ከሕይወት ተሽሎ ሲበልጥብን፣ ያኔ በእውነት አርነት የወጣን ነን። እግዚአብሔር ስለሚያደርግልን ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ስለ ሆነ በማንነቱ እንወድደዋለን። ለምንጠይቀው ጥያቄ እግዚአብሔር ‘እንቢ’ ሲለን በጸጋ ተቀብለን ፍቅራችንን አንነሳውም። እዚህ ላይ እምነት የምንፈልገውን የምናገኝበት መንገድ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ለሚፈልግልን ነገር ‘ዕሺ’ እንድንል የሚያስችል አቅም ነው። ያኔ የምንመላለሰው በእምነት እንጂ፣ በማየት አይደለም በማለት ቃሉን እንኖረዋለን። የሚታየው ነገር አያሰናክለንም። ይልቁንም የእግዚአብሔር መንግሥት ስለ መብልና መጠጥ ሳይሆን፣ በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ደስታ መሆኑ ርግጥ ገብቶን ሕይወቱን እናጣጥመዋለን።
እምነት የምንፈልገውን የምናገኝበት መንገድ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ለሚፈልግልን ነገር ‘ዕሺ’ እንድንል የሚያስችል አቅም ነው።
በለስም ባታፈራ፣ ምድር ብትነዋወጥ፣ ከሁኔታዎች ውጭ በሆነ ዐውድ እኛ ግን በእግዚአብሔር ደስ የሚለን እምነት ነጻ ሲያወጣን ነው። እምነት እኛን ነጻ የሚያወጣው እግዚአብሔርን ነጻ ስናደርገው ነው። እርሱ ያለው ይሁን በማለት ለፍቃዱ በመገዛት፣ ልባችን በጊዜውም ያለጊዜውም እርሱን ማምለክ ሲሆንለት እምነታችን በሥራ ታየ ማለት ነው። ያኔ እምነት ነጻ አወጣን ማለት ነው።
እግዚአብሔር በሰማያዊ ስፍራ አስቀምጦናል። በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ባርኮናል። ሕይወት እንዲሆንልን ብቻ ሳይሆን፣ እንዲበዛልን መጥቶልናል። ለዓለም ብርሃንና ጨው እንድንሆን ጸጋ ተለቅቆልናል። የመንግሥቱ አምባሳደር እንድንሆን ተሹመናል። ፍሬ እንድናፈራ፣ ፍሬያችን እንዲኖር ተቀብተናል። ከክርስቶስ ጋር ወራሾች ሆነናል። የእግዚአብሔር ልጅነት ሥልጣን ተሰጥቶናል። ለሌሎች የምስራቹን እንድንሰብክ ተልከናል። በስሙ እንድንፈውስና አጋንንትን እንድናስወጣ ኀይል ተቀብለናል። እምነት እነዚህ ታላላቅ እውነቶችን ማወቅ ብቻ ሳይሆን፣ በሕይወታችን እንድንገልጣቸው የሚያስችል ነው። እኛ እምነትን ታች አውርደን ለብልፅግና አውለነው ስንባክን፣ እያመለጠን ያለውን ታላቅ ሕይወት ልብ እንበል። እምነትን ተጠቅመን እግዚአብሔርን ለማዘዝ ላይ ታች ስንል፣ እግዚአብሔር ያከናወነውን ማጣጣም ተሳነን። ለሥጋ ሞተን ለመንግሥቱ በትንሣኤ ተነሥተን የምንኖረውን ክብር አጣን። ራሳችንን ክደን እርሱን በመከተል የምንለማመደውን ተአምራዊ የመንግሥቱ ሕይወትን አስቀረ።
እምነትን ተጠቅመን እግዚአብሔርን ለማዘዝ ላይ ታች ስንል፣ እግዚአብሔር ያከናወነውን ማጣጣም ተሳነን።
መንፈስ ቅዱስ በሥራ ላይ ነው። እኛ ግን እምነትን ለእንጀራና ቍሳዊ ለሆነ ነገር ብቻ ወስነን አራከስነው። መከሩን ችላ አልን። ታላቅ የወንጌል አርበኛ መሆናችንን የሚያስቀርብን አለማመን ነው። ክርስቶስ እምነት ቢኖረን ይህን ተራራ ተነቅለህ ወደ ባሕር ሂድ ብንለው ይሆናል ያለን ለምክንያት ነው። ልባችን መንግሥቱ ላይ ከሆነ፣ የሚያቈመን ነገር አለማመናችን ብቻ ነው። መንፈስ ቅዱስ ቈሞ እየጠራን ነው። ጌታ ለራሳችን ብቻ ሳይሆን፣ ከራሳችን ተርፈን ለብዙዎች እንድንተርፍ የሚያድርግ አጀንዳ አለው። ዛሬም ቢሆን ብርና ወርቅ ባይኖረንም፣ ሽባን ከመተርተር አያስቈመንም። ድንቅና ተኣምራት ብርቅ የሆነው እግዚአብሔር ተቀይሮ ወይም አርጅቶ ሳይሆን፣ የእኛ አለማመን ነው።
እየሆነ ባለው የእኛ ስንፍና ምክንያት ግን፣ ሰይጣን ድምፁን ከፍ አድርጎ በእግዚአብሔር ላይ እየዋሸ ነው።
እምነትን መቼ አወቅን? ጌታ የሚያስተምረውን የእምነት አመለካከት ጥለን፣ እኛ የራሳችን የእምነት አመለካከት ፈጠርን። ይህንም በማድረጋችን ከፍቅርና ከሕይወት ጎደልን። ደግሞም ሌሎች በጨለማና በእስራት ሆነው ከእግዚአብሔር ተለይተው ሲጠፉ የሚደርስላቸውን አሳጣን። እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ነው፤ ኀይሉም ታላቅ ነው። እየሆነ ባለው የእኛ ስንፍና ምክንያት ግን፣ ሰይጣን ድምፁን ከፍ አድርጎ በእግዚአብሔር ላይ እየዋሸ ነው።
የእግዚአብሔር ታላቅነት እንዲወጣ፣ ክብሩም ምድርን እንዲሞላ፣ የቅራቅንቦ እምነትን ከራሳችን ላይ አራግፈን ጥለን እምነትን ከመንፈስ ቅዱስ እንቀበልና እንነሣ። የመጨረሻው ጊዜ ላይ ነን። ኢየሱስ ሊመጣ በደጅ ነው። ታዲያ ጌታ ዳግም ሲመጣ “እምነት አገኝ ይሆን?” ያለውን እናስብ።
Share this article:
የተለያዩ ክስተቶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በማያያዝ፣ “በዚህ ጊዜ ጌታ ሊመጣ ነው፤ የዓለም መጨረሻ ሊሆን ነው” የሚሉ ግምቶች ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ለመኖራቸው ታሪክ እማኝ ነው።
In this brief testimony and reflection, Melak Hailu shares his experience of COVID-19 after his wife was tested positive.
አገራችን ኢትዮጵያ በለውጥ ሂደት ላይ እንዳለች በብዙዎች ዘንድ መግባባት አለ። የተጀመረው ለውጥ የሚፈለገው ቦታ ላይ እንዲደርስ ሁሉንም የኅበረተ ሰብ ክፍል ማሳተፍ እንደሚያስፈልግ አሁንም በብዙዎች ዘንድ እምነት አለ። የወንጌላውያን አማኞች የኅብረተ ሰቡ አካል እንደመሆናችን ለአገራችን ሰላም፣ ፍትሕ እንዲሁም ብልጽግና የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። እስከ አሁን በነበረን አገራዊ ተሳትፎ ‘ብዙ ትኩረት አልሰጣችሁም’ ተብለን የምንወቀሰው እኛ ወንጌላውያን፣ ለዚህ ወቀሳ አዎንታዊ ምላሽ የምንሰጥበት ጊዜ ላይ እንዳለን ይሰማናል።
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.
Add comment