[the_ad_group id=”107″]

ጲላጦስማንነው?

በሉትራን ቤተ እምነት፣ ከጌታ በመቀጠል ብዙ ጊዜ ስሙ የሚጠራው ሰው፣ ጳውሎስ ወይም ጴጥሮስ ወይም ከነቢያት አንዱ ወይም ሉተር አይመስለኝም። በእኔ ግምት ጲላጦስ ነው። በሐዋርያት የእምነት መግለጫም ሆነ በኒቂያ የእምነት መግለጫዎች ላይ ስሙ የተጠቀሰ ብቸኛ ግለ ሰብ ቢኖር ጲላጦስ ነው። እነዚህ የእምነት መግለጫዎች ስለ ሥላሴና ስለ ክርስቶስ ሰውነትና አምላክነት የሚገልጡ ናቸው። በየእሑዱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምእመናን እምነታቸውን ያሳውቁባቸዋል። 

የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለምን የእነርሱን ስም አስገቡ የሚለውን ለሌላ ጊዜ እንተወው። ግን ከትውልድ ትውልድ በተላለፉና ሉትራን ብቻ ሳንሆን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በሚቀበሏቸው በእነዚህ መግለጫዎች መካተቱ ግርም የሚል ነው። በዚህ የተነሣ በተለያዩ ቋንቋንዎች ጲላጦስ በየእሑዱም ሆነ ከዚያ ውጭ በሚኖሩ የአምልኮ ሥነ ሥርዐቶች ላይ ስሙ ይነሣል። 

ጲላጦስ በጣም ጨካኝ መሪ ነበር። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያወሱት ከሥልጣኑ የመወገዱ ምክንያቱ፣ ያለ አግባቡ ለሃይማኖት ብለው የተሰሰቡ የሰማርያ ሰዎችን በመግደሉ ነበር። ጕዳዩ ከፖለቲካ ጋር ያልተገናኘ ነው ብለው ተቀማጭነቱ ሶሪያ ለነበረ ለሌላ የሮም አለቃ ክስ ስለቀረበበት፣ ሮም በጢባሪዮስ ዘንድ እንዲቀርብ ተወሰነበት። በኢየሩሳሌም ለዐሥር ዓመታት ገዥ የነበረ ሲሆን፣ የጌታ የምድር አገልገሎት በእርሱ የሥልጣን ዘመን ተጀምሮ የተጨረሰ ነው። ጌታ ብቻ ሳይሆን መጥምቁ ዮሐንስም እርሱ በሥልጣን እያለ ነበር ያገለገለው። 

በሌሎች የክርስትና እምነቶች ዘንድ፣ ጲላጦስ በክርስቶስ አምኖ መሥዋዕትነት ከሚስቱ ጋር ተቀብሏል ተብሎ ይታመናል። ለምሳሌ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ጲላጦስን እንደ ሰማዕት ተደርጎ የሚቈጠር ሲሆን፣ ካልተሳሳትሁ ሰኔ ላይ የሚዘከርበት ቀን አለው። 

እኔ እንደምረዳው፣ ይህ ሰው ለሥልጣኑ ያደረ ከመሆኑ የተነሣ፣ ከሾመው የሮም መንግሥት ጋር እንዳይጣላ ፈርቶ ጻድቁን ጌታ እንዲሰቀል ፈርዶበታል። ፍርድን ስናነሣ የታሪክ ጽሑፎች ከእርሱ በፊት ከነበሩ የሮማ ሹማምንት በተለየ፣ በይሁዳ ግዛት ፍርድ እንዲሰጥም ልዩ ሥልጣን የተሰጠው እንደ ነበር ተነግሮለታል። ነገር ግን፣ ይህን ዕድል ለመልካም አልተጠቀመውም። በርባንን ለቅቆ ጌታን አስገርፎ ሰቅሎታል። ሚስቱ የነገረችውን አለመስማቱ፣ “እውነት ምንድን ነው?” ብሎ ከእውነት ጌታ ተነግሮት ያለመስማቱ፣ ሥልጣን ምን ያህል ልቡን እንዳሸነፈው ያመለክታል። ሕዝቡ፣ ‘ለቄሳር ያደርህ አይደለህም’ ብሎ እንዳይከስሰው በመፍራት፣ እውነትን እያወቀ እውነትና መንገድ የሆነውን ጌታ እንዲሰቀል ፈርዶበታል። ስለዚህም ክፉ ሥራው ከዘመን ዘመን እየተሻገረ ይነገራል። 

ዛሬስ፤ ለሥልጣኑና ለገዛ ጥቅሙ ሲል ስንቱ ነው ጌታን እያወቀ አሳልፎ የሰጠው? ላለመነካካት ሲል እውነትን ያልካደ ማን ነው? ጌታ በልዩ ልዩ መንገድም ሆነ በቃሉ ተናግሮት፣ ግን ለገዛ ፈቃዱ ያልሮጠ ማን ነው? እኔም ጲላጦስ ነኝ! ጸጋውን በዝቶ መለሰኝ እንጂ። ጌታ ጸጋውን ያብዛልን! 

“የሁላችን ድርሻ ተጠራቅሞ ነው ውጤት ያመጣነው”

ዘላላም አበበ በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስትያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማኅበር (ኢቫሱ) ውስጥ ለረጅም ዓመታት አገልግሏል፡፡ ለአራት ዓመታት በደቡብ አካባቢ የኢቫሱ ቢሮ በሙሉ ጊዜ አገልጋይነትና የአካባቢው ቢሮ አስተባባሪ በመሆንና ከ1996 ዓ.ም. እስከ 2007 ዓ.ም. ለዘጠኝ ዓመታት ደግሞ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ በመሆን አገልግሎ በቅርቡ በራሱ ፈቃድ የዋና ጸሐፊነት ሥራውን አስረክቧል። ወንድም ዘላለም በትምህርት ዝግጅቱ ከአዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ እርሻ ኮሌጅ በእርሻ ሥራ እንዲሁም ከኢቫንጄሊካል ቲዮሎጅካል ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪውን በነገረ መለኮት ያግኝቷል። ዘላለም በአሁኑ ሰዓት አሜርካን አገር በሚገኘው Gorden Conwell Theological Seminary በሥነ አመራር የድኅረ ምረቃ ትምህርት በመመላለስ እየተከታተለ ይገኛል፡፡ በኢቫሱ ውስጥ በነበረው አገልግሎቱና በተያያዙ ጉዳዮች አስናቀ እንድርያስ ከዘላለም አበበ ጋር ያደረገው ቆይታ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

የሴራ አስተሳሰብ የጠፈረን እኛ!

አገራችን አሁን ያለችበትን ፖለቲካዊ ኹኔታ አስጊ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ የሴራ ትርክት በአየሩ ላይ መናኘቱ እንደ ሆነ ይህ የሰሎሞን ጥላሁን ጽሑፍ እያሳሰበ ተጨባጭ ምክንያታዎነት መድረኩን እንዲረከበ ጥሪ ያደርጋል።

ተጨማሪ ያንብቡ

የማይናወጥ ሐሴት

“እግዚአብሔር አምላክህከጓደኞችህ ይልቅበደስታ ዘይት ቀባህ፥”ዕብራውያን 1፥9 “መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ …ወደ ጌታህ ደስታ ግባ:”ማቴዎስ 25፥21 የማይናወጥ ሐሴትየኢየሱስ ክርስቶስ ደስታትርጕም በአማረ ታቦር ከከፋ አደጋ ያዳኖት

ተጨማሪ ያንብቡ

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.