[the_ad_group id=”107″]

ጌታን ተቀበሉ!

Photo credit: Abinet Teshome

“ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ
የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው” (ዮሐንስ 1፥12)

የወንጌል ውትድርና 

‘ወንድሜ፤ ጌታን ተቀብለሃል?̕’ ‘እኅቴ፤ ጌታን ተቀብለሻል?̕’ 

የወንጌል መልእክተኛ የሆኑ ሰዎች ይህን ጥያቄ በአንድም በሌላም ጠይቀዎት ይሆናል፤ ለምን ጌታ ያሉትን ኢየሱስ ክርስቶስን ሊቀበሉ እንደሚገባም ተነግሮዎም ይሆናል። አዎን፤ ‘ጌታን ተቀበሉ!’ የሚለውን የንስሓ ጥሪ በታማኝነት የሚያቀርቡ ትጕሃን የእግዚአብሔር መንግሥት ሠራተኞች፣ የወንጌሉ ወታደሮች በመካከላችን አሉ። 

አንዳንዶች ያለ አእምሮና ለሰዎች ባላመጠንቅቅ እንዲያው በስሜታዊነት በወንጌል ሰበካ ስም፣ ከሰላም አብሳሪነት ይልቅ አላስፈላጊ ኹከት ፈጣሪ የሚሆኑበት አጋጣሚ የለም ማለት ግን አይደለም።

እነዚህም፣ በኖህ ዘመን ሊመጣ ከነበረው ጥፋት ሰዎች ይድኑ ዘንድ እንደሰበከው ዐይነት ናቸው። በዚያን ዘመን በሰው ልጆች መክፋት ምክንያት ዐመፀኞችን ለማጥፋት እግዚአብሔር ካዘዘው የቅጣት ጎርፍ፣ ቅሬታ የሚሆኑትን ሊያድን ወዳዘጋጀው የደኅንነት መርክብ ግቡ ይል እንደ ነበረው ያሉ ናቸው። በተመሳሳይ በመጨረሻ ዘመን ሊመጣ ካለው የዘላለም ጥፋት ሊያድንን ራሱን ወደ ሰጠው፣ ወደ ኢየሱስ ክርስቶሰ በእምነት ገብተን እንድናመልጥ ነፍሳትን በወንጌል ተማጽኖ የሚያድኑ ታማኝ የሰው አጥማጆች ናቸው። “ኢየሱስም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።” (ማርቆስ 1፥17)።

በዐይኖቻቸውም ፊት የበራው ብርሃን፣ ራሱ የፈጠራቸው ጌታ በመሆኑ እርሱን አለማውራት አይችሉም። ከዚህም የተነሣ ይህን ጥሪ በልዩ ልዩ መንገድ ያለመታከት ያቀርቡታል። የሚተጕበት መሰጠት እንደ ዓለም አተያይ እጅግ ሞኝነት የሚመስል፣ ብዙ ንቀትን የሚያስከትልና የበዛን ዋጋ የሚያስከፍል ነው። ይህን ጥሪ ለማቅረብ ያስነሣቸው የግል ጥቅም ሳይሆን፣ ከውዱ ጌታቸው የተቀበሉት ዐደራና የሚያገኙት ዘላለማዊ ትርፍ ነውና  ‘ዋጋን አስከፈልን’ ብለው የሚቈሙ አይደሉም። ዋጋን ስለ ስሙ ሊከፍሉ እንደሚገባ ቀድመው የተረዱ፣ ዐውቀውም የተሰማሩ ናቸው (ማቴዎስ 10፥22፤ የሐሥ 5፥41፤ 2ኛ ጢሞ 3፥12)።

በእምነት ካለ ርግጠኝነትና ስለ እውነት ከሆነ ተጋፋጭነታቸው የተነሣ፣ በሰዎች ፊት እንደ ንክና እንደ ሥራ ፈት ተደርገው ቢቈጠሩም፣ እነርሱን የሚያሳስባቸው ከፍ ባለ ስፍራ ለብቻው ተለይቶ ያለው የጌታ አምላካቸው ዕይታ እንጂ፣ የጠፊዋ ዓለም አስተያየት አይደለም። ዓለም እነርሱን ልትገነዘብ የምትችልበት የዕውቀት ብርሃን የላትም። ይህን ስንል፣ አንዳንዶች ያለ አእምሮና ለሰዎች ባላመጠንቅቅ እንዲያው በስሜታዊነት በወንጌል ሰበካ ስም፣ ከሰላም አብሳሪነት ይልቅ አላስፈላጊ ኹከት ፈጣሪ የሚሆኑበት አጋጣሚ የለም ማለት ግን አይደለም። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በጥበብና በፍቅር፣ በትሕትና፣ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ልንሰብከው የሚገባ ነው።  

ወንጌል ጥበበኞችና አዋቂዎች ነን ለሚሉ ብዙዎች ከተራ ወሬና ከተረት ተረት ለይተው ሊያዩት የሚችሉት ነገርም አይደለም፤ ይህም እግዚአብሔር የምድርን ሊቃውንትና ተራቃቂዎችን ሳይሆን፣ በስብከት ሞኝነት መንግሥቱን እንደ ሕፃን ሊቀበሏት ለሚችሉት ራሱን ሊገልጥ መልካም ፈቃዱ በመሆኑ ነው።

‘አንተ ማን ነህና ነው የኔን መዳኛ የምትመነግረኝ? መዳኛው አንተ ምትሰብከው ሳይሆን እኔ የማምነው እንዳልሆነ በምን ታውቃለህ?’ እና የመሳሰሉት የተቃውሞ ምላሾች ሲቀርቡለት የወንጌለኛው መልስ፦ ̕የወደድከውን የማመን መብት እንዳለህ ባውቅም፣ በትክክለኛ መንገድ ላይ ነህ በማለት ግን ውሸትን አልነግርህም፤ እኔ እያለሁ ባለማወቅ ወደ ሲኦል አትወርድም፤ እውነት የሆነውንና የሚዳንበትን አንዱን መንገድ ስላገኘሁት ታመልጥ ዘንድ እነግርሃለው’ የሚል ነው። 

በርግጥ ሰው ሁሉ የሚያምነውን የመምረጥና ለሚያመልከው የመለየት መብት አለው። ይህን ነጻ ፈቃዱን፣ ምንም የማይፈይድለት ሥጋ ለባሽ ይቅርና፣ እስትንፋሱን የሰጠው ፈጣሪው እግዚአብሔርም አይከለክለውም። በጌታ የሆነው፣ በክርስቶስ ከእግዚአብሔር ልጆች የሚቈጠረው ሰው ግን፣ ይህን ጥሪ የማቅረብና ላላወቁት የማሳወቅ የፍቅር ግዴታ አለበት፤ ሕይወቱን ሰጥቶ ካዳነው ጌታ የተቀበለው ክቡር ተልእኮ ነውና። ሐዋርያው ጳውሎስ፣ “… ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ” (1ቆሮንቶስ 9፥16) እንዳለው፣ ወንጌልን መስበክ ደመወዝን ከላከን የምንቀበልበት ለሰዎች ሁሉ ያለብን ዕዳ፣ በዐደራ የተሰጠን የማንነት ግዴታችን ነው። “እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።” (ማርቆስ 16፥15)።

ከሃይማኖተኝነትና ለሃይማኖት ወገን ካለ ቅንዓት በላይ፣ ሰዎችን ከወንጌል የሚያሸሸው ለኀጢአትና ለዓለም ያለ ፍቅር ነው (ዮሐንስ 3፥20)። በወደቀው የሰው ማንነት ውስጥ በምቾት የሚኖረው የጨለማው መንፈስ፣ ሰዎችን ከዚህ ጥሪና ከሚከተለው መዳን በማከላከል ይቃወማል። እግዚአብሔር መዳናችንን እንደሚወድድ ሁሉ፣ መጥፋታችንን አጥብቆ የሚፈልግ ተጻራሪ የጨለማ ኀይል ለዐላማው እየሠራ በዙሪያችን አለ። ወንጌል በጨለማ እስራት ያሉትን ፈትቶ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚያሻግር የመዳን ድልድይ ነውና፣ ዜጎቹን ላለማጣት የጨለማው ገዥ በገዛው ማንነታቸው ውስጥ ሆኖ እንዳያመልጡት በመቃወምም ይሠራል (የሐሥ 26፥17-18፤ ቈላስይስ 1፥13-14)።

ከሃይማኖተኝነትና ለሃይማኖት ወገን ካለ ቅንዓት በላይ፣ ሰዎችን ከወንጌል የሚያሸሸው ለኀጢአትና ለዓለም ያለ ፍቅር ነው።

ወንጌል እግዚአብሔር አስቀድሞ የወሰናቸውን ወደ ቤታቸው የሚያስገባበት ጥሪ ነውና ሊድኑበት ለተገባቸው መልካም ዜና፣ እንዲጠፉ ለሚሆኑትም የተጠላ ድምፅ መሆኑም አይቀሬ ነው። “ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳን የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው።” (2ኛ ቆሮንቶስ 4፥3)።

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ወደ ሕይወት የመጣ ሰው ሁሉ፣ ካመለጠበት የጥፋት ጉድጓድ ሌሎችም እንዲያመልጡ ይናገራል። የሰዎችን አቋምና እምነት አክብሮ ወደ ማይወጣበት ሞት እንዲሸኛቸው የሚያስችለው ዐሮጌ ማንነት፣ በክርስቶስ ከእርሱና ከእርሷ ተወግዷልና በማይመች ሁኔታና በከፋ ምላሽ ውስጥ ሁሉ ‘ጌታን ተቀበሉ’ እያለ ይናገራል፤ ̕‘ኑ! በመዳን እኛን ምሰሉ’ በማለት ወደ ዘላለም ሕይወት ይጣራል።

የወንጌል ወታደር የታጠቀውን እውነት ለፍጥረት ሁሉ የማወጅ ግዴታ ቢኖርበትም፣ ሰዎች ያንን አድምጠው የሚወስዱት ውሳኔ የራሳቸው ነው። ወንጌል ጥበበኞችና አዋቂዎች ነን ለሚሉ ብዙዎች ከተራ ወሬና ከተረት ተረት ለይተው ሊያዩት የሚችሉት ነገርም አይደለም፤ ይህም እግዚአብሔር የምድርን ሊቃውንትና ተራቃቂዎችን ሳይሆን፣ በስብከት ሞኝነት መንግሥቱን እንደ ሕፃን ሊቀበሏት ለሚችሉት ራሱን ሊገልጥ መልካም ፈቃዱ በመሆኑ ነው። “በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገና፦ የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለገለጥክላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎ አባት ሆይ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአል።” (ሉቃስ 10፥21)፤ “በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን ስላላወቀች፣ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአበሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና።” (1ኛ ቆሮንቶስ 1፥21)።

እኔም እኅታችሁ በእግዚአብሔር ጸጋና መልካም ፈቃድ፣ የዚህ ሕይወት የሆነው ጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አብስሪነት ዕጣ ወደቀብኝ።

እኔም እኅታችሁ በእግዚአብሔር ጸጋና መልካም ፈቃድ፣ የዚህ ሕይወት የሆነው ጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አብስሪነት ዕጣ ወደቀብኝ። ይህን እውነት እንዳስተውል፣ ሞኝነት የሚመስለውን የመዳን ጥበብ ልቤን ከፍቼ እንድቀበል የረዳኝን፣ ዐውቀው ዘንድ ራሱን የገለጠልኝን ቸር አባት እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። 

“በወንጌል አላፍርም፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዚአብሔር ኀይል ነው …” (ሮሜ 1፥16 አመት)

Zeritu Kebede

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ መንግሥትና ሕዝብ ልብ ልንል የሚገባቸው ነጥቦች

ይህ ጽሑፍ ከቀናት በፊት ለንባብ የቀረበ ሲሆን፣ ዐቢይ ትኩረቱም ማኅበራዊ ንክኪን መቀነስ ላይ ያተኩራል። ጽሑፉ አነስተኛ አርትዖት ተደርጎበት ለሕንጸት አንባቢያውን እንደሚከተለው ቀርቧል።

ተጨማሪ ያንብቡ

መልካም ጅምሩ እንዳይደናቀፍ

የሥነ መለኮት ጥናት በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያን አጭር ዕድሜ ያለው ነው፡፡ የዕድሜው ዕጥረት ከወንጌላውያን ክርስትና አጀማመር ጋር የራሱ ቁርኝት አለው፡፡ የአብያተ ክርስቲያናቱ የቆይታ ዘመን በአንጻራዊነት ከታየ አጭር የሚባል ነውና፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በርካታ ቤተ ክርስቲያናት፣ አጋር ቤተ ክርስቲያናትና ግለ ሰቦች የመጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤቶችን መክፈት ጀምረዋል፡፡ በመሠረቱ ይህን መሰሉ ጥረት ሊበረታታ ይገባል እንላለን፡፡ ይሁን እንጂ ጥረቱን ማበረታታት እንዳለ ሆኖ ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ እነዚህ ጉዳዮች በዋናነት ከትምህርት ጥራት ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

እውነተኛ አገልጋይ ማነው?

የምንኖረው እጅግ በዘመነ ትውልድ ውስጥ ነው። በዘመኑ ውስጥ በዓይናችን የምናያቸውና በልቡናችን የምናስተውላቸው በርካታ ነገሮች አሉ። በተለይም በብዙ አቅጣጫ ውሸተኞች ሆነው ሳሉ ነገር ግን እውነተኛውን መስለው የሚገለጡ ነገሮችን እናስተውላለን።

ተጨማሪ ያንብቡ

36 comments

Leave a Reply to Libanos Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

  • ልታስተላልፊው ከምትፈልጊው መልክት በላይ ልትነቅፊ የፈለግሽውን አካል በፎቶ ማሳየትሽ መልክትሽ ትልቅ አንቺ ግን ምን ያህል የወረደ አስተሳሰብ ላይ እንዳለሽ ያሳያል። ይሄ ኦርቶዶክስን መጎንተል የተጠናወተሽ መንፈስ ከላይሽ ላይ ይውረድልሽ እንጂ በዚህ ሁኔታሽ ላንቺም መዳን አይኖሮም ምክንያቱም ይህ ስራ አምላኩን የሚያውቅ ሰው ስራ አይደለው። ኦርቶዶክስ ለአማኞቿ ተይ እና እዛው እራሳቹ ጋር የጠፋትን በመጀመርያ ገስጪ..ልቦና ይስጥሽ

    • ይሄን የምልሽ በጌታ ፍቅር ነው እህቴ
      ከዚህ ሁሉ መልካም ፅሑፍ ልታውጪ የቻልሽው የተጠመዘዘ ነገር በመሆኑ በጣም የሳዝናል :: ለዘሪቱ በቸርነቱ ራሱን የገለጠላት አምላክ ላንቺም ይገለጥልሽ ::
      ነጠላ የለበሰ የኦርቶዶክስ እምነት ብቻ ነው ብሎ ትርጉም መስጠት በራሱ የበሽበትን የመላክታል። ለነብስሽ ስትዪ እህቴ ልብሽን ከፍቺና በቀና መንፈስ ለመረዳት ትጊ፣ ጌታ ቢረዳሽ መፅሐፍ ቅዱስሽ ላይ ካለው እውነት ውጪ እዚ ፅሑፍ ላይ እንደሌላ በተረዳሽ :: ሰላም ላንቺ!

  • I am so happy about you.. u r truly inspirational
    Geta yebarkesh!!
    I see Christ in you than most agelgays.
    I wish to serve the Gospel with you one day

  • Dear Zerfe Kebede,

    It is really wrong to categorize and defame others. It is Jesus who can judge or condemn.
    It is not your task. NEVER RUSH TO JUDGE BECAUSE IT IS NOT YOUR DUTY. That is the duty only God does. Do not quote scriptures to criticse others. Please stop any form of accusation and just do your own faith and live a holy life.

    We do not know the work of God. He has plan in everyone. Every preacher.
    Stop categirizing, labeling, and dwnouncing. That is not how gospel is preached. That certainly hampers the spread of the gospel.

    Thank you.

  • First, remove the photo on top, shot by Abinet (Photo credit: Abinet Teshome). The photo is a destruction to the whole text you wrote.

  • God blessed you,
    ብዙዎችን የእርኩስ መንፈስ ያስነጥሳቸዋል እህቴ አንች ግን በርች የሠላም ዓምላክ ፀጋዉን ያብዛልሽ ።

  • ይሄ የእውነት ቃል ሁሉም ልቀበለው የምገባ የደህንነት መንገድ ነው!!
    ዘመንሽ ይባረክ በርች!

  • The” True Life” is given for us by Christ’s resurrection. I’m so glad & so happy to hear this. GOD Bless You.

  • ለራሄል ሙሉጌታ ከመፅሃፍ ቅዱስ ቃል ውጪ ተናግራለች እንዴ?ምነው እህቴ መፃፍና ማንብ ከቻልሽ መፅሀፍ ቅዱስሽን አውጪና አንብቢ እውነቱን መንፈስ ቅዱስ ይርዳሽ መዳን በክርስቶስ ብቻ ነው “እኔ ህይወትም መንገድም ነኝ ከኔ በቀር ወደአብ የሚያደርስ የለም” ይልሻል ጌታ ደግሞ እንዳትረሺ በዘመን መጨረሻ በጌታ ፊት የሚፈረድብሽ ብቻሽን እንጂ በማህበር አይደለም ጌታ ይርዳሽ እና እስኪ ራስሽን ከማንም ጋር ሣይሆን ከመፅሀፍ ቅዱስ አኳያ የቱ ጋር እንዳለሽ ገምግሚ ጌታ ይወድሻል ተባረኪልኝ

  • ጌታ ይባረክ በመዳንሽ በጣም ደስ ብሎኛል እህቴ ጌታ ቀሪ ዘመንሽን ሁሉ በደሙ ይሸፍንሽ እልፎችን ጌታ ባንቺ ተጠቅሞ ይማርክ በርቺልኝ እወድሻለሁ ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ

  • የመሰአዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል !!! በርቱ አይዞአችሁ …….የነገርሁህን እስከማድረግ ድረስ አልተውህም…….. ያለ እግዚአብሔር አለ

  • Geta yeberkesh wude ehetachen gn teker set(ምሳሌ 31፥10) be hulu negresh lay leba endethogn god bless u zeritu

  • የኔ ውድ እህት በጣም ነው የምወድሽ አንቺ ለብዞዎች በረከት ነሽ

    አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ ጌታ ልብዋን ከፈተላት። ሐዋርያት 16፥14

  • በቅድሚያ በውስጤ ድብን ያለ ቅንዓት ነበረኝ
    ዘሪቱ ዘፋኝ ከምትሆን ምንአለ? ዘማሪ ብትሆን እያልኩ በህይወት እያለሁ ዘማሪ ሆነሽ በማየቴ እግዚአብሔርን አመሰገንኩት
    እውነት ቤት ወይም መኪና ከመግዛት በላይ ነው ደስ ያለኝ ጌታ ይባረክ!

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.