
የቤተ ክርስቲያን የማንነትና የወንጌል ተልእኮ ተሐድሶ
ግርማ በቀለ (ዶ/ር) ለሕንጸት በላከው በዚህ ጽሑፉ፣ የእግዚአብሔር ተልእኮ ምንነትን፣ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ተልእኮ ያላትን ሚና ምንና እንዴት ያለ መሆኑን እየተነተነ ያስቃኛል።
[the_ad_group id=”107″]
“እጅጉን የተወደድሽ፣ጸጋን የሞላብሽ ውዷ ባለቤት ክብርት ካትሪን ሉተር (ዶ/ር) የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛልሽ!”
ካትሪን ቫን ቦራ ሊፕንዶርፍ፣ ሳክሰኒ ውስጥ ጃንዋሪ 29 ቀን 1499 ከምስጉን ደኻ ቤተ ሰብ ተወለደች። በ1504 ብርሄና ውስጥ ወደሚገኝ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ገብታ ማንበብ፣ መጻፍ፣ የላቲን ቋንቋ እና መዘመር ጠንቅቃ ተማረች። በ1508 ናምብሽን ወደሚገኘው ማሪየንትሮን ገዳም ተቀላቅላ በ1515 ቃል መሃላ በመፈጸም ምንኩስናዋን ተቀበለች። በናምብሽን ቆይታዋ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ፣ ዕርሻ ማስተዳደር እና በሽተኞችን መንከባከብ እንደተማረች ይነገራል።
የቤተ ክርስቲያን ተሓደሶው እንቀስቃሴ በመላው አውሮፓ ተቀጣጥሎ ገዳማት ውስጥም ዘልቆ ገባ። መነኩሴው ማርቲን ሉተር በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አበክሮ ከተቃወማቸው ልማዶች አንዱ መነኮሳቱ እና አገልጋዮቹ (Nons and Clergies) እንዳያገቡ ያለባቸውን ክልከላ ነው። ይህን እገዳ አጥብቆ መቃወሙ ለብዙ መንኩሳት እና አገልጋዮች ድፍረት እየሰጠ ትዳር እንዲመሠርቱ ከማድረጉም አልፎ፣ ያገቡ ሰዎች በቤተ መቅደስ አገልጋይ እንዲሆኑ በር የከፈተ ታሪካዊ ክስተት ነበር። በአፕሪል 17 ቀን 1523 ካቲ ቫን ቦራ፣ ከዐሥራ አንድ መነኩሳት ጋር በመሆን ከነምብሽን የገዳም ሕይወት በመሽሽ በቪተንበርግ ከተማ በሽማግሌው ሰአሊ ሉቃስ ክራናች መኖሪያ ቤት ውስጥ ተሸሸጉ። ሉተር ውሃ አጣጪውን ያገኘው ተሓድሶውን የተቀላቀሉትን እነዚህን በሽሽት ላይ ያሉ የቅዱስ ቤኔዲክት ወይም የክሌርቯው ቅዱስ በርናርድ ተከታይ የነበሩትን መነኩሳት (ex-Cistercians) ትዳር እንዲያገኙ በሚረዳበት ወቅት ነበር።
ካትሪና ቫን ቦራ ከገዳም ሕይወቷ እንደ ወጣች መጀመሪያ ላይ ከቪተንበርግ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከነበረው ሂክሮኒመስ ቦምጋርትነር ጋር ጋብቻ ለመመሥረት ፍቅር ጀምራ ነበር። የቦምጋርትነር ፍቅር ያልሰመረላት ካቲ ለቪተንበርግ ፕሮፈስር ካስፐር ግላትስ ብትታጭም፣ ‘ልቤ የፈቀደው ማርቲን ሉተርን ነው’ በማለቷ፣ ግላትስን ለትዳር አሻፈረኝ አለች። መነኩሴው ሉተር ግን ልቡ የደነገጠው ለካቲ ጓደኛ አቪ ቮን ሾንፊልድ እንደ ነበር ለወዳጆቹ ተናግሯል። ይሁን እንጂ ያለውን ማንኛውንም ተቃውሞ በተግባር ለመግልጽ ወደኋላ የማይለው ደፋሩ እና ልበ ሙሉው ሉተር፣ አስቀድሞ ለወዳጆቹ “ልቤ በካቲ ፍቅር አልቀለጠም” እያለ ቢከርምም፣ ከካቲ የቀረበለትን የእንጋባ ጥያቄ ሳያቅማማ ተቀብሎ በዘመኑ አውሮፓን ያነጋገረ፣ የክፈለ ዘመኑ “ቅሌት” ያስባለ፣ እስከ ወዲያኛውም የዓለምን ታሪክ የቀየር ተግባር ፈጸሙ። በጁን 13 ቀን 1525 ማርቲን ሉተር እና ካትሪና ቫን ቦራ የምንኩስና ማህላቸውን አፍርሰው ትዳራቸውን መሠረቱ ።
ይህ የሉተር ውሳኔ ያልተጠበቀ እና ጓደኞቹን ግራ ያጋባ እንደ ነበር በተሓድሶው እንቅስቃሴ የሉተር ቀኝ እጅ የነበረው ፊሊፕ ሜላንክተን በ1525 ተናግሯል። ሉተር ስለ ውሳኔው “ካቲን በማግባቴ መላእክት ሲደሰቱ ስይጣንን አስለቅሽዋለሁ” ሲል በኩራት አስረድቷል። ምን አልባት ማርቲን ሊገለጥ ያለው የካትሪን አይበገሬ ፅናት ልዩ ፍቅር እና መልካም የቤት አስተዳደር ብቃት በልቦናው ታይቶት ይሆን? እንጃ፤ ሳይሆን አይቀርም። “ከማግባቴ በፊት አልጋዬ ለረጅም ጊዜ አይነጠፍም፤ አንሶላውም በላብ በመበላሽቱ ሽታው ይከረፋል። ብዙ ሰዓት እሠራ ስለ ነበር ደክሞኝ መጥቼ ተዘርሬ እተኛበት ነበር። ካቲ ስትመጣ ታሪክ ተቀየረ። አልጋው በሥነ ሥርዐቱ ይነጠፋል፤ አንሶላው ቶሎ ቶል ይቀየራል፤ የቤቱ ንጽሕና በአግባቡ ይጠበቃል” ሲል ካቲን በማግባቱ እንዴት ያለ ምቾት እንደተሰማው መስክሯል። የትዳር በርከቱ በዚህ ሳያበቃ 20 ዓመታትን በዘለቀው ትዳራቸው ሉተር እና ካቲ ሃንስ (ዮሐንስ)፣ ኢሊዛቤት፣ ማግዳሊን፣ ማርቲን፣ ፖል እና ማርጋሪታ የተስኙ 6 ልጆችን አፍርተዋል።
ማርቲን ሉተር ለትዳር የሚመኙት ዐይነት ሰው አልነበረም። “ሉተር ዐመለ ጥፉ፣ ተጨቃጫቂ፣ ግልፍተኛ እና ችኩል ዐይነት ሰው ነበር። ሉተር ሁሌም ተጓዥ፣ ከተራ ቤተ ሰብ የመጣ፣ የጋብቻ ቀለበት እንኳን መግዛት ያልቻለ ደኻ፤ ነጭ ደኻ ነበር” ይላል አንድሪው ከሪ “How a Runaway Nun Helped an Outlaw Monk Change the World” በሚል ርእስ በናሽናል ጂኦግራፊ ድረ ገጽ ላይ ያቀረበው ጽሑፍ። ሉተር ትዳር ሲመሠርት ከጥቂት መጻሕፍትና ንጽሕና ከጎደላቸው ልብሶቹ በስተቀር ምንም አልነበረውም። የ42 ዓመቱ ሰባኪና አስተማሪ ሉተር ለጳጳሱ የቤተ ክርስቲያን አፍራሽ፣ የስሕተት ትምህርት አስተማሪ ተብሎ በአደባባይ የተወገዝ፣ ጽሑፎቹም እንዲቃጠሉ የተፈረደበት ርጉም ሰው ቢሆንም፣ ለካትሪን ቫን ቦራ ግን ከዚህ የተለየ ልቧን ያሽነፈ ጀግና ነው!
እንዲህ ልቧ የተሽንፈለት ይህ ማርቲን ሉተር ግን ማን ነው? በማተሚያ ማሽን መፈብረክ ታግዞ በ16ኛው ክፍለ ዘመን በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተንሰራፍቶ የነበረውን ሙስና (ሌብነት) በማየት በኦክቶበር 31 ቀን 1517 በቪተንበርግ መቅደስ ግድግዳዎች ላይ 95 አናቅጽ ቸንክሮ ተቃውሞውን በይፋ በመግለጽ የቤተ ክርስቲያንን ተሓድሶ ያቀጣጠለ፣ ሃሞተ ኮስታራ፣ ደፋር እና ጀግና፣ እስከወዲያኛው የዓለምን ታሪክ የቀየረ ጀርመናዊ መነኩሴ!
ትዳር ለካቲ እና ለሉተር አልጋ በአልጋ አልሆነላቸውም። ሉተርን መነከባከብ ለካቲ ቀላለ የቤት ሥራ አልሆነም። ሉተር አብዝቶ ታማሚ ነበር። አንዳንድ ጊዚ የሆድ ድርቀት፣ እንቅልፍ እጦት፣ የመገጣጠሚያ አጥንት ሕመም፣ የኩላሊት ጠጠር፣ የጭንቅላት ማዞር እና የመሳሰሉት ሕመሞች በእጅጉ ያሰቃዩታል። ‘ዋናው ጤና ነው’ የምትለው ካቲ የባህል መድኃኒት ቅመማ ችሎታም ስለ ነበራት ሥራ ሥር በጥሳ እና ቀምማ እንዲሁም ባላት የማሳጅ ችሎታ የውድ ባሏን ጤና ትንከባከብ ነበር። ካቲ – ሚስት ብሎ ዝም!
‘የጎን አጥንቴ ካቲ’ ይላታል ሲያቆላምጣት። ሉተር የካቲ ፍቅር ሲጠናበት፣ በሕመሙም ወቅት እንክብካቤዋና ለአግልግሎቱ የጀርባ አጥንት እንደሆነች ሲያይ ካቲን ከማወደስ እና ከማድነቅ ሌላ አማራጭ አልነበረውም። ሉተር ለካቲ ያለውን አክብሮት ማስታወሻነት ለመዘከር ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ገላቲያ ሰዎች የጻፈውን መልእክት “የኔ ካቲ ቫንቦራ” እያለ በቁልምጫ ይጠራው እንደ ነበር (መልእክቱን በጣም ይወድደው ስለ ነበር) ሮላንድ ቤንተን ስለ ማርቲን ሉተር በጻፈው የሕይወት ታሪክ ላይ ያስረዳል (Roland Benton, Martin Luther, Here I Stand)።
አንዳንድ ጊዜ “ብዙ ዋጋ ከከፈለልኝ ጌታ አስበልጬ ለካቲ አክብሮት እሰጣለሁ” እያለ ይጨነቅ እንደ ነበር የታሪክ ጸሐፊው ቤንተን ይገልጻል። ሉተር ከካቲ ብቻ ሳይሆን “አይ ጠላዋ! አየ ጠጇ” እንዲሉ ከምትጠምቀው የቢራ መጠጥም ጋር ፍቅር እንደነበረው ይናገራል። “ከቤቴ ርቄ ስሄድ በቤቴ የሚጠመቀው ቢራ፣ የወይን ጠጅ እና ቆንጆዋ ሚስቴ ሁሌም ይናፍቁኛል” ይል ነበር። ሉተር ለካቲ በፌብሪዋሪ 17 ቀን 1532 ስለጉዞው በጻፈው ደብዳቤ ላይ፣ “ማታ ማታ ለ6 ወይም ለ7 ሰዓት ያህል ደስ የሚል እንቅልፍ እተኛለሁ፤ ምን አልባት ቀን የምጠጣው ቢራ ሳይሆን አይቀርም” ሲል ለቢራ ያለውን ፍቅርም ጠቅሷል (February 27, 1532; Letters to his Wife By Martin Luther – 1483-1546)።
ሉተር ለሙዚቃ ጥልቅ ፍቅር ብቻ ሳይሆን ሉት (Lute) እና ዋሽንት(flute) የተባሉ የክር እና የትንፋሽ የሙዚቃ መሳሪያዎችን አሳምሮ ይጫወታል። መዝሙር መዘመርም ይወድድ ነበር። ሉተር በማዕድ ዙሪያ ሲቀመጡ ብዙውን ጊዜ ንግግር ያበዛል (አይ የሰባኪ ነገር!) ይህን ባሕርይ በተደጋጋሚ ያየችው ካቲ፣ በአንድ ወቅት ንድድ ብሏት “ዶክተር ለምን አፍህን ዘግተህ የቀርበልህን አትበላም?” ብላ ብትቆጣው፣ ግልፍተኛው ሉተር “ምናለ ሴቶች አፋቸውን ከመክፈታቸው በፊት የጌታን ጸሎት ደጋግመው ቢጸልዩ” ሲል በምላሹ አምባርቆባታል። ካቲም አንዳንዴ ነርቩን ትነካው ነበር ማለት ነው!
ካትሪን ቫን ቦራ ለሉተር ሚስት ብቻ ሳትሆን የቪተንበርግ የንጋት ኮከብ፣ ‘የሱልስዶርፍ ሀብታም ወይዘሮ’ እያለ የሚኩራራባት ንግድ አዋቂም ሴት ነበረች። ጎህ ከመቅደዱ ከቪተንበርግ ከተማ ነዋሪዎች ቀደማ ተነሥታ ሥራዋን ትከውናለች። “ሉተር በዕለት ተለት የቤተ ሰቡ አስተዳደር ብዙ ጣልቃ አይገባም፤ ካቲ የቤቱን ሥራ በመቆጣጠሯ ሉተር እጅግ ደስተኛ ነበር። ይህም ሉተር በነጻነት ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ በብቃት ለማስተማር፣ ለመስበክ እና የጽሑፍ ሥራውን ለመሥራታ አስችሎታል” ትላለች በርሊን በሚገኘው ፍራይ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ተመራማሪዋ ጋብሪየል ያንከ።
ካቲ፣ ከሉተር እውቀት ለመቅሰም እና ትምህርቱን ለመስማት ወደ ቤታቸው ከሚመጡ ስዎች በምትሰበስበው የክፍያ ገንዘብ በእርሻ መሬት፣ የአሳማ እና የዓሣ እርባታ እንዲሁም የአትክልት ቦታዎችን እየገዛች የቤተ ሰቡን ፋይናንስ እና ሀብት ታሳድግ ነበር። ሉተር የአትክልቱን ቦታ ሲንከባከብ ካቲ የአስማ፣ የከብት እና የአሳ እርሻውን ጠንክራ ትንከባከብ ነበር። ማርቲን ከመኖሪያቸው ቪተንበርግ ከተማ ርቆ ባለ ሱልስዶርፍ በሚባል ቦታ ካቲ የምታስተዳድረው የእርሻ ቦታ ነበረው። ይህን ትጋቷን ያየው ሉተር “በሥጋ ቪተንበርግ፣ በመንፈስ ሱልስዶርፍ የምትኖረው የሱልስዶርፍ ሀብታሙ ወይዘሮ” እያለ ካቲ ላይ ይቀልድባት ነበር። ቀደሞ ለገዳም አገልግሎት ይውል የነበረ ባለ 3 ፎቅ መኖሪያ ሕንጻቸውን የቪተንበርግ የእውቀት እና ማኅበራዊ ሕይወት ማእከልነት ደረጃ ቀይራዋለች።
ካቲ ግዙፍ የነበረውን የሉተርን መኖሪያ ቤት ቀጥ ለጥ አድርጋ በማስተዳደር ብቃት ሉተርን ከማስደመም አልፋ በሴቶች ላይ ያለውን አመለካከት በእጅጉ እንዲያሻሽልም ረድታዋለች። ማርቲን ሉተር በቤቱ ውስጥ ከአብራኩ ከተገኙ 6 ልጆች በተጨማሪ ወደ 20 የሚጠጉ ተማሪዎች፣ 8 ወላጅ አልባ ሕፃናት፣ በወቅቱ በአውሮፖ ተከስቶ ከነበረው ወረሽኝ በመሸሽ በቤቱ የተጠለለ ሌላ ትልቅ ቤተ ሰብ፣ የተለያዩ እንግዶች/ጎብኝዎች እና የቤቱን ባለሟሎችን ቀጥ አርጎ ለማስተዳደር እንደ ካትሪን ቮን ቦራን ያለች መልካም ሚስት ለሉተር ታስፈልገው ነበር። እመቤት ካቲ ይህች ነበረች!
ካቲ ሚስት ብቻም አልነበረችም። ባለባት የሥራ ጫና ሳትወስን በትጋት ቅዱሳን መጻሕፍትን አንባቢም ናት። በዘመኑ ለነበሩ ሴቶች ከወንዶች ጋር አንድ ላይ ቁጭ ብሎ በጠረጴዛ ዙሪያ መወያየት የተለመደ ባይሆንም፣ ካቲ ግን ምሁራዊ ውይይቶችን ለማድረግ የሚያስችል የላቲን ቋንቋ ችሎታ እና የሥነ መለኮት ንቃት ነበራት። ከእራት በኋላ ሉተር፣ ካቲ እና የተመረጡ እንግዶች በጠረጴዛ ዙሪያ ስለ ሥነ መለኮት፣ ፖሊቲካ እና የተሓድሶውን የአስተሳሰብ አድማስ ለማጠናከር በሚያደርጓቸው ሞቅ ያሉ ውይይቶች የነበራት ንቁ ተሳትፎ ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው።
“የቫን ቦራ ታሪክ የቤተ ክርስቲያን ተሓድሶ እንቅስቃሴ ውጤት የአንድ ሰው ተሳትፎ ብቻ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው። ሉተር በቤተ ክርስቲያን ተሓድሶ ውስጥ የራሱን ሚና ተጫውቷል። ነገር ኝ ቫን ቦራ የነበራትንም አስተዋእጾ ማስተዋል ይገባል” ትላለች የዶክትሬት መመረቂያ ጽሑፏን በቫን ቦራ ላየ የሠራችው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመራማሪ ሳቢን ክሬመር። ማርቲን ሉተር አብዛኛው በተሓድሶ እንቅስቃሴ ውስጥ ያነሣቸው የነበሩ ሐሳቦች ጥልቅ ምሁራዊ ውይይት ይደረግባቸው የነበረው ማታ ማታ ካቲ በምታሰናዳው ማእድ ዙሪያ መሆኑ ሲታሰብ፣ ተሓድሶው ያለ ቅዱሳን እኅቶች ተሳትፎ ግቡን አይመታም ማለት ይህን ጊዜ ነው።
Share this article:
ግርማ በቀለ (ዶ/ር) ለሕንጸት በላከው በዚህ ጽሑፉ፣ የእግዚአብሔር ተልእኮ ምንነትን፣ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ተልእኮ ያላትን ሚና ምንና እንዴት ያለ መሆኑን እየተነተነ ያስቃኛል።
በባለፈው የፈረንጆች ዓመት ማብቂያ ላይ፣ ማለትም እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 25 2014 ኤሪክ ሜታክስስ የተባለው ዕውቅ ጸሐፊ በዎልስትሪት ጆርናል “Science Increasingly Makes the Case for God” በሚል ርእስ ሳይንስ ፈጣሪ ስለ መኖሩ የሚቀርቡ ሙግቶችን ዕለት ዕለት ይበልጥ እየደገፈ ስለ መምጣቱ ጽፏል።1 ይህ አነጋጋሪ ጽሑፍ እ.ኤ.አ. በ1966 በታይም መጽሔት “ፈጣሪ ሞቷል?” የተሰኘውን ጽሑፍ መነሻ በማድረግ የዘመኑ ሳይንስ የፈጣሪን አለመሞት፣ ብሎም ስለ መኖሩ ይበልጥ ርግጠኛነትን የሚያስጨብጥ ግኝት ላይ እንደ ደረሰ ይናገራል። ይህ ግኝት ምን እንደሆነና ከሜታክስስ ጽሑፍ ጋር የተገናኙ አንዳንድ ሐሳቦችን በዛሬው ጽሑፋችን ለመዳሰስ እንሞክራለን።
“I believe ecumenical unity can save Ethiopia or at least it can play a very great role in minimizing differences and creating unity in this country.” Writes Naol Befekadu.
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.
1 comment
ወንድም ታምራት፡
የካታሪና ቮን ቦራን የህይወት ታሪክ በመተርጎምህ (ወይም ኣሳጥረህ በመጻፍህ) በጣም ላመሰግንህ እወዳለሁ። ነገር ግን እንደ ማጣቀሻ የተጠቀምክባቸው መጻህፍት ወይም ጽሁፎች በመጨረሻው ክፍል ቢጠቃለሉ ኖሮ ጥሩ ነበር እላለሁ። ተባርክ፡ ሌላ ተጨማሪ ስራ በመስራት ለበረከት ሁን!