
“ማን ኦፍ ጋድ” መባል ያማራት ነፍስ
” ‘ማን ኦፍ ጋድ መባል አማረኝ’ አለ … ቲቪ ላይ ማፍጠጥ፣ ኮት በሰደሪያ መልበስ፣ ጸጉሩን እንደ አክሱም ሐውልት ማቆም፣ ድምፁን ማጎርነንና መንጎራደድ አብዝቶ ነበረና፡፡” አስናቀ እንድሪያስ ይህን የምኞት ጉዞ እንዲህ ያስቃኘናል።
[the_ad_group id=”107″]
በዚህች አጭር መጣጥፍ እስራኤልን እስራኤል ስላደረገች እናት ለማየት እንሞክራለን። እስራኤላውያን ጠንካራ ሕዝቦች ናቸው። በየቀኑ በዜና ስለ እነሱ ሳንሰማ ማደር አንችልም። አባታቸው ያዕቆብ እግዚአብሔር በሚገርም መልኩ መርጦ የታላቅ ወንድሙ የዔሳው የበላይ ያደረው የእግዚአብሔር ሰው ነበር።
የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን የያዕቆብ አባት ይስሐቅ ርብቃን ያገኛት በእግዚአብሔር ምሪት ነበር። አብርሃም የታመነ ባሪያውን ለልጁ ሚስት እንዲያመጣለት ሲልከው የመጨረሻ ማሰሪያ ንግግሩ ʻአምላኬ መልአኩን ስለሚልክ ነገር ሁሉ ይቀናልሃልʼ የሚል ነበር። እንደተባለውም ርብቃን ውሃ ልትቀዳ ስትመጣ አገኛት። እናንተዬ፤ ውሃን ውሃ ያነሣዋል። ርብቃ ውሃ ዳር ተገኘች። ራሔልም ውሃ ልትቀዳ ብትመጣ ውሃ አጣጭዋን አገኘችው። ታላቁ ነቢይ ሙሴም ሚስቱን ያገኘው በውሃ ዳር ነበር። እንዴት ነው ነገሩ? ታዲያ ʻየእኅት ያለህ!ʼ ለምትሉ ወንድሞች ውሃ ዳር አትጥፉ ልበል እንዴ?! የአዲስ አበባ ወንድሞች ግን የቦኖ ውሃ ነው መሰል ያላችሁ።
ወደ ነገሬ ስመለስ፣ ርብቃ በአንድ ቀን ታጨች፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማዘግየት ካልነበራት ጽኑ ፍላጎት የተነሣ በማግስቱ ከማታውቀው ከአብርሃም ሎሌ ጋር ወደ ከነዓን ምድር ለመምጣት አልዘገየችም። ይስሐቅ በፍቅሯ ተሸንፎ የእናቱን ኀዘን ለመርሳትም ጊዜ አልወሰደበትም። ምን ዐይነት ድንቅ ሴት ብትሆን ነው የእናቱን ኀዘን፣ ያውም እንደ ዐፄ ቴዎድሮስ አንድ ለእናቱ ለሆነ ልጅ ኀዘኑን በአጭር ጊዜ ያስረሳችው። የእግዚአብሔር ፈቃድ ስለነበረበት ልቡን ወዲያው በደስታ ሞላችው።
ጋብቻቸው ግን ወዲያውኑ በልጅ የታጀበ አልነበረም። ጥናቶች ያመለክታሉ ብለው የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ከተጋቡ ጥንዶች ውስጥ ከ80 በላይ የሚሆኑት በዓመቱ ልጃቸውን ይታቀፋሉ። አሁን ይኑር አይኑር አላውቅም እንጂ ከሰርግ ዘፈኖች አንዱ “የዛሬ ዓመት የማሙሽ አባት…” የሚል ስንኝ ነበረው። እነ ርብቃ ግን በዚህ የታደሉ አልነበሩም። ነገሩ ጭንቅ ቢሆንበት ይስሐቅ ወደ እግዚአብሔር ስለ ሚስቱ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ልመናውን ሰማ፤ ርብቃም አረገዘች። ማርገዟስ ባልከፋ ነገር ግን የሆዷ ውስጥ ትግል ሊያሳብዳት ደረሰ። ነገሩ የጸሎት መልስ ሆኖ ከእግዚአብሔር ትቀበለው እንጂ መከራው ግን የምትችለው አልነበረም። እናንተዬ፤ ከእግዚአብሔር የምንቀበለውም ነገር ቢሆን ከበድ ይላል ማለት ነው እንዴ? ሌላው ባሏን ʻምን መዐት አመጣህብኝ፤ ጉድ ሠራኸኝʼም የሚል ቃል አልወጣትም። ርብቃ ናታ! ቀጥታ ያደረገችው ነገር ቢኖር ሰጪውን አካል መጠየቅ ነበር። ማሕፀኗ ውስጥ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ እንደሆነና አሸናፊው ግን ታናሽየው እንደ ሆነ እግዚአብሔር ነገራት። ʻለምን እንዲህ ይሆናል?ʼ ብሎ መጠየቅም ሆነ ከእግዚአብሔር ሐሳብ ጋር መጣላት የለም። ርብቃ ናታ!
ታጋዮቹ ተወለዱ። ታላቁ በጠጉር ተከቦ ሲወጣ ታናሽየውም ይቅርታ እየጠየቀ በሚመስል መልኩ የታላቁን ተረከዝ ታቅፎ ወጣ። ኑሮ ከማሕፀን ውጪም ተጀመረ። ዔሳው አዳኝ ነው፤ በረሓ እየወረደ፣ እያደነ እንስሳትን ያመጣል። ይስሐቅ ሆዬ እየታደነ የሚመጣው የድኩላ፣ የሚዳቋም ሆነ የሌሎች እንስሳትን ሥጋ ጥሞታልና ዔሳውን ይወደዋል። አይ ይስሐቅ፤ በሆድ ይደለላል። ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወደዋለች፤ ጭምት ነው። መቼም ዔሳው ካመጣው ሳትበላ ቀርታ አይመስለኝም፤ ለሆዷ አለማደሯ ይሆን ወይስ ቀደም ተብሎ የተነገራት መልእክት? መንግሥተ ሰማይ ያገኘኋት ቀን የምጠይቃት የመጀመሪያ ጥያቄዬ ይሆናል።
ዔሳው እንስሳ ማደን የተሳካለት ቢሆንም ቅሉ እኅት ላይግንደካማነው።ስለወንድሙብሎይሁንወይም አዳኝነቱ ያስተማረው ነገር ሁለት ሚስቶችን አገባ። አብርሃም ሁለት ሚስቶች በአንዴ አልነበረውም። አባቱ ይስሐቅም ያለ አንዲት ሴት በዕድሜ ዘመኑ አላገባም። ዔሳው ግን በዚህ “ፈር” ቀዳጅ ነበር። የሚገርመው ግን ይስሐቅ ዝም ማለቱ ነው። አባቱʼኮ ርብቃን አገር አቋርጦ አንዲያገባት ያደረገው ከነዓን ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሴት እጥረት በመኖሩ አልነበረም። ታዲያ የአብርሃም የልጅ ልጅ እንዲህ በማድረግ እነ ዮዲትን (“ዮዲት” ማለት ይሁዲት ማለት ነው) ሲያገባ ምነው ዝም ማለቱ። የዔሳው ሚስቶች እንደባላቸው እያደኑ ዝል ዝል ጥብስ ባያበሏቸውም የነ ይስሐቅን ጨጓራ በማድበን ግን ወደር አልነበራቸውም። ያዕቆብ የዔሳው እኩያ ነው። ወንድሙ ሁለት ሚስት ሁሉ ሲኖረው እሱ ግን አንድ ለማግባት የማይጥር፣ ፈዛዛ ቢጤ ይመስላል።
ይስሐቅ እርጅና ቤቱን ሲሠራበትና ዐይኖቹ ከማየት ሲደክሙ ሞት አንድ እግሩን እንዳስገባ በገባው ጊዜ አዳኙ ዔሳውን ጠራው። ሊባርከው ስለፈለገም ከአደኑ ክሽን ያለ ምግብ ሠርቶ እንዲያመጣለትና ሆዱን እንዲሞላ፣ ከዚያም በሆዱ ውስጥ ያለውን በረከት ሊሰጠው ዐሰበ። በዚህ ጊዜ ነበር ርብቃ ይህ ነው የማይባል ከፍተኛ ሚና የተጫወተችው። አገር ሰላም ብሎ ያለው ያዕቆብን ጠርታ አባቱ ሊያደርግ ያለውን ነገር አረዳቸው። እንደ እውነቱ ቢሆን ይስሐቅ ማድረግ የነበረበት ልጆቹን ሰብስቦ መባረክ ነበር (ይህንን ያዕቆብ በዕድሜው ፍጻሜ ላይ አድርጎታል)፤ ያዕቆብ ግን ያለው ዕድል በእናቱ ምሪት መሄድ ነበር። ከዚህ በፊት፣ ብኩርናን ክሽን ባለች ምስር ከዔሳው ተቀብሏል። አሁን ግን ከፊቱ ያለውን በረከት በተመሳሳይ ዋጋ ማግኘት አይችልም። ዕድሜ ለብልኅ እናቱ ይሁንና አባቱን አታሎ በረከትን ማግኘት ቻለ።
ባሏ ሊያነሣቸው የሚችላቸውን የማንነት ጥያቄዎች በአግባቡ የሚመልሱ መታወቂያዎችን ከሰጠችው በኋላ ይስሐቅን ቢተኛ እንኳን ከእንቅልፉ ሊያነቃው የሚችል መዓዛ ያለውን ምግብ አሸክማ ላከችው። ያዕቆብ ድመት የገደለ ይመስል እጁ እየተንቀጠቀጠ ወደ አባቱ ቀረበ። አባቱ አደን ለማደን የሚፈጀውን ጊዜ በማስላት ልምዱ ከፍተኛ ነበርና እንዴት ፈጠንክ የሚል ጥያቄ አቀረበ። ያዕቆብ ሆዬ አምላክህ ረዳኝ ብሎ እርፍ (የጌታ አምላክህን
ስም በከንቱ አትጥራ የሚለውን ትዕዛዝ የት ያውቀዋል?!)። እግዚአብሔር፣ ወጣት በነበረ ጊዜ ለአባቱ አገልጋይ መንገዱን እንዳቀና ዛሬ በዘመኑ መጨረሻ ደግሞ ለልጁ አደን እንስሳን በማምጣት የረዳው ሳይመስለው አልቀረም። ነገር ግን ጥርጣሬውን ሙሉ ለሙሉ የተቀረፈ አልነበረም። ስለዚህ ና ሳመኝ አለው። ርብቃ ያልታጠበውን የዔሳው ልብስ ከየት እንዳመጣችው አይታወቅም። ይሄኔ እኮ እነዚህ ዐመለ ቢስ ሴቶች የባላቸውንም ልብስ የማያጥቡ ጉደኞች ሳይሆኑ አይቀሩም። ዔሳው ገላው ጠጉራም ስለ ነበር ቆዳውንም ሳይቀር መረመረ፤ ነገር ግን ተጨባጭ ማስረጃ አላገኘም። መረጃም ማስረጃም የሌለው ጉዳይ ነው። ሰው መረጃ እያለው ማስረጃ አጥቶ ሳይከሰስ በሚኖርባት ዓለም፣ ሁለቱም ከሌሉ ጥፋተኛ ነህ የሚባልበት ምክንያት የለም። የምግቡ ሽታ ልቡን ነሥቶት ሌላ ተጨማሪ መረጃ አጥቶ በድምፅ ጥርጣሬ ብቻ ጊዜውን የሚያባክንበት ምክንያት ስላልነበረ የቀረበውን ምግብ እንዳይሆን አድርጎ በረከት የሚባል ነገር ሳያስቀር ለያዕቆብ ሰጥቶ ሰደደው። ዔሳው አገር ሰላም ብሎ በረከት ፍለጋ ቢገባ ይስሐቅ የጠገበ ሆዱን እያሻሸ ወደ እንቅልፍ እየተንደረደረ የነበረ ይመስል ነበር። አዳኙ ወንድሙ ያደረገበትን ሲሰማ አበደ። እናቱ ግን ከመጋረጃው ጀርባ እንዳለች ያወቀ አይመስልም። ሼባው ሊደይም ስለሆነ ያኔ ዘላቂ መፍትሔ እሰጠዋለሁ አለ። እናቱን የማክበር ሐሳብ ያለው አይመስልም። ወይ ሚስቶቹ ጠምዝዘውት ይሆናል?! “አማትና ምራት ተያይዘው መሬት” እንዲል አበሻ።
ያዕቆብ በእናቱ ምክር ተስቦ በረከትን ከአባቱ ቢያገኘም፣ የሞት አዋጅ ከታናሽ ወንድሙ (ከምስር ወጡ በኋላ ታላቅነቱ የሱ ነው) እንደሚመጣበት ያሰበ አይመስልም። ርብቃ በዚህ ጊዜ ወደ ወንድሟ ወደ ላባ ቤት እንደምትልከው ነገረችው፤ ነገር ግን እንዴት?ʼ የሚለው ጥያቄ ምላሽ ያላገኘ ይመስላል። ርብቃ ይስሐቅ ዘንድ ሄዳ ያዕቆብ የዚህ አገር ልጆችን እንዲያገባ አልፈልግም፤ ልጁን አንድ በልልኝ አለችው። ብልኀት ይሏል ይኼ ነው። ይስሐቅ ሆዬ ሐሳቡን እሱ ያፈለቀ በሚመስል ሁኔታ ወደ እናትህ ዘመዶች ሂድ ብሎ ባርኮ ሸኘው። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ አትሉም። ልጇን ከሞት መታደጉ ቀዳሚው ሲሆን፣ በትዳር ከከነዓን ሴቶችም ጋር እንዳይጠላለፍ ማድረጉ ተከታዩ ነበር።
ያደረገችውን ዐስቡት፡- ያዕቆብን ወደ በረከት አመጣችው፤ ከሞት አተረፈችው፤ ውሃ አጣጪውን ከትክክለኛ ቦታ እንዲያገኝ መራችው። እናት ይሏል ርብቃ ናት። እስራኤል በእናቴ እዚህ ደረስኩ ይበል። አስደማሚው ነገር ያዕቆብ ሲሞት የተቀበረው ከእናቱ ጎን መሆኑ ነው። ዛሬም በዘመናችን ልጆቻቸውን ከሞት ታድገው የወንጌል ዐርበኛ የሚያደርጉ እናቶች ያስፈልጋሉ። ሱዛና እንደነዚህ ካሉ እናቶች መካከል አንዷ ናት። ምንም እንኳን የእነ ያዕቆብ ያህል ብርቱ ነኝ ባልልም፣ (መቼም እንደማልሆንም አውቃለሁ) ነገር ግን በክርስትና ሕይወቴ በእጅጉ ተጽእኖ የፈጠረችብኝ እናቴ ናት። እንደ እርሷ ልጆቻቸውን በእግዚአብሔር ቤት ተክለው እንዲኖሩ የሚያደርጉ እናቶች እግዚአብሔር ደግሞ ደጋግሞ ይስጠን።
Share this article:
” ‘ማን ኦፍ ጋድ መባል አማረኝ’ አለ … ቲቪ ላይ ማፍጠጥ፣ ኮት በሰደሪያ መልበስ፣ ጸጉሩን እንደ አክሱም ሐውልት ማቆም፣ ድምፁን ማጎርነንና መንጎራደድ አብዝቶ ነበረና፡፡” አስናቀ እንድሪያስ ይህን የምኞት ጉዞ እንዲህ ያስቃኘናል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቴሌቪዥን መስኮት ብቻ እናውቃቸው የነበሩ አንዳንድ አፍሪካውያን “አገልጋዮች” በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ መታየት ጀምረዋል። በቅርቡ የተከሰቱ ሁለት ኩነቶችን እንኳ ብንመለከት “ሜጀር ሼፐርድ ፕሮፌት” ቡሽር ከማላዊ፣ “ነቢይ” ኮቦስ ቫን ሬንስበርግ ከደቡብ አፍርካ ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ልብ ይሏል።
“አንዱ በብሔሩ ዘረኛ ሲሆን፣ ሌላኛው በዜግነቱ ዘረኛ ይሆናል። አንዱ ብሔሩን ሲያስቀድም፣ ሌላኛው ዜግነቱን ያስቀድማል። አንዱ የብሔር ዘረኛ የራሱን ብሔር ለብቻው ሊያገንን ሲፈልግ፣ ለኢትዮጵያ ዐብሮነት መሠረት ውጋት ይሆናል። እንደዚሁም የዜግነት ዘረኛ ኢትዮጵያን ለብቻዋ እንድትገን ሲፈልግ፣ በጨለማ ላለ ጥቁር አፍሪካ ሕዝብ አንድነት ውጋት ይሆናል።
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.
Add comment