[the_ad_group id=”107″]

ዕረፉ!

Photo credit: Abinet Teshome

“ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።” መዝሙር 46፥10

ሰው የራሱን ሕይወት ሳይቀር፣ ‘እኔ’ ወይም ‘የእኔ’ ብሎ፣ ምንም ነገር ሊቈጥር እንዳይችል አፈጣጠሩ ይገድበዋል፤ በፈቃዱና በዕውቀቱ አልተፈጠረምና። የተፈጠረው ሁሉ በእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ፣ ለራሱ ለእግዚአብሔር ክብር ተፈጥሯል (ሮሜ 11፥36)።

ከተፈጠረውም ሁሉ በእግዚአብሔር አምሳልና መልክ የተፈጠረው የሰው ልጅ ይልቃል፤ ለዐብሮነትና ለፍቅር ተፈጥሯልና (ዘፍጥረት 1፥26-27)።

ፍጹም ደስታ፣ ከሁኔታ በላይ የሆነ ሰላምና እውነተኛ መከናወን ያለው በእርሱ ፈቃድ ውስጥ ለተገኘ ሰው ነው። 

ሰው እግዚአብሔርን በማወቅ ውስጥ ብቻ ሊገኝ የሚችለውን ማንነቱን ካለገኘ፣ በመላ ምት ኗሪ፣ ብኵንና ተቅበዝባዥ ምስኪን ፍጥረት ነው። በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ እርሱም በሰጠው ችሎታ ተመራምሮ የደረሰባቸው በርካታ ነገሮች ቢኖሩም፣ ዘላለማዊ ፋይዳ ያለው የሕይወት ትርጕም ላይ የሚደርሰው፣ የእግዚአብሔር ብርሃን ባገኘው ጊዜ ብቻ ነው።

ሰው፣ ሰው መሆኑን የሚያውቀው፣ ሰውን ሰው የሚያረገውንና ፍጹም ሰው የሆነውን፣ ፍጹም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን ባገኘ ጊዜ ነው። የሰው ዕረፍት ያለው በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ነው። ፍጹም ደስታ፣ ከሁኔታ በላይ የሆነ ሰላምና እውነተኛ መከናወን ያለው በእርሱ ፈቃድ ውስጥ ለተገኘ ሰው ነው። ከሁሉ አስቀድሞ፣ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኙና ወደ ዕረፍቱ እንዲገቡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው (ሮሜ 12፥2፤ ዮሐንስ 6፥40፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥4፤ ዕብራውያን 4፥3)።

እኔነት ባለበት ዕረፍት የለም፤ አንጻራዊ ትሕትናም እውነተኛ ዕረፍትን አይሰጥም።

ይህን እውነት፣ ይህች እኅታችሁ ትመሰክራለች። ጥልቅና ረቂቅ መስሎ በሚያታልል ጉረኛ ጥበብ፣ ራሷን ስትሞላና ልትሞላም ስትጣጣር የኖረች ታናሻችሁ ትናገራለች (1 ቆሮንቶስ 1፥20-21)፤ እውነትንም ፍለጋ እጅግ ባክናለች። ለነፍሷም ዕረፍትን ስታስስ በብዙ ተንከራትታለች። ከባድና ሩቅ ነገርን ጠብቃ፣ ቀላልና ቅርብ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ዕረፍቷን ያገኘች ታናሻችሁ ትመሰክራለች። መልሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ቀላልና ቅርብ የሆነው የኢየሱስ ሕይወት በርግጥ ቀላልና ቅርብ ሆኖ ሳይሆን፣ ከብርቱ ፍቅሩ የተነሣ ከእርሱ ክብር ርቀንና ጎድለን ለኖርነው የሰው ልጆች እናገኘው ዘንድ፣ ቀልሎና ቀርቦ ስለ መጣልን ነው (ፊልጵስዩስ 2፥6-8)። እርሱ ለነገር ሁሉ ትርጕምን፣ ለነፍስም ዕረፍትን እንደሚሰጥ እኔ እመሰክራለሁ። ዐድሎኝ ስላገኝሁት እመሰክራለሁ። ኢየሱስ ዕረፍት ነው።

በእኔነት መንደር ለኖርነው ምስኪኖች፣ ከምስኪንነታችን ጋር አስተዋውቆን፣ ቀሊል የሆነውን የእርሱን ቀንበር አሸክሞ አሳርፎናል።

እርሱ በእኔነት መንደር፣ በራስ አስተያየት ጥበበኛ በመሆን ጎዳና፣ ‘በእኔ መንገድ’ ብለን በሞገትነው ሳይሆን፣ በትሕትና ጥበብ፣ በራሱ መንገድ ላይ ብቻ እንደሚኖር አስተምሮናል። በእኔነት መንደር ለኖርነው ምስኪኖች፣ ከምስኪንነታችን ጋር አስተዋውቆን፣ ቀሊል የሆነውን የእርሱን ቀንበር አሸክሞ አሳርፎናል።

እኔነት ባለበት ዕረፍት የለም፤ አንጻራዊ ትሕትናም እውነተኛ ዕረፍትን አይሰጥም። ሰው ዐፈር እንደ ሆነ በማወቁ ትሕትና ብቻ አያርፍም። ከዐፈርነቱ ባሻገር፣ ሰው የመሆኑን ምስጢርና ሊያርፍበት የሚገባውን የደኅንነት ቦታ በእምነት በማወቁ ያርፋል እንጂ። ይህም ቦታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ሕይወትህን ካበጃት በላይ ማን ይበጃታል? ከሠራንስ በላይ ማን ያውቀናል? ስለ እኛ ለማወቅ፣ በዚያም ዕውቀት ልንሆን የሚገባንን ለማስተዋል ወደ እግዚአብሔር እንዙር። ፈጣሪ አምላካችንን ዕናውቀው ዘንድ በውስጣችን ረኻብን፣ በፍጥረቱ ሁሉ ምስክርን አኑሮ ዘወትር ያነጋግረናል።

ሕይወትህን ካበጃት በላይ ማን ይበጃታል? ከሠራንስ በላይ ማን ያውቀናል? ስለ እኛ ለማወቅ፣ በዚያም ዕውቀት ልንሆን የሚገባንን ለማስተዋል ወደ እግዚአብሔር እንዙር።

‘ዕሺ’ ብንለው ራሱን ሊገልጥልን አለ። ሊያውቁት ለሚወድዱ ሁሉ ቅዱስ ቃሉን ሰጥቶናል። ቃሉ የጸናና የማይሻር የእግዚአብሔር ዐሳብ ነውና እናምነው ዘንድ፣ አምነንም እናውቀው ዘንድ ከቃሉ እንስማ። በቃሉ ውስጥ የምናርፍበትን የፈቃዱን ዕውቀት እንገነዘባለን፤ የምንገዛለትን ሰላም የሞላው የሕይወት መርሕ እናገኛለን። የተደረገልንን ዐውቀን የሚገባውን እናመልካለን። የመታዘዝን ብልሃት ተምረን በዚያ ለዘላለም እንጠበቃለን።

‘ወደ እኔ ኑ፤ ላሳርፋችሁ’ የሚለው ጌታ በርግጥ ያሳርፋል። ወደ እርሱ ኑ፤ በኢየሱስ ዕረፉ። አምላክ ክብሩን መግለጥ፣ ባሕርዩን አብዝቶ ማሳየት በፈለገ ጊዜ ሰው ተፈጥሯል። እርሱ ባለበት እንዲሆን፣ እንዲመስለውና እንዲያመልከው ፈጥሮታልና ያንን ማድረግ በቻለ ጊዜ ብቻ ያርፋል፤ እውነተኛና ዘላቂ ርካታንም ያውቃል።

“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለው። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና፥ ለነፍሳችሁ ዕረፍትን ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።” (ማቴዎስ 11፥28-30)

እምነታችን ሲፈተሽ

የእምነትን አመለካከት በሁለት አቅጣጫ ዐጠር ባለ ሁኔታ እንመልከት። ይህም አንደኛ፤ እምነትን ለግል ኑሮ የምንጠቀምበት አግባብና፣ ሁለተኛ እምነትን ለመንግሥቱ የምንጠቀምበት አግባብ ነው።  እምነት ለግል ኑሮ በግል

ተጨማሪ ያንብቡ

የጸሎት ኀይል ለአእምሮ ተሓድሶና ለውጥ

እግዚአብሔርን ያስደነቀና ያስገረመ ነገር ካለ በርግጥም አስገራሚና አስደማሚ ጕዳይ ነው። የእግዚአብሔር ቃል በኢሳያስ 56፥19 ላይ እንዲህ ይላል፡- “ሰውም እንደሌለ አየ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም …”፡፡ እግዚአብሔር በምንም የማይገረምና የማይደነቅ አምላክ ነው። ታድያ በሰው ልጆች አለመጸለይና አለመማለድ ስለ ምን ይሆን የተደነቀው? የምር ልብ ብለን ብናየው እርሱን ያስደነቀ ነገር እውነትም ድንቅ ነው። በጸሎት ውስጥ ያለው ኀይል ወሰን የማይገኝለት ነው፤ አምሳያም የሌለው ነው። ፀሓይንና ጨረቃን በስፍራቸው ያቆመና ባህርን ከፍሎ እንደ ግድግዳ ያቆመ ኀይል ከጸሎት ውጪ ከየት ሊያገኝ ይችላል? ሙታንን ማስነሣትና አጋንንትን ማስወጣት የሚችል ጉልበት በየትኛውም የምርምር ጣቢያና ዩኒቨርስቲ ውስጥ እንዳለ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አልተሰማም። መናን ከሰማይ የሚያወርድና ውሃን ከዐለት ለማፍለቅ የሚችል ኀይል በታሪክ ውስጥ አልተመዘገበም። ጸሎት ለደካማ ሰዎች የተሰጠ ብርቱ መለኮታዊ ክንድ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ

16 comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

      • You write nothing. You just simply copy paste verses from the Bible. This indicated that you don’t even understand that Bible is word of God and requires spiritual tendency to grasp the messages of each verse. No matter you tried, you added no value in clarifying the message you want to deliver to you audience. It is better to read and grasp it message before you re-write the Bible. My God! Dear readers I would honestly would like to suggest you to read the Bible than such pieces of misleading verses. Dear writer, I would also like to advise you that please get in to a theology school of your respective religion (if they have) and look back to your “article”. May God give you the wisdom that you pretending. Amen!

  • Totally agree with you and looking forward to to read your next article. Please Keep on writing us your understanding my sister.

  • በጣም ደስ የሚል ግሩም መልዕክት
    እህቴ ተባረኪልኝ። በእውነትም ኢየሱስ ፍፁም ዕረፍታችን እና የዘላለም ታዛችን ነው።

    ፀጋ ይብዛልሽ!🙏

  • “ለነፍሷም ዕረፍትን ስታስስ በብዙ ተንከራትታለች። ከባድና ሩቅ ነገርን ጠብቃ፣ ቀላልና ቅርብ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ዕረፍቷን ያገኘች …”
    I like this

  • I Follow. u and go on…so many things happen in our generation coz of JESUS, so i appreciate your determination.

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.