ሙስና እና አማኝ ማኅበረ ሰቡ፦ ዐጭር የዳሰሳ መጠይቅ ዘገባ
ሙስና በአማኝ ማኅበረ ሰቡ ላይ እያሳደረ ያለውን ተጽእኖ ለመመዘን በሚል ሕንጸት የሠራውን የዳሰሳ ጥናት ሙሉውን ሪፖርት ያንብቡ።
[the_ad_group id=”107″]
የሥነ መለኮት ጥናት በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያን አጭር ዕድሜ ያለው ነው፡፡ የዕድሜው ዕጥረት ከወንጌላውያን ክርስትና አጀማመር ጋር የራሱ ቁርኝት አለው፡፡ የአብያተ ክርስቲያናቱ የቆይታ ዘመን በአንጻራዊነት ከታየ አጭር የሚባል ነውና፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በርካታ ቤተ ክርስቲያናት፣ አጋር ቤተ ክርስቲያናትና ግለ ሰቦች የመጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤቶችን መክፈት ጀምረዋል፡፡ በመሠረቱ ይህን መሰሉ ጥረት ሊበረታታ ይገባል እንላለን፡፡ ይሁን እንጂ ጥረቱን ማበረታታት እንዳለ ሆኖ ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ እነዚህ ጉዳዮች በዋናነት ከትምህርት ጥራት ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡
ሰዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ሥነ መለኮትን መማር የሚፈልጉበት ጊዜ ላይ ናቸው፤ ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ የሰዎች የተለያዩ ምክንያቶች ግን በትምህርት ጥራቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያመጣ መጨነቅ ያስፈልጋል፡፡ አንዳንዶች፣ ቤተ ክርስቲያናት ለአገልግሎት “እርከን” ዕድገትም ይሁን አገልጋዮችን ተቀብሎ ለማሰማራት የሥነ መለኮት ምሩቃን የሆኑትን የሚፈልጉበት ጊዜ ከመሆኑ የተነሣ፣ “ወረቀት” (ዲግሪ) ፍለጋ ይመጣሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ብዙ ጊዜ የትምህርት ጥራቱ አያሳስባቸውም፤ እንደውም ትምህርቱ እንዲከብድና ጥራቱ እንዲጠበቅ የማይፈልጉበት ጊዜ ይበዛል፡፡ ታዲያ ት/ቤቶች ገበያውን በማሰብ ብቻ “ዲግሪ መቸብቸብ” ሥራቸውን ካደረጉ ለመሰል ግለ ሰቦች ጊዜያዊ ፍላጎት መንበርከክ ግድ ይላቸዋል፡፡
በተመሳሳይም ት/ቤቶቹም ጊዜያዊ ጥቅምን በማሰብ ብቻ ከተቋቋሙ ወይም የግባቸው መዳረሻ ገንዘብ ማግኘት ከሆነ ችግሩ የጎላና የገዘፈ ይሆናል፡፡ ከአቅማቸው በላይ በሆነ ሁኔታ ተማሪዎችን ለከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ሲያጩ የሙያ ሥነ ምግባርም ሆነ የኅሊና ወቀሳ የማይሰማቸው አሉ፡፡ ለድኅረ ምረቃ ይቅርና ለሠርተፊኬትና ለዲፕሎም መርኀ ግብሮች በቂ ተቋማዊ ዝግጅቱና አቅሙ የሌላቸው “ት/ቤቶች” በዶክትሬት ማዕረግ እንደሚያስመርቁ ያስታውቃሉ፡፡ የትምህርት ጥራቱን ማረጋገጥ ከማይቻል የውጪ ተቋም ጋር አብረው እንደሚሠሩ፣ ዲግሪውም ከውጪ እንደሚመጣ በመንገር የተማሪዎችን ልብ ያማልላሉ፡፡ በመርሕ ደረጃ ማንኛውም ትምህርት ከንግድ ያለፈ ዓላማ አለው፤ የሃይምኖት ትምህርት ሲሆን ደግሞ ኀላፊነቱ በዚያው መጠን ከፍ ይላል፡፡ ስለሆነም እንዲህ ያሉ ት/ቤቶች ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚችልበት አሠራር መዝርጋት አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ፣ የኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ተቋማት ማኅበር የጀመረው ጥረት ሊበረታታና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው እንደ ሆነ ሳንጠቁም አናልፍም፡፡
በሌላ በኩል የሥነ መለኮት ተማሪዎች በፍጹም ጥንቃቄና ኀላፊነት ስሜት ሊማሩ ይገባቸዋል፤ ሲሚዎቻቸውን ወደ ትክክለኛው የሕይወት ጎዳና ለመምራት ትልቅ ዐደራ የተጣለባቸው ናቸውና፡፡ የሚሰማሩበት መስክ የሰው ሕይወት ነው፤ የሚያገለግሉት የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ስለሆነም ተጠያቂነቱ በሰውም በአምላክም ፊት መሆኑ አይቀረም፡፡ ተማሪዎች ለምን እንደሚማሩና እንዴት መማር እንዳለባቸው የማወቅ ትልቅ ኀላፊነት አለባቸው፡፡
በቤተ እምነት የሚተዳደሩ የሥነ መለኮት ተቋማት ለትምህርት ጥራት፣ ለተቋማዊነትና ለዐውዳዊነት ትልቅ ስፍራ ሊሰጡ ይገባቸዋል፡፡ ትምህርት ቤቶቹ የሚያስተምሯቸው ተማሪዎች የቤተ እምነቱን ከዚያም ሲያልፍ የአማኝ ማኅበረ ሰቡንና የአገርን ጥያቄ በአቅማቸው የሚመልሱ መሆናቸውን ሁሌም ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡ የሥነ መለኮት ተቋማቱን እንደ ዋና የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት አካል መቁጠርና አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ የቤተ እምነቶቹ ኀላፊነት ነው ብለን እናምናለን፡፡
በእንጭጭ ደረጃ ላይ ያለው የሥነ መለኮት ትምህርት ሥር ሰድዶ የበለጠ እንዲያብብ የሚመለከታቸው ሁሉ ኀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡

Share this article:
ሙስና በአማኝ ማኅበረ ሰቡ ላይ እያሳደረ ያለውን ተጽእኖ ለመመዘን በሚል ሕንጸት የሠራውን የዳሰሳ ጥናት ሙሉውን ሪፖርት ያንብቡ።
ጌታችን ስለ ሰው ልጆች የከፈለውን ዋጋ በምናስብበት በሰሙነ ሕማማት፣ ንጉሤ ቡልቻ “እንዴት እንሙት?” የሚል ጥያቄ ይጠይቃሉ። ምላሹ በክርስቶስ ሞት ውስጥ የቀረልን ትልቅ ትምህርት ሆኖ አለ።
አገኘሁ ይደግ በኢትዮጵያ የወንጌላውያን አማኞች የዝማሬ አገልግሎት ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚነሡ ዘማሪያን መካከል የሚጠቀስ ነው። ዘመን ዘለቅ በሆኑት ዝማሬዎቹም ብዙዎች ተጽናንተዋል፣ ታንጸዋልም። የሕይወትን አስቸጋሪ ፈተናዎች በመቋቋም እግዚአብሔርን በጽናት ማገልገሉ ለአርኣያነት የሚያበቃው እንደ ሆነ የሚያውቁት ይናገራሉ። የዚህን ዘማሪ 25ኛ የአገልግሎትና 20ኛ የትዳር ዘመን በዓል ምክንያት በማድረግ ሕንጸት የቆይታ ዐምድ እንግዳ አድርጎታል። ጳውሎስ ፈቃዱ ከዘማሪ አገኘሁ ይደግ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው ቀርቧል።
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.

Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.
Add comment