[the_ad_group id=”107″]

የምፀት ምድር

ከእስክንድሪያ ከተማ በቅዱስ አትናቴዎስ የተሾሙት የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጳጳስ አባ ፍሬምናጦስ (ከሳቴ ብርሃን ሰላማ) ጀምሮ ያለውን የታሪክ መገንጠያ ካሰብን፣ ክርስትና አገራችን ከገባ ወደ 1700 ዓመታት ሊያስቆጥር ነው! ሆኖም ዘረኝነትን መሠረት ያደረገ የክፍፍል ጽልመት ያጠላበት አገራችን፣አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፣ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፣ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” (ገላ 328) የሚለው የወንጌል ቃል፣ ያልነገሰባት ምድር ናት። ምናልባት፣የተሻለ ቃልና መገለጥአለኝ በማለት የሚመጻደቀው የፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ዘንድ ይሻል ይሆናል ብዬ እንዳላሰብ፣ እዚያ ቤተ ያለው ፈርጀ ብዙ የቀውስ ጡዘት፣ የነብዪ ኤርምያስን (የመጽሐፍ ቅዱሱን ማለቴ ነው!) ድብልቅ ስሜት ያስታውሰኛል፦እኔም የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ በእውነት ድሆችና ሰነፎች ናቸው፤ ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ እናገራቸውማለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና አልሁ። እነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፣ እስራቱንም ቈርጠዋል።” (ኤር. 54-5)

አድዋ የኢትዮጵያዊ ማንነታችንና የአንድነታችን መለያ አንዱ ምልክት ብቻ ሳይሆን፣ የመላው ጥቁር ሕዝብ ኩራት የነጻነት ተምሳሌት በመሆኑ 123 ዓመታት ዘክርናል። የቅኝ ግዛትን ባረነትን አሻፈረኝ ብለን፣ የዘረኝንት፣ የቂምና የጥላቻ ባሪያዎች ሆነናል! በታሪካችን ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር የለንም፤ በደም የተለወሰ እንጂ። አገራችን፣ አረንጓዴ፣ የብዙ ከረስ ምድር ባለሀብት፣ ወርቃማ የአየር ንብረት፣ አኩሪና እንግዳ ተቀባይ ናት በማለት እንሞግታለን። እውነትም ነው። ሆኖም አስከፊ ድኽነት ይሳለቅብናል፤ በየባዕድ ምድሩ ያንከራትተናል። በመልካም አስተዳደር እጦት፣ የፍትሕ ረገጣ የተደራጀ አገር ዘረፋ፣ በገዛ አገር ስደተኝነት አስከፊ ከሚባሉት አገሮች አንዷ አገራችን ናት። የብዙ ሺህ ዓመታት አኩሪ የነጻነት ታሪክ ያላት፣ አምላክበልዩ ዐይኑየሚያያትና የሚሳሳላት፣ በማለት እንዘክራላታለን፤ ይሁን እንጂየቸሩ እግዚአብሔር ምድር ናትባለንባት በዚህችው ምድር፣ ሰው ከዘሩ ብቻ የተንሳ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሮ የሚፈናቀልባት የበዙ ምፀት ምድር ሆናለች፤ ከራሷ የተጣላች!

በዓለም አቀፍ ሽብረተኝነትየተፈረጁ ፓርቲዎች/መሪዎች፣ በምሕረት የተቀበለች አገር፤ በከፊል ከእነዚሁ መካከል በተነሱ ጽንፈኞ የምትታመስ አገርግራ ያጋባን የነጻነት ተቃርኖ! ሕልም የነበረብን የማሰብና የመናገር ነጻነት፣ አሁን ሌሎችን በቃላት የምንገድልበት መሣሪያ ሆኖብናል። ይህም ምፀት ነው! ስለ ፍትሕና የጽድቅ መሪ ጮኸን አለቀሰን፤ / ዐቢይ መጣ፤ ከእግዚአብሔር የተላከ ሙሴ ነው አለን (ክርስቲያኑም ሙስሊሙም!) ሆኖም ገና ሳይነጋ በዚያው አንደበት፣ ዐይንህን ለአፈር ለማለት ቸኮልን። በፌደራልና ክልላዊ አስተዳደር መካከል ሊኖረው የሚገባው ጤናማ፣ ተአማኒነትና ተደጋጋፊት ያለው የኀያል ሚዛን፣ብቻዬን፤ ወይምየእኔ ብቻየሚል ንፉግነት በተናወጠው የዘር ፖለቲካ ተናግታል።

በሕዝበ ክርስቲያኑ መካከል የሚታየው የአመራር፣ አስተምህሮአዊና ሞራላዊ ቀውሶች፣ የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮና መልእክት ቅቡልነትና ተኣማኒነት ጥያቄ ውስጥ ከተዋል። ልቡ በአንደበቱ ላይ የሚፈርድበትና ምግባር አልቦ የሆነየስም ወንጌላዊነትንባሕርዩ ያደረገ ትውልድ እያፈራን ይሆን? መሠረታዊ የሆኑ ክርስቲያናዊ እሴቶች ወይም ፋይዳዎች እየተፋለሱ የመንግሥትን ዳኝነት የጠየቁ የመብት ሙግቶች ለእርስ በእርስ መወጋገድ ዳርገውናል፤ ጦርነቱ ከጠላት ጋር መሆኑን ረስተን እርስ በእርስ ተወጋገደናል። ድኅረ ዘመናዊነት ያፈራቸው በጎ ባሕል አፍራሽ ልቅነቶች የወጣቶችን ልብ ሲሰርቁ፣ ቤተ ክርስቲያንተዉ! አያዋጣም! ከሁሉም በላይ እግዚአብሔራዊ አይደለም!” እንዳትል የርስዋም የሞራል መሠረቶች ተዛብተዋል። በአገር ቤትና በዳያስፖራው መካከል ተፎካካሪ የሆኑ አብያተ ክርስቲያናትና አግልግሎቶች በዝተዋል። ትልልቆቹ ለቁጥር፣ ትንንሾቹ ደግሞ ለተኣማኒነት ይታገላሉ። ቁጥር እንጂ ጥራት፣ ቅርጽ እንጂ ይዘት ትኩረት አይደሉም። የተሳሳተ የመጽሐፍ ቅዱስ አፈታታችን፣ ለብዙ ስሁት ትምህርቶች ጋርዶናል። ፈሪሃ እግዚአብሔር በብልጠትና በአምባ ገነናዊ ድፍረት ተተክቷል፤ ዓለምንና ቤተ ክርስቲያንን የሚለዩ የድንበር እሴቶች ደብዛቸው እየጠፋ ነው።

ምናልባት የወንጌል አማኞች ቁጥር ወደ 25% ደርሷል የሚል ግምት አለ። ከአራት ኢትዮጵያዊ አንዱ የወንጌል አማኝ ነው ማለት ነው! በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው መከፋፈል፣ ክብርና ሞግስ እየራቀ ያለው አመራር፣ አገርን እያመሰ ያለው ዘረኘነትና ቅዱሱ መጽሐፍ እንደግድያየሚያየው ወንድምን የመጥላት ኀጢአት፣ የዚህእድገትተቃርኖ ሆኖውብናል! ውጭ ሲዘንብ፣ ወደ ቤት ይሸሻል፣ የቤቱ ጣራ ካፈሰሰ ወደ የት ይኬዳል? ዘረኝነትን ከምስባካችን እንቃወመዋለን፣በሕይወታችን ግን እንኖረዋለን። ስለአንድነት እንሰብካለን፣ እርስ በእርስ እንወጋገዳለን፤ ስለፍቅር እንሰብካለን፣ ጥላቻን አንግሠናል። እርስ በእርስ በተጣረሰ የታሪክ ተቃርኖ ተጠፍረናል!

እውነተኛው አርነት፣ ራስን ከራስ የተቃርኖ እስር ቤት ማስፈታት ነው! በአስጨናቂው ዘረኛ አፓርታይድ መንግሥት በግፍ የተገደለው ስቲቭ ቢኮ እንዳለው፣ ከማኅበራዊና ፓለቲካዊ ጨቋኝ አገዛዝ እስር ቤት ይልቅ፣ የከፋው ትልቁ እስር ቤት የተዛባ የራስ እይታ [mindset] ወይም የአስተሳሰብ ደካማነት ነው። Steve Biko: I Write What I Like: (London, Bowerdean Press, 1978).74ff.

ትልቁ የፈጠጠው ችግር ቤተ ክርስቲያን በተጽእኖ የጽድቅ ተራራ ላይ ከፍ ብላ ያለመታየቷ፣ ጨው፣ ብርሃንና አማራጭ በመሆን፣ ምድራችን ላለችበት ቀውስ የዕርቅ፣ የመቀባበልና የሰላም መንበር የመሆን ዐቅም ማጣቷ ይመስለኛል! ይህ ዐይናችንን፣ በኀፍረት እድንሰብርና ለንስሓ ካላነሣሣን ምን ተስፋ አለ? ጌታ፣ዐይንሽን በዕፍረት አልሰብር ብለሻልእንደ አላት ይሁዳ ሳንሆን አልቀረንም! (ኤር 33) ወገኖች፣ ትውልዱ እንዴት እያየን ይሆን? መጪውስ ትውልድ በምን ያሳታውሰን ይሆን? በእግዚአብሔርም በታሪክም ሚዛን ላይ ተቀምጠናል!

አገራዊ ንስሓ ያስፈልገናል፤ ከልብ የሆነና በፍሬ የሚገለጥ፤ ተሐድሶ ያስፈልገናል፤ ቅዱስ ቃሉን መሠረት ያደረገ! በግል ሕይወት ከሥጋዊነት ወደ መንፈሳዊነት፣ ከወጋዊ ወይም ከልማዳዊ ሃይማኖተኛነት ወደ እውነተኛ ምስክርነት፣ ቃል ብቻ ከሆነ ባዶነት ወደ ክርስቶሳዊ ሥነምግባራዊነት (በተለምዶ የተራራው ስብከት እንደሚባለው ዐይነቱ ማለቴ ነው!) ከጣዕም የለሽነት ወደ ጨውነት ልንታደስ ይገባል። በቤተ ክርስቲያን ደረጃ ደግሞ መንፈሱና የቅዱስ ቃሉ የበላይነት ባይተዋር ከሆነበት ማኅበራዊነት ወደ ክርስቶሳዊ አካልነት መታደስ አለብን። ቤተ ክርስቲያንን ክርስቶሳዊ አካልነትዋን ቸል አስደርጎ፣ ግራ በተጋባ በዚህ ኅብረተሰብ ውስጥ ሊኖራት የሚገባትን አዎንታዊ ተጽእኖ አሳጥቶ፣ እንደ ተራ ማኅበራዊ ስብስብ እንድትሆን ከሚያስገድዳት ልማዳዊነትና ተጽእኖቢስነት አርነት የሚያወጣት ክርስቶሳዊ ተሃድሶ ያስፈልጋታል። ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ የወንጌልን ሀብት ለትውልድ የማውረሻው መንገዱ ይኸው ነውና።

እንደ ዳዊት፦የሠራዊት አምላክ አቤቱ መልሰን፤ ፊትህንም አብራ፤ እኛም እንድናለን።” (መዝ 8019) ብለን ልንጮኽ ይገባል። በርግጥም እንደ ዕንባቆም፦እግዚአብሔር ሆይ ዝናህን ሰምቻለሁበኛም ዘመን አድሳቸው፤ በኛም ዘመን እንዲታወቁ አድርግ።” (ዕንባ 32) በማለት የእግዚአብሔርን የማዳን ኃይል የሚዘክረውን ጸሎት፣ የተሓድሶ ጩኸታችን ልናደርገው ይገባል።

እግዚአብሔር ዘመናችንን፣ አገራችንና የወንጌል ሥራዋን ያድስ፤ ይባርክም!

የአብርሃም እንግዶች እነማናቸው?

እውነተኛ ገጠመኝ ነው። ከኹለት ዐሠርት ዓመታት በፊት ታቦተ ሥላሴ ደባል[1] በኾነበት በአንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለሐምሌ ሥላሴ ክብረ በዓል የተገኙት ምእመናን በቍጥር ጥቂት ነበሩ። ይህን የታዘቡትና በሥልጣን በመናገር የሚታወቁት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በኹኔታው ዐዝነው እንዲህ ብለው ነበር፤ “ምእመናን ዛሬ የሥላሴ በዓል እኮ ነው? ምነው ታዲያ ምእመናኑ ጥቂት ኾኑ? ይህን ጊዜ የገብርኤል በዓል ቢኾን እንኳን ለዓመቱ ለወሩም ብዙ ሕዝብ ይገኝ ነበር፤ ምእመናን ከገብርኤል እኮ ሥላሴ ይበልጣሉ? ስለዚህ ማንን ማምለክ እንዳለብን ማስተዋል ይገባናል።”

ተጨማሪ ያንብቡ

እሣቱ በጭስ እንዳይታፈን

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ዕድገት የብዙ ነገሮች ድምር ውጤት ነው፡፡ ወንጌላዊቷ ቤተ ክርስቲያን ስትተከል፣ ስታብብና ስትጎመራ፣ ፍሬም ማፍራት ስትጀምር የዕርሻው ባለ ቤት እግዚአብሔር አብሯት ነበር፡፡ ከታየው ዕድገት ጀርባ የቤተ ክርስቲያን ራስ የሆነው ጌታ ክርስቶስ በሰጣቸው ጸጋ ብዙ የደከሙ ታማኝ አገልጋዮቹ ነበሩ፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን እዚህ እንድትደርስ ማዕረግ ያላቸውም ይሁኑ፣ ስም ያልወጣላቸው፣ ታሪክ የዘከራቸውም ይሁኑ እርሱ አንድዬ ብቻ የተመለከታቸው ብዙ የወንጌል አማኞች አሉ፡፡ እነሱ የከፈሉት ዋጋ በላይ በሰማይ፣ በከበረው መዝገብ ሰፍሯል፡፡ በዚህ ሁሉ ግን የመንግሥቱ ንጉሥ፣ የቤቱ ጌታ፣ የሥራው አለቃ እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን!

ተጨማሪ ያንብቡ

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.