
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ክብር ነው
አማረ ታቦር፣ “Seeing and Savoring Jesus Christ” ከተሰኘው የመጋቢ ጆን ፓይፐር መጽሐፍ እየቀነጨበ የሚያቀርበውን ንባብ ሦስተኛ ክፍል እዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል። በዚህኛው የትርጉም ክፍል፣ ስለ ጌታችን ኢየሱስ መለኮትነት ሐተታ የተሰጠበት ሲሆን፣ ይህም መለኮታዊ ማንነት በስሞቹ መንጸባረቁን ያስቃኛል።
[the_ad_group id=”107″]
ከተራዛሚ ግጭቶችና ቍርቍሶች ለመውጣት ብዙ አገሮች ድኅረ ግጭት የሰላም ግንባታ ትግሎችን አካሂደዋል፤ እያካሄዱም ይገኛሉ። ማኅበረ ሰብ ፊትና ጀርባ ሆኖ ከቆየባቸው የተራዘሙ ግጭቶች ወጥቶ፣ አንዲትን በራእይ የተጣጣመች አገር መልሶ መገንባት “መደመር” ከሚለው ቃል ጋር ሳይጋጭ፣ ነገር ግን ከዚያ በዘለለ መልኩ በርካታ የሰላም ግንባታ ሒደት ያለበት ውስብስብና ተከታታይ ተግባራትን ይጠይቃል።
ዐመፃን ማቆም የዚህ የሰላም ግንባታው ሒደት የመጀመሪያው ደረጃ ብቻ ነው። ማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ ያተኮሩ ወሳኝ የመንግሥት ሥራዎች መታደሳቸውን (ሥር ነቀል ለውጥን ጨምሮ) ሁሉ ይጠይቃል። እዚህ ውስጥ ደግሞ ቀድሞ ተቃዋሚ የነበሩ ኀይላት ተሳታፊ የሚሆኑበትን መንገድ ሁሉ መቀየስን ያካትታል። በአገራችን ፖለቲካ ቀድሞ ተቃዋሚ የነበሩ ከዚህ ቀጥሎ የሚያስፈጽሙት አጀንዳ ከሌላቸው የኅልውናቸው ዐላማ ነባሩን መንግሥት መጣል ብቻ ነበረ ማለት ነው። ካላቸው ግን፣ ምንድን ነው? መቼና እንዴትስ ነው የምናውቀው?
በግልጽና ስውር የዐመፅ ሽክርክሪት ውስጥ የነበረን ሕዝብ፣ ሥነ ልቡናዊና መዋቅራዊ እንቅፋቶቹን አስወግዶ መምራት፣ በደንብ ሰፋ ያለ ጊዜ ይጠይቃል
በግልጽና ስውር የዐመፅ ሽክርክሪት ውስጥ የነበረን ሕዝብ፣ ሥነ ልቡናዊና መዋቅራዊ እንቅፋቶቹን አስወግዶ መምራት፣ በደንብ ሰፋ ያለ ጊዜ ይጠይቃል። ስለዚህ በዚህ አጭር ጽሑፍ የጥድፊያ ጥያቄ ጠያቂ እንዳልሆንኩ ይታወቅልኝ። በሰላም ግንባታ ሒደት የአንዱን አገር ተሞክሮ አምጥቶ ወደ አንዱ በማድረግ እንዳለ መተግበር አይቻልም፤ ሁሉም የሰላም ግንባታ ከጂኦፖለቲካ፣ ከባሕልና ከታሪክ እንዲሁም ከነባራዊ ሁኔታ አንጻር እንደ ጣቶቻችን አሻራ ሁሉ የተለያየ ነው። ይሁን እንጂ በባለጋራዎች መካከል ያለውን ልዩነት ወደ ሰላም አምጥቶ ድኅረ ግጭት የሰላም ግንባታ የሚያስፈልጋቸውን ማኅበረ ሰቦች ጕዳይ ማስላት፣ ጽንሰ ሐሳቡን መገንዘብ እና የሒደት ቅደም ተከተሎችን እንዲህ ናቸው ብሎ መናገር ይቻላል።
ስለዚህ “መደመር” ተተግብሮ ብትንትኖሹ ወደ ግጥምጥሞሽ ከመጣ በኋላ ወደ ተጣጥሞሽ የሚሻገረው እንዴት ነው? የሚለው ጥያቄ በአሁኑ ወቅት ወሳኝ ነው። በኢትዮጵያ “ድንገቴና መድኅናዊ” ለውጥ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያ የምጥ መርፌ ሆኖ (Inducing Agent) አገሪቱ በዐይነቱ “ቶኪቻው” የሆነ ለውጥ አምጣ እንድትወልድ አድርጓል፤ ይህንንም አማኞች እንደ መግቦተ እግዚአብሔር (Providence of God) ሲያዩት፣ ኢ-አማንያን ደግሞ እንደ ምትሓት እያዩት ነው። ይሁን እንጂ፣ ይህ ለውጥ ከዕድሜው አኳያ ገና እንቡቃቅላ ልጅ ነው። ዕርሻ ልከነው በሬ አይጠምድልንም፤ ሜዳ ሰድደነው ከብት አይጠብቅልንም፤ ከተማ ልከነው አያስተዳድርልንም፤ ውጭ አገር ልከነው አይቦተልክልንም። አሳዳጊ ይጠይቃል፤ ሞግዚት ይፈልጋል።
በሥሥትና በጕጕት የሚታይ ብርቅዬ ለውጥ የመደመር ሒደቱን እንደ አጀማመሩ በፍጥነት ጨርሶ የማባዛት ሒደቱን በፍጥነት መጀመር አለበት። የደኅንነት (የደኅናነት) የማኅበራዊና የፖለቲካ ጕዳዮችን እርስ በርስ መልሶ ለማስተሣሠር ግንኙነታቸው እንዴት ያለ ሊሆን ይገባል? የሰላም ግንባታ ሒደቱስ ምን ዐይነት ነው? ትምምኖች የሚገነቡትስ እንዴት ነው? የሰብአዊ መብት ጥበቃ ዋስትናዎች፣ የፖለቲካ ሥልጣን ሽግግሮች ማኅበራዊ ማንሰራራቶችና ማኅበራዊ ልማቶች እንዴት ይፈጠራሉ? እንዴትስ ይጠናከራሉ? ድኅረ ግጭት የሰላም ግንባታ (Post-conflict peacebuilding) እየተካሔደ ነው ለማለት የምንችለው ምልክታዊ የሆኑ መተቃቀፎች እውን በሆኑ የጉርብትና መከባበሮች በማኅበረ ሰቡ ውስጥ በዘላቂነት ጎልተው መታየት ሲጀምሩ ነው። እንግዲህ ማንኛውንም ግልጽና ስውር ዐመፅ በማኝኛውም ዐይነት መንገድ በቍጥጥር ሥር የሚያውል ሥርዐት መፍጠር፣ ለመከባበር ጕርብትና የማያወላዳ ቀዳሚ መስፈርት ነው። የማኅበራዊ ግንኙነት አቅጣጫ ደኅንነት እስከ ትምምን ካልደረሰ ለሚፈለገው የሰላም ግንባታ ተባባሪ እጅ ማግኘት አይቻልም። መተማመን የለም ማለት ሰላም የለም ማለት ነው። ርግጥ ነው፤ ማኅበራዊ ግጭት ሙሉ በሙሉ አይጠፋም፤ ይሁን እንጂ ጸባኢ (Antagonist) የሆኑ ግጭቶችን በሚመለከት በቂ መልስ መስጠት ተገቢ እና ግድ ነው። የሰላም ግንባታ ጥረት አንዲት አገር የምትውጠው ኪኒን አይደለም፤ የምትጓዝበት ጎዳና እንጂ። ዐመፅን የምንቆጣጠርባቸው ልዩ ልዩ መንገዶችን በመጠቀም ብቻም አይመጣም፤ ሥረ መሠረቱና ሥነ ልቡናዊ ሕማሞቹ መፈወስ አለባቸው። እንግዲህ እዚህ ጋ ነው የፍትሕ ሒደት የሚመጣው። ማኅበረ ሰቦች በተለያየ እውነተኛ በሆኑና ባልሆኑ ትራኬዎች አማካኝነት የደረሰባቸው ወይም ደረሰብን ብለው የሚቆጥሩት (real and/or perceived) በደል አለ። ለዚህ መልስ የሚሆን ስልታዊ የማኅበረ ሰብ ንቃተ ኅሊና ማዳበሪያ በተከታታይ ማድረግና የዚህም ውጤት የሆነ ሊቀር የማይገባ የመዋቅር ለውጥ ካልተከተለ፣ የሰላሟ ርግብ በክንፍ የበረረችውን ያህል፣ በምድር ላይ በእግሯ መቆም የማትችል ትሆናለች። እንግዲህ ተደጋጋሚ ዐመፅን ለማስወገድ፣ የዐመፅን ሥረ መሠረት ማስወገድ አማራጭ የለውም። ይሁን እንጂ በአገር ደረጃ በሰላም ግንባታ ሒደት ውስጥ ጥላቻና አለመተማመን መፍትሔ ከሚያመጡ ውሳኔዎች በኋላም፣ እየደጋገሙ ሊከሰቱ የሚችሉ አሰልቺ ዙረቶች ናቸው። በእንዲህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ተደጋጋሚ ስምምነቶች (Renegotiation) ባለመሰልቸት ሊደረጉ ግድ ነው።ቡድኖች ለገቡት የሰላም ቃል ኪዳን ፈጣን እሺ ባይነት ከማሳየት ይልቅ ስምምነቶች መተግበር ሲጀምሩ የአቋም መንሸራተትና ታማኝነትን ማጉደል ያሳያሉ። ከዚህም አንጻር የሰላም ሒደት ተግብሮት የሚደናቀፈው/የሚዘገየው ከትምምን እጦት የተነሣ ነው። ስለዚህ በቡድኖች መካከል ያለ የጥላቻና የቁጣ ስሜት ርዝራዡ እስካለ ድረስ የሰላም ግንባታው ሒደት ይደናቀፋል ወይም ይጓተታል ብሎ መገመት ተገቢ ነው። እንግዲህ ተጨባጭ የግጭት ምክንያቶችን ለማቃለል ከሚደረገው ጥረት ባሻገር፣የሕዝቦች የግንኙነት ጥገና ጎን ለጎን አብሮ መሥራት የግድ ይላል። ስለዚህ ሕዝብ ማስተዋል ያለበት ነገር የሰላም ስምምነት ተካሂዷልና ነባሩ ግጭት ሙሉ በሙሉ ተወግዷል ማለት እንደማይቻል ነው፤ ምክንያቱም አንዳንዴ የሰላም ግንባታ ሒደቶች በራሳቸው እንኳ ለግጭት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች አይጠፏቸውምና ነው።በተለይ አንዳንድ ስምምነቶች ግትርና አስገዳጅ ሲሆኑ፣ የዳግም ግጭት ክስተት ምክንያት ይሆናሉ። ለስምምነቶች ታማኝ መሆንና ለቀጣይ የሰላም ግንባታ መነሣሣት አገርን ከጠብ መቀራቅር አውጥቶ ወደ ፊት እንድትሄድ ለማድረግ የሚጠቅም ነው፤ ነገር ግን እውነተኛና ከልብ የሆነ ራስን መስጠት (Commitment) ከቡድኖች ሁሉ ይጠበቃል። ይህ የትምምን መፈጠሪያ አንዱ ትልቅ ምልክት ሲሆን፣ ትምምን በሌለበት አገር ሰላም ይኖራል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው! ድኅረ ግጭት የሰላም ግንባታ (Post Conflict Peacebuilding) የሚለው ስያሜ በራሱ አሁን ካለንበት እዚህም እዚያም ካሉ ግጭቶችና ለኋላ መተጋተጊያ ስልት ከሚታዩ እፎይታዎች ሌላ ግጭት መች ቆመና የሰላም ግንባታ/ድኅረ ግጭት እንላለን? የሚሉ አስተያየቶች አሉ አስተያየቶቹም ተገቢ ናቸው።እንዲህ ዐይነት አስተያየቶች ስለ አገባቦች (Interventions) ምንነትና ባሕርያት እንድናነሣ ያስገድዱናል። ግጭትን አስመልክቶ ያሉ አገባቦች ብዙና ዘርዘር ያሉ ቢሆኑም በሦስት ዐምዶች ሊገለጹ ይችላሉ፦ ፩) ግጭት ከመፈጠሩ በፊት ግጭት ጠቋሚ ሁኔታዎችን (Conflict indicators) በመጠቀም የሚደረግ የመከላከያ አገባብ (Preventive intervention )፤ ፪) በግጭቱ ጊዜ ያሉ እንደ ድርድር፣ ግልግል፣ ስምምነት፣ ተኩስ አቁም፣ ረዴ ግጭት (Conflict coaching) ሦስተኛ ወገን አደራዳሪ/ አንጋሪ (bilateral and unilateral agreements)፤ ፫) ግጭቱ ካከተመ በኋላ የሰላም ግንባታ፣ ሁለትዮሽ/ ሦስትዮሽ ስምምነቶች፣ ካሳ፣ ፍትሕ እርቅ፣ መዋቅር ማስተካከሎች፣ ትምህርቶችና ሥልጠናዎች ወዘተ.።
በሥሥትና በጕጕት የሚታይ ብርቅዬ ለውጥ የመደመር ሒደቱን እንደ አጀማመሩ በፍጥነት ጨርሶ የማባዛት ሒደቱን በፍጥነት መጀመር አለበት።
በእነዚህ ከላይ በተጠቀሱት ሦስት የግጭት ዕድሜዎች ውስጥ ሳያቋርጡ የሚሽከረከሩ ሦስት ተግባራት አሉ፤ አንደኛ፣ ጥናትና ምርምር፣ ሁለተኛ፣ የሰላም ግንባታ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እና ሦስተኛ፣ ሰላምና ግጭት ነክ ጽንሰ ሐሳቦችን ማዳበር (research and studies, peace work and practice and developing theories)።
እንግዲህ በአገራችን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ስንመለከት በርካታ ግልጽ ያልሆኑ ቅደም ተከተሎች በመኖራቸው የትኛውን ተግባር ምን ዐይነት ስያሜ ልንሰጠው እንደምንችል ለማወቅ አዳጋች ነው። ይሁን እንጂ ከአምስት ወር በፊት የነበረውን ቀውስና አገር አቀፍ ግጭት/ዐመፅ ማነጻጸሪያ አድርገን ከወዲህ ያለውን “አንጻራዊ ሰላም” እንደ ድኅረ ግጭት ብንቆጥረው እና እንቅስቃሴዎችን “ድኅረ ግጭት የሰላም ግንባታ” በሚል ስያሜ ብንጠራቸው ሊያነጋግረን ቢችልም እንኳ አግባብነት ያለው ስያሜ ነው ብዬ አምናለሁ። እንዲህም ሆኖ ግን የሰላም ግንባታ ልዩ ልዩ ተግባራት እንደ ብዙ ሙያዎች ሁሉ ድርርቦሽ (Overlap) ሊኖራቸው ይችላል። በተለይ ደግሞ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ቅደም ተከተሎች ግልጽ ባልሆኑበት የአገራችን የለውጥ ሒደት የትኛውን የሰላም ግንባታ ቃል የትኛው ተግባር ዘንድ መጠቀም እንደሚቻል ጥርት አድርጎ ማስቀመጥ አዳጋች ይመስለኛል። በመሆኑም ውይይት ይጠይቃል፤ የሐሳብ ፍልሚያ ያስፈልጋል። የግንዛቤአችን ደረጃ ሊታመን ከሚችለው በላይ ከበጎ ሐሳብ እጅግ ሩቅ ነው፤ የአገራችንም የፖለቲካ ተዋንያን አብዛኛዎቹና አብዛኛውን ጊዜም አጸፋ ምላሻዊ እንጂ፣ ጽንሰ ሐሳቦች ላይ አሰላስሎታዊ አይደሉም። ለዚህ ነው አማኙም ማኅበረ ሰብ በኢትዮጵያዊነቱ ከዚያ ያልተለየው። ስለዚህ ጽንሰ ሐሳባዊ ዘመቻ መያዝ አለብን ብዬ አምናለሁ። እጅና እግራችን ሐሳብ ያቀበለውን ተግባሪ ነውና አቅም የፈቀደውን ያህል በየሙያ ዘርፉ ከብሶታችንም ጋር ቢሆን ጽንሰ ሐሳቦችን እናዳብር የሚል ጥሪ አለኝ። ይህ ጽሑፍ በአብዛኛው ጽንሰ ሐሳቦች ላይ ያተኮረውም፣ በግጭት ጊዜ በአብዛኛው ተግባራችን ከላይ ያለው ትኩሳት ላይ እንዲሁም “በስማ በለው” ላይ የተመሠረተ እሰጥ አገባ እንጂ፣ ከውስጥ ያሉ የግጭት ሰበቦች እንዲሁም የመፍትሔ ውስብስብነት ላይ ያተኮሩ ባለመሆናቸው፣ ያንን የሚያረክስ ሐሳብ ለማቀበል በሚል ነው።
Share this article:
አማረ ታቦር፣ “Seeing and Savoring Jesus Christ” ከተሰኘው የመጋቢ ጆን ፓይፐር መጽሐፍ እየቀነጨበ የሚያቀርበውን ንባብ ሦስተኛ ክፍል እዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል። በዚህኛው የትርጉም ክፍል፣ ስለ ጌታችን ኢየሱስ መለኮትነት ሐተታ የተሰጠበት ሲሆን፣ ይህም መለኮታዊ ማንነት በስሞቹ መንጸባረቁን ያስቃኛል።
ሙስና በአማኝ ማኅበረ ሰቡ ላይ እያሳደረ ያለውን ተጽእኖ ለመመዘን በሚል ሕንጸት የሠራውን የዳሰሳ ጥናት ሙሉውን ሪፖርት ያንብቡ።
ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር፣ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ስለ ወንጌሉ እውነት እንዲሁም እርሱ ስለ መሠረታት ቤተ ክርስቲያን ግድ የሚላቸው ሰዎች ተሰባስበው ያቋቋሙት መንፈሳዊ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ በምድራችን ላይ ያለችው ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን፣ ክርስቶስን መስላ እንድታድግ በሚደረገው የማነጽ ሂደት ውስጥ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ያለመ ነው፡፡ ስያሜውም ይህንኑ የሚገልጽ ነው፤ “ሕንጸት” የግዕዝ ቃል ሲሆን፣ “ማነጽ” ወይም “መገንባት” የሚለውን ፍቺ ይይዛል፡፡
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.
Add comment