[the_ad_group id=”107″]

ጤነኛ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖረን ኀላፊነታችንን እንወጣ

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስትና ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በፈተና ውስጥ እንዳለ እናምናለን፡፡ እነዚህ ፈተናዎች ደግሞ የወንጌላውያኑን ማንነት እያደበዘዙ፣ በማኅበረ ሰቡ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት እያጠፉ፣ የአማኞችን የሕይወት ጥራት እየቀነሱ፣ ቤተ ክርስቲያን ምድራዊና ራስ ተኮር ብቻ እንድትሆን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ይህ በዚህ ከቀጠለ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ምን ዐይነት መልክ ሊኖረን እንደሚችል መገመት አስቸጋሪ አይሆንም፡፡

ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቋቋምና አልፋ ለመሄድ ብዙ መሥራት ይጠበቅባታል፡፡ ልትወጣቸው ይገባል ከምንላቸው መካከል፡- የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ተገቢውን ስፍራ መልሶ እንዲይዝ ማድረግ፤ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በተወሰኑ “ቅብዓን” ላይ ብቻ እንዲንጠለጠሉ አለማድረግ፤ ከእግዚአብሔር ለተቀበሉት መንጋ እና ለመድረኮቻቸው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ፤ እረኞች በመገናኛ ብዙኀን ለሚተላለፉ መልእክቶች ንቁ ክትትል በማድረግ ምእመናንን ወደ ጠማማ የሕይወት መንገድ ከሚወስዱ ትምህርቶች የሚጠብቁበትን ሥርዐት መዘርጋት ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

የቤተ ክርስቲያን አጋዥ የሆኑ የነገረ መለኮት ተቋማትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካለት ስለ ቤተ ክርስቲያን ጤነኛ አስተምህሮ ልዩ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል እንላለን፡፡ ጥራት ላለው የነገረ መለኮት ትምህርት መስፋፋት ትኩረት መስጠት፤ ዐውደ ገብ የሆነ የሥነ መለኮት ሥርዐተ ትምህርት ማጎልበት፤ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ችግር ፈቺ የሆኑ የምርምርና የጥናት ውጤቶችን ማበርከትና ማበረታታት፤ ኑፋቄና ኑፋቄያዊ ለሆኑ ትምህርቶች ተገቢውን ምላሽ በወቅቱ በመስጠት የዕቅበተ እምነት ኀላፊነትን መወጣት፤ በአገልግሎት መስኩ ላይ ያሉ አገልጋዮች የትምህርት ሥልጠና (የአጭር ጊዜም ሊሆን ይችላል) የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት፣ ብሎም ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በአገርኛ ቋንቋ የሚማሩበትን ዕድል መፍጠር፡፡

ከነገረ መለኮት ትምህርት ቤቶች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተመርቀው የሚወጡ ምሩቃንም ሊጫወቱት የሚገባው ሚና ሰፊ ነው እንደ ሆነ እናምናለን፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታ በማጥናት ለችግሮቿ መፍትሔ የሚሆኑ ሐሳቦችን መፈንጠቅ፤ ዐውዳዊነትን የአገልግሎታቸው ማዕከል ማድረግ፤ ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ጋር ጥሩ ግንኙነት በመፍጠር ለሥነ መለኮት ትምህርት ማበብ ምቹ ድባብን መፍጠር፤ ባገኛቸው አጋጣሚዎችና የአገልግሎት በሮች፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም ባለ ሥልጣንነት ማስተማር፤ በአፍቅሮተ ንዋይ ሳይሳቡ የእውነትን ቃል በፍቅርና በግልጽ ማስተማር የተልእኳቸው አካል መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ይህን ስንል ለወንጌላዊያን ክርስትና መፍትሔ አምጪዎች የነገረ መለኮት ተቋማትና ምሩቃኑ ብቻ ናቸው እያልን አይደለም፤ እነዚህ ተቋማት ሊጫወቱት የሚገባው ሚና እጅግ የላቀ መሆኑን ለማሳየት ነው እንጂ፡፡ ስለ ቤተ ክርስቲያን ጤነኛ አካሄድ ይገደናል የሚሉ ሁሉ ኀላፊነታቸው ትልቅ እንደ ሆነ እናውቃለን፡፡ ለክርስቶስ አካል ጤነኝነት ሁሉም እንደተሰጠው ጸጋ መጠን ይሠራ ዘንድ መልእክታችን ነው፡፡

የተዘነጋው አሁን

ሁላችን በሐሳብ ባህር ላይ ቀዛፊዎች ነን። ቀዘፋው ደግሞ በትላንት እና በነገ የሐሳብ ማዕበል የሚናጥ ነው። ከትላንት ለመማርም ሆነ ነገን የተሳካ ለማድረግ አሁንን መኖር መጀመር እንዳለብን ይህ የተካልኝ ነጋ (ዶ/ር) መጣጥፍ መንገድ ይጠቁማል።

ተጨማሪ ያንብቡ

ቃለ መጠይቅ ከአገኘሁ ይደግ ጋር

አገኘሁ ይደግ በኢትዮጵያ የወንጌላውያን አማኞች የዝማሬ አገልግሎት ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚነሡ ዘማሪያን መካከል የሚጠቀስ ነው። ዘመን ዘለቅ በሆኑት ዝማሬዎቹም ብዙዎች ተጽናንተዋል፣ ታንጸዋልም። የሕይወትን አስቸጋሪ ፈተናዎች በመቋቋም እግዚአብሔርን በጽናት ማገልገሉ ለአርኣያነት የሚያበቃው እንደ ሆነ የሚያውቁት ይናገራሉ። የዚህን ዘማሪ 25ኛ የአገልግሎትና 20ኛ የትዳር ዘመን በዓል ምክንያት በማድረግ ሕንጸት የቆይታ ዐምድ እንግዳ አድርጎታል። ጳውሎስ ፈቃዱ ከዘማሪ አገኘሁ ይደግ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ተጨማሪ ያንብቡ

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.