[the_ad_group id=”107″]

እግዚአብሔር - አለ!

የንጹሐን ደም በግፍና በጭከና እየፈሰሰ፣ የፍርሀትና የስጋት ጽልመት አገራችንን በሸፈነበት በዚህ ወቅት፣ ለፍትሕ የምናሰማው ጩኸት እንዳለ ሆኖ፣ እግዚአብሔር ዓለማትን በፈጠረበትና ደግፎ በያዘበት በዚያው የሥልጣኑ ቃል፣ አገራችንን በፍጹም ሉዓላዊነት ደግፎ እንደያዘ ልብ ልንል ይገባል። እርሱ ትላንትናን፣ ዛሬና ነገን በአንድ ጊዜ በእጁ የያዘ አምላክ ነው። ነገሥታት ነገን አያውቁም፤ ከሊቆችም የተሰወረ ነው። በርግጠኝነት የምናውቀው ግን፣ የእግዚአብሔርን ሁሉን ዐዋቂነት፣ ሁሉን ገዢነት፣ ቻይነትና ታማኝነት ነው። ፍርሀታችን፣ ጥያቄያችን፣ ስጋታችንና ተጋዳሮቶቻችን በሙሉ በእርሱ ዘንድ የታወቁ ናቸው። የአንዲቷም ሰኮንድ ኹነት (event) ከእርሱ ልትሰወር አትችልም።

የሰላም መረበሽና የፍትሕ ቀውስ እየከረረ በመጣበት በዚህ ዘመን፣ እንደ ክርስቲያን ተስፋ የምናደርገው የታሪክን አቅጣጫ በልጓም የያዘውን ልዑል እግዚአብሔርን ነው። ከእርሱ የፍትሕ ዐይኖች የሚሰወር ምንም ነገር የለም። እግዚአብሔር ከአቤል ዘመን ጀምሮ የንጹሐንን ደም ሲያፈስሱ ከነበሩት ግፈኞች ይልቅ እጅግ ብርቱ አምላክ ነው፤ ከዙፋኑ ፍርድ ይሰጣል። በገዛ ወንድሙ ከተገደለው ከአቤል ጀምሮ፣ በቅርቡ ዲያቢሎሳዊ በሆነ ጭከና እስከ ተገደሉት ወገኖቻች ድረስ የፈሰሰው የንጹሐን ደም በከንቱ አይቀርም። የቱንም ያህል ቢጨልም፣ አገራችን በልዑል እግዚአብሔር እጅ እንጂ፣ በግፈኞች እጅ አይደለችም።

ኢዮሣፍጥ በሁሉ አቅጣጫ ጦርነት በታወጀበትና ግራ በተጋባበት ጊዜ፦ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በሰማይ የምትኖር አምላክ አይደለህምን? የምድር ሕዝቦችን መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ ነህ፤ ኀይልና ሥልጣን በእጅህ ነው፤ ሊቋቋምህም የሚችል ማንም የለም።” በማለት ጸለየ (2 ዜና 20፥6)።

ወገኖቼ – እግዚአብሔር – አለ! አዎን አለ! ምንም እንኳን ከተከበበት የስጋት ጽልመት መውጫውን ባያውቅም፣ በእግዚአብሔር ሉዓላዊነትም በመደገፍ፣ ኢዮሣፍጥ እንዲህ አለ፦ “የመጣብንን ይህን ታላቅ ሰራዊት እንቋቋም ዘንድ አቅም የለንምና የምናደርገውን አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወዳንተ ናቸው . . .” (2 ዜና 20፥12)።

እግዚአብሔርን ፈለገ፤ ተገኘለትም። “ሰልፉ የእኔ ነው፣ የማደርገውን ማዳን ተመልከት አለው።” ሁሉን ቻዩ ልዑል እንደተናገረው፣ ድብቅ ጦርን አስነሣ፤ ምድሪቱም አረፈች፤ በዙሪያው ካለው ስጋት ሁሉ አሳረፈው!

ለአገራችንም እንዲሁ ይሁንልን። አሜን!

ሊላሽቅ የሚገባው የኢትዮጵያውያን ልቅ ጀብዱ

የታሪክ አጥኚው አፈወርቅ ኀይሉ (ዶ/ር) በዚህ ጽሑፉ፣ ኢትዮጵያዊነት “ጨዋነት” ብቻ አለመሆኑን፤ ይልቁን ጸያፍ የሆነ “የጀብደኝነት” አመለካከት ከማንነታችን ጋር የተጋባ መሆኑን ከታሪካችንና ከአሁኑ ሁናቴ ጋር ያዛምደዋል። “ልቅ” የተባለው ይህ “ጀብደኝነት” በቶሎ ካልላሸቀ ያጠፋናል ይላል ዶ/ር አፈወርቅ።

ተጨማሪ ያንብቡ

እምነት፡- ስጦታ ወይስ ችሎታ?

ብናስተውለውም ባናስተውለም እያንዳንዳችን ለየዕለቱ ኑሯችን እምነት ያስፈልገናል፡፡ የዚህን የእምነት ዐይነት በምሳሌ ለማስረዳታ ያኽል፣ የምንቀመጥባቸው ወንበሮች ክብደታችንን መሸከም መቻላቸውን አምነን መቀመጣችን ከሞላ ጎደል ማሳያ ነው፡፡ የዚህ እምነት መሠረቱ ወይም ድጋፉ የቀድሞ ልምምዳችን ሊሆን ይችላል፡፡ ለተለምዷዊ ሕይወት የሚሆነው እምነት መገኛው ልምምዳችን ቢሆንም፣ የማመን ዐቅም ግን በውስጣችን ሳይኖር አይቀርም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

Add comment

Your email address will not be published.

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.