[the_ad_group id=”107″]

እሣቱ በጭስ እንዳይታፈን

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ዕድገት የብዙ ነገሮች ድምር ውጤት ነው፡፡ ወንጌላዊቷ ቤተ ክርስቲያን ስትተከል፣ ስታብብና ስትጎመራ፣ ፍሬም ማፍራት ስትጀምር የዕርሻው ባለ ቤት እግዚአብሔር አብሯት ነበር፡፡ ከታየው ዕድገት ጀርባ የቤተ ክርስቲያን ራስ የሆነው ጌታ ክርስቶስ በሰጣቸው ጸጋ ብዙ የደከሙ ታማኝ አገልጋዮቹ ነበሩ፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን እዚህ እንድትደርስ ማዕረግ ያላቸውም ይሁኑ፣ ስም ያልወጣላቸው፣ ታሪክ የዘከራቸውም ይሁኑ እርሱ አንድዬ ብቻ የተመለከታቸው ብዙ የወንጌል አማኞች አሉ፡፡ እነሱ የከፈሉት ዋጋ በላይ በሰማይ፣ በከበረው መዝገብ ሰፍሯል፡፡ በዚህ ሁሉ ግን የመንግሥቱ ንጉሥ፣ የቤቱ ጌታ፣ የሥራው አለቃ እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን!

ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለዓለም አቀፋዊቷ ቤተ ክርስቲያን ዕድገት ጉልሕ ድርሻ እየተወጡ ናቸው ከሚባሉ ምክንያቶች መካከል፣ ከሃያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ የተቀጣጠለው የጴንጤቆስጤ እንቅስቃሴ እና እሱን ተከትሎ የተጀመረው የካሪዝማቲክ ክርስትና ንቅናቄ አንዱ መሆኑን የቤተ ክርስቲያንን ዕድገት የሚያጠኑ ይስማሙበታል፡፡ ይኸው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ብዙ ርቀት እንድትጓዝ አድርጓታል፡፡ ለዚህ የድል ጕዞ አሁንም ክብሩ ለእግዚአብሔር ይሁን!

ይህ የሕንጸት ልዩ ዕትም በዋናነት በመንፈስ ቅዱስ እና ሥራዎቹ ላይ እንዲያተኩር ተደርጓል፡፡ የዚህ ዝግጅት ዋና ዐላማ፣ ባለፉት ዘመናት በምድራችን ላይ ባለችው ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ለተሠራው የወንጌል ሥራ ዕውቅና መስጠት ሲሆን፣ እግረ መንገዱንም በመንፈስ ቅዱስ ስም በሚደረጉ ሕፀፆች የክርስቶስ ወንጌል ሥራ ሳይደናቀፍ እንዲቀጥል ለማሳሰብ ጨምር ነው፡፡

ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር ከእውነተኛው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጋር አብሮ ተሰላፊ ነው፡፡ የአገልግሎት ማኅበራችን መንፈስ ቅዱስ በምድሪቱ ላይ ለሚሠራቸው ሥራዎች ዕውቅና ከመስጠት ባለፈ እውነተኛው ከሐሰተኛው ተለይቶ እንዲታይ ያለ መታከት ይሠራል፡፡ በታሪክ እንደተመሰከረው መንፈስ ቅዱስ በግብሩ ከቃሉ ጋር አይጣረስም፡፡ ሐዋርያት ሁሉን መርምረንና ፈትነን እንድንይዝ ከሰጡት ምክር ጀርባ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ እንዳለ የተገለጠ ነው፤ ቅዱሳት መጻሕፍት ሰዎች በቅዱሱ መንፈስ ተነድተው የጻፉት ነው የሚለው ከእምነት አንቀጾቻችን መካከል ነውና፡፡ ልንታዘዝ የሚገባን የተጻፈውን ሕያው ቃል እንጂ ልምምዳችንን አይደለም፡፡ ስለሆነም የሚደረገውን ልንፈትን፣ በቃሉም ልንመረምር ስንጀምር የቁጣ ድምፃቸውን የሚያሰሙት ክፉ ሥራቸው እንዳይገለጥ የሚፈልጉቱ እንደሆኑ ይገባናል፡፡ እውነተኞቹ የጌታ ደቀ መዛሙርት በዚህ ቅር የሚሰኙ አይደሉምና፡፡ ሕንጸት ቀድሞም፣ አሁንም፣ ወደ ፊትም የመንፈስ ቅዱስ ሥራ አክባሪ፣ ተካፋይ እና ጠባቂ አገልገሎት መሆኑን ገልጽ በሆነ ቋንቋ ማስቀመጥ እንፈልጋለን!

በምድራችን ላይ የተቀጣጠለው የመንፈስ እሣት እንዳይዳፈን ሁላችንም ልንወጣው የሚገባ ኀላፊነት አለ፡፡ እሣቱ በጭስ እንዳይታፈን ንጽሕ አየር እንስጠው፤ ወደ እሣት የተወረወረ ሁሉ አይነድምና ትክክለኛውን ማገዶ እንለይ፡፡ ያን ጊዜ የእሳቱን ኀይል፣ የሚሰጠውንም ሙቀት በጋራ እንካፈላለን፡፡

የሴራ አስተሳሰብ የጠፈረን እኛ!

አገራችን አሁን ያለችበትን ፖለቲካዊ ኹኔታ አስጊ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ የሴራ ትርክት በአየሩ ላይ መናኘቱ እንደ ሆነ ይህ የሰሎሞን ጥላሁን ጽሑፍ እያሳሰበ ተጨባጭ ምክንያታዎነት መድረኩን እንዲረከበ ጥሪ ያደርጋል።

ተጨማሪ ያንብቡ

ወርኀ ጽጌ ወስደት

“ወርኀ ጽጌ ወስደት” የተሰኘው ይህ ጽሑፍ፣ በወንጌላውያኑ ዘንድ ብዙ ትኩረት ስለማይሰጠውና ጌታ ኢየሱስ በሕጻንነቱ ወራት ከእናቱ ማርያምና ከዮሴፍ ጋር ወደ ግብፅ የተሰደደበትን ታሪክ መነሻ በማድረግ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሁነቱ ያለውን ትርክት ያስቃኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.