
[the_ad_group id=”107″]
ሰው በምድር ቈይታው፣ ገና ሳይጨልምና ሩጫው ሳይቋጭ ከሁለቱ ምርጫዎች አንዱን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መርጦ ይኖራል። ኢየሱስ ወይም ሞትን ይመርጣል። ምርጫውም እስትንፋሳቸው ላልተለያቸው ብቻ የሚሠራ ነው፤ ማንም በሲዖል ወይም በሰማይ ሆኖ ይህን ወይም ያንን ብሎ ሊመርጥ አይችልም፤ በቍሙ የመረጠው ምርጫ ግን ከሁለቱ በአንዱ ነዋሪ እንዲሆን ያደርገዋል። ሰው ሁሉ ከሁለቱ በአንዱ መርከብ ላይ ተሣፋሪ ነው፤ ወይ በኢየሱስ ወደ ዘላለም ሕይወትና ዕረፍት በየዕለቱ እየቀረበና እየተዘጋጀ ይጓዛል፤ ወይም ካለ ኢየሱስ ወደ ዘለዓለም ሞትና ቅጣት ይገሰግሳል። “ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።” (1 ዮሐንስ 5፥12)።
በምንኖርባት ዓለም ብዙ ዕውቀቶችና ጥበባት፣ ብዙ እምነቶችና ፍልስፍናዎች፣ ሰዎችን እያስከተሉና እውነት የሚሉትን እየሰበኩ ነበሩ፤ ዛሬም አሉ። የሰው ልጆችም ይበጃናል ባሉትና ባመኑበት መንገድ እንዲሁም ከቤተ ሰብና ከአካባቢያቸው በወረሱት (በተማሩት) ልማድ በኵል እውነትንና መንፈሳዊ ደኅንነትን ይፈልጋሉ።
ሰው እውነትን የሚያውቀው እግዚአብሔርን በክርስቶስ ባወቀ ጊዜ ብቻ ነው።
አንድ ሰው በደረሰበት መረዳት ልክ ‘እውነት ነው’ ብሎ የሚቀበለው እምነት ይኖረዋል፤ ይህም አንጻራዊ እውነቱ ነው። ሆኖም ግን ቋሚ የሆነ አንድ እውነት አለ። ይህ ቋሚ እውነት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ከእርሱ ውጪ የሆነውም ሁሉ ውሸት ነው።
ሰው እውነትን የሚያውቀው እግዚአብሔርን በክርስቶስ ባወቀ ጊዜ ብቻ ነው። እርሱ ራሱ እውነት መሆኑን የነገረንን ጌታ፣ ከሌሎች ጋር ዐብረን ‘እውነት’ ብንለው፣ እርሱን ውሸታም እናደርገዋለን፤ ከእርሱ በቀር ሌላ አማራጭ እውነት የለምና። እርሱ በቃሉ እንደነገረን፣ እኛም አምነን እንዳየነው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻውን እውነት ነው።
እርሱ ሕይወትና ወደ ሕይወት መግቢያ በር፣ የመግቢያውም ብቸኛ ቁልፍ ነው። እውነት የሚመስሉና ለእውነቱ የተጠጉ ሌሎች ውሸቶች በየበኵላቸው መግቢያ እንደ ሆኑ ቢሰብኩንም፣ መዝጊያውን ከፍቶ ሊያስገባን የሚችለው ትክክለኛው ቁልፍ ኢየሱስ ብቻ ነው። “ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” (ዮሐንስ 14፥6)።
ከምናየውና ከምንሰማው ልዩ ልዩ ልምምድና እንቅስቃሴ የተነሣ ብዙ አማራጭ ያለ ቢመስልም፣ የዘላለም ሕይወት ርግጠኝነትን ለሰዎች ከማቀዳጀት አንጻር ያለው መንገድ፣ በኢየሱስ ክርስቶስና ኢየሱስ ክርስቶስ የሆነው ዘላለማዊ መንገድ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ያለው መንገድ ሁሉ የሞት መንገድ ነው።
ከምናየውና ከምንሰማው ልዩ ልዩ ልምምድና እንቅስቃሴ የተነሣ ብዙ አማራጭ ያለ ቢመስልም፣ የዘላለም ሕይወት ርግጠኝነትን ለሰዎች ከማቀዳጀት አንጻር ያለው መንገድ፣ በኢየሱስ ክርስቶስና ኢየሱስ ክርስቶስ የሆነው ዘላለማዊ መንገድ ብቻ ነው።
ሰዎች በልዩ ልዩ ሃይማኖት ወይም አስተሳሰብ መንገድ ላይ እንዳሉ ቢያምኑም፣ በኢየሱስ ካልሆኑ ግን መንገዳቸው የሞት መንገድ ይሆናል። ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ የላቸውም። ከኢየሱስ መንገድና ከሞት መንገድ ውጪ ሌላ ሦስተኛ አማራጭ የለም። ሰው ሁሉ ከእነዚህ ከሁለት መንገዶች በአንዱ ላይ እየተመላለሰ ለዘላለማዊ ቤቱ የሚዘጋጅ ነው።
ሰው ሕይወት በሆነው በኢየሱስ መንገድ ተጕዞ ሕይወትን ካላገኘ፣ በሞት መንገድ ጸንቷልና መጨረሸው የዘላለም ሞት ነው። ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ መንገድ ነን የሚሉ ሁሉ ምንም በአቀራረብ የተለያዩና የተራራቁ ቢመስሉ፣ ሁሉም በሁለተኛው አማራጭ፣ ማለትም በሞት መንገድ ላይ ያሉ ናቸው፤ የሚያመሩትም ወደ ዘላለም ሞት ነው፤ ከሞት ወደ ሕይወት የሚያሻግረው ብቸኛ መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና።
እንዲህ ያለውን ዐሳብ በድፍረትና በርግጠኝት መናገር በአስተሳሰባችን ያልሠለጠንን፣ ለሌሎች እምነትና አመለካከት አክብሮት የሌለን ቢያስመስለንም፣ ለሰዎች የተሰጠው ዘላለማዊ የድነት መንገድ ይህ ብቻ ነውና እውነትን በፍቅር ከመናገር ወደ ኋላ አንልም።
በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን የመረጥን ሁሉ፣ ዘላለማዊ የሰማይ መንግሥት ዜግነትን አግኝተናል። መንግሥቱም የሕያዋን መንግሥት ነው፤ ኢየሱስን ያልመረጡ ሁሉ በሞት አሉና ዘላለማዊውን የሕያዋን መንግሥትን አያዩም። “እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያንም የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24)።
እንዲህ ያለውን ዐሳብ በድፍረትና በርግጠኝት መናገር በአስተሳሰባችን ያልሠለጠንን፣ ለሌሎች እምነትና አመለካከት አክብሮት የሌለን ቢያስመስለንም፣ ለሰዎች የተሰጠው ዘላለማዊ የድነት መንገድ ይህ ብቻ ነውና እውነትን በፍቅር ከመናገር ወደ ኋላ አንልም።
ሰው ሁሉ የተፈጠረበትን ክቡር ዐላማ፣ ፈጣሪው ያየለትን ድንቅ ሕይወትና ያንንም ከመኖር ከልክሎት ያለውን ጕድለቱን፣ እንዲሁም ከጕድለቱ ሊያወጣው የሚችለውን ብቸኛ መፍትሔ አውቆ በዚያ ቢጠቀም እጅግ የተሻለ ነው። ከዚህ አማራጭ ውጭ ያለው በኀጢአት በተገዛ የዓለም ውሸት ውስጥ ለዘላለም መጥፋት ነው። ከሞት ሕይወት እጅግ የተሻለና ሊወዳደር የማይችል ነው። ሕይወትም እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
በኢየሱስ የሆንን እኛ በሕይወት ነን፤ ማንም እርሱን በሕይወትነቱ ቢያውቀው በሕይወት ይኖራል። ሊያውቀው ባይወድድ ግን በሞት ይቀራል፤ መጨረሻውም ለዘላለም ከእግዚአብሔር የመለየት ቅጣት ይሆናል። “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት አንኳ ሕያው ይሆናል፤ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ …” (ዮሐንስ 11፥25-26)።
ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በጸጋው ምሕረት፣ በመስቀሉ ሥራ ከበደሉ ነጻ እስካልሆነ ድረስ ሞት የተፈረደበት፣ ከእግዚአብሔር ክብር የጎደለ ኀጢአተኛ ነው። ሕያው መሆንን ለሚወድዱ ሁሉ፣ “ኢየሱስን ምረጡ፤ ከዘላለም ሞት አምልጡ!” ለሚለው የምሕረት ድምፅ ልባቸውን ላላደነደኑ ኢየሱስ ሕይወትን ይሰጣቸዋል፤ ይህንም የሚያደረገው ስለ ወደደን፣ አስፈላጊ የሆነውን ዋጋ ሁሉ ከፍሎ ነው።
“ … እግዚአብሐር በምሕረቱ ባለጠጋ ስለ ሆነ፣ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ፣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሰጠን፤ በጸጋ ድናችኋልና።” (ኤፌሶን 2፥4-5)።
Share this article:
የትንሣኤን በዓል በምናከብርበት በዚህ ሰሞን፣ ስለ ጌታችን ትንሣኤ ምንነትና ፋይዳ ባትሴባ ሰይፉ የሚከተለውን አስነብባለች።
አገራችን አሁን ያለችበትን ፖለቲካዊ ኹኔታ አስጊ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ የሴራ ትርክት በአየሩ ላይ መናኘቱ እንደ ሆነ ይህ የሰሎሞን ጥላሁን ጽሑፍ እያሳሰበ ተጨባጭ ምክንያታዎነት መድረኩን እንዲረከበ ጥሪ ያደርጋል።
ከ1960ዎቹ የሙሉ ወንጌል ሀ መዘምራን እስከ ዜማ ለክርስቶስ ህብረት፣ በአንድ እጅ ጣት ከሚቆጠሩ ዝማሬዎች እስከ አለንበት ዘመን የዝማሬ ጎርፍ፣ ከለሆሳስ የጓዳ ዝማሬ እስከ አደባባይ ሆታ፣ ከአንጋፋ እስከ ወጣት ዘማሪያን እስከ ወጣት ዘማሪያን . . . ይህ የኢትዮጵያ ቤ/ክ የዝማሬ ታሪክ ነው፡፡ መዝሙር ተቀዛቅዟል የለም አድጓል የሚለውን ሙግት የሻረ አዲስ የዝማሬ መንፈስ፣ ሁሉንም የሚያስማማ አቀራረብ፣ የተዋጣለትና የተሟላ ዝማሬ እነሆ ከወጣት ዘማሪያን ለኢትዮጵያ ቤ/ክ ተብርክቷል፤ ከዜማ ለክርስቶስ፡፡ ወጣትነታቸውን፣ ጉብዝናቸውንና ችሎታቸውን ሁሉ ለጌታ የሰው ወጣቶች የሰጠኸንን አንሆ ብለው ለዘመናት ንጉስ ከልብ የሆነ ሕያው ዝማሬ ተቀኝተዋል፡፡
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.
1 comment
ተባረክ የእግዚአብሔር ስው::