[the_ad_group id=”107″]

የእግዚአብሔር ሕዝብ

ኢየሱስ ለሁሉ

Hand of Christ reaching down from heaven to grab the hand of man

መልአኩም እንዲህ አላቸው፦እነሆ፣ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።’” (ሉቃስ 2፥10-11)

ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰዎች ሁሉ የሚሆን መልካም ዜና ነው። በክፉ በተያዘ ዓለም ውስጥ መጽናናትና ዕረፍት፣ ትርጕምና ደኅንነት፣ በኀጢአት ምክንያት ለዓለም ሁሉ ከሆነው ርግማን ሊያወጣን የሚችል እውነተኛ በረከት እርሱ ብቻ ነው። ታማሚ ለሆነችው ዓለም መድኃኒቷ ኢየሱስ ነው። መድኃኒትነቱም ለተቀበሉት ሁሉ ነው፤ ያለ ልዩነት። በሞት ፍርድ ሥር ሆነው፣ በሞት መንገድ ላይ እየተጓዙ ላሉ ማንም ይሁኑ ከየት፣ ማምለጫ ሊሆን ራሱን የሰጠው ለሁሉም ነው። እርሱ ድቅድቅ በነበረው ክፉ ጨለማ ላይ የብርሃኑን ኀይል የገለጠ፣ የዓለም ሁሉ ብርሃን ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰዎች ሁሉ ጥልቅ የነፍስ ፍለጋ ነው። ሰው ከእርሱ ጋር ኅብረት ያደርግ ዘንድ ፈጥሮታልና፣ ሰው ያንን ማድረግ በቻለ ጊዜ ብቻ ያርፋል። ሰውም ያንን እስኪያደርግ ድረስ ጥልቅ የሆነውን ክፍተቱን እየሸነገለና ያንንም ለመሙላት የተለያየ ነገርን በማሳደድ በብዙ ይደክማል። 

እግዚአብሔር ማዳንን ይወድዳል። ይድን ዘንድ የማይፈልገው ሰው የለም፤ የማዳኑ በር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሚመጡ ሁሉ የተከፈተ ነው፤ የምሕረት ዕድሉ ለዓለም ሁሉ ነው። ማንም ይታዘዘው ዘንድ መርጦ ነፍሱንም ከዘላለም ሞት ማስመለጥን ወድዶ በኢየሱስ ክርስቶስ ቢያምን ይድናል፤ የህያዋን አገር ዜጋም ይሆናል። የእግዚአብሔር ከሆነው ሕዝብ ይቈጠራል። እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ ይወድዳል። የማዳን ፍቅሩም ለዓለም ሁሉ ነው። በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።(ዮሐንስ 3፥6)።

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰዎች ሁሉ ጥልቅ የነፍስ ፍለጋ ነው። ሰው ከእርሱ ጋር ኅብረት ያደርግ ዘንድ ፈጥሮታልና፣ ሰው ያንን ማድረግ በቻለ ጊዜ ብቻ ያርፋል። ሰውም ያንን እስኪያደርግ ድረስ ጥልቅ የሆነውን ክፍተቱን እየሸነገለና ያንንም ለመሙላት የተለያየ ነገርን በማሳደድ በብዙ ይደክማል። አንዳንዶች ስኬትን፣ ሌሎች ብልጽግናን፣ አንዳንዶች ዝናን ሌሎች ዕውቀትን፣ አንዳንዶች ደስታን ሌሎች ወዳጅነትን፣ አንዳንዶች ፍቅርን ሌሎች እውነትን በመፈለግ በየምንደርስበት ደረጃ የፍለጋችንን ጥልቀት በበለጠ እየተረዳን ብቻ ርካታን ሳናገኝ እንባክናለን። ኢየሱስ ግን ለተጠማችው ነፍሳችን ርካታን ሰጥቶ፣ ለጥያቄያችን ሁሉ መልስ ሆኖ ያሳርፈናል።

እርሱ ሊያድነው የማይችለው የኀጢአት በሽታ የለም፤ ለእርሱ የሚከብደው ጨለማ፣ ከይቅርታው በላይ የሆነም በደል የለም። 

የሰው ዘር በሙሉ ኢየሱስን የማወቅ ዕድልን ሊያገኝ ይገባዋል፤ ሌሎች ፍለጋዎቻችንን ባንደርስባቸው፣ ያልደረስነው እነርሱ ላይ ብቻ ነው፤ ኢየሱስን ባናገኘው ግን ያላገኘነው ራሳችንንም ነው፤ የተፈጠርንበትን ዐላማና የፈጠረንን ወዳድ አምላክ የማወቅ ዕድልን፣ ከዘላለም ሞት የመዳን አጋጣሚን ሳናገኝ ቀረን ማለት ነው። ሰዎች ሁሉ እግዚአሔር እንዴት ባለ ፍቅር እንደወደዳቸው ሊያውቁ ይገባል። በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ወደ ሕይወት የመጡ ሁሉ፣ ገና በሞት መንገድ ላይ ላሉቱ ያለ አድልዎና ያለ ልዩነት ወደ ሕይወት ይመጡ ዘንድ ሊናገሩ ይገባቸዋል፤ ለሰዎች ሁሉ የሚያስፈልግ እውነተኛ መልስ ኢየሱስ ነውና። እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል። (1 ጢሞቴዎስ 2፥4)።

እርሱ ሊያድነው የማይችለው የኀጢአት በሽታ የለም፤ ለእርሱ የሚከብደው ጨለማ፣ ከይቅርታው በላይ የሆነም በደል የለም። ከመንገዳቸው ሊመለሱ ለሚወድዱት ሁሉ ጥሪው የንስሐ ነው። ካዳናቸው መካከል፣ ‘አንተ ንስሐ አያስፈልግህም፤ አንተ ጥሩ ሰው ነህ፣ ያንተ ኀጢአት ብዙም አይደልም’ ብሎ የሚያልፈው አንድም ሰው የለም። ሁላችምን በድለናልና፣ ሁላችንም ከኀጢአት ለመዳን ኢየሱስ ያስፈልገናል። ‘ያንተ ኀጢአት ትንሽ ይበዛል፤ አንተን ማዳን አልችልም’ በማለት ሳይምር የሚመልሰውም አይኖርም፤ እርሱ የመጣው ኀጢአተኛውን ሊያድን ነውና። ወደ እርሱ የመጡትን ሁሉ ሊያድን፣ ፈጽሞም ይቅር ሊል ይችላል፤ ይወድዳልም።

ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ በምድር በተመላለሰባቸው ወራት፣ ከሰዎች ጋር የነበረው ግንኙነት በርግጥ እርሱ ሰዎች ሁሉ ይድኑ ዘንድ ያለውን ብርቱ መሻት የሚመሰክር ነው። የሰዎች መዳን ቅድሚያ የሚሰጠው፣ እስከ ሞትም ድረስ ዋጋን የከፈለበት ጕዳይ ነው።

ሰዎች በማኅበረ ሰብ ውስጥ የሚታዩበት ዕይታ፣ እርሱም ከእነርሱ ጋር በመታየቱ ሊሰጠው ስለሚችለው ስም ግድ አልነበረውም፤ ጕዳዩ የነበረው መዳናቸው ነው።  የወጣለትም የሐሜት ስም፣ “የቀራጮችና የኀጢአተኞች ጓደኛ” የሚል ነበር። እርሱ፣ የተገኘበት ማኅበረ ሰብ እንደ ከሃዲና ጠላት አድርጎ በሚያያቸው፣ በርግጥ ሕዝባቸውንም በድለው በነበሩ ቀራጮች ቤት ሲበላ፣ ትኵረቱ ከምሕረቱ የተነሣ ሊቀበሉት ስላላቸው መዳን እንጂ፣ የእነርሱ ያለፈ ታሪክ ወይም ወቅታዊ ሁኔታ አልነበረም። ሊወግሯት የተጠራሩባትን ሴት በርግጥ መበደሏን ከማናቸውም ይልቅ ቢያውቅም፣ መጠሪያዋ “አመንዝራ” ሆኖ እንዲዘልቅ ግን አልፈቀደም። በደሏ እንደ በደላቸው እንደ ሆነ በጥበብ ገልጦ፣ ኀጢአትን ደግማ የማትሠራ ትሆን ዘንድ ነግሯት ሲያበቃ፣ በምሕረቱ አዳናት።

ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ በምድር በተመላለሰባቸው ወራት፣ ከሰዎች ጋር የነበረው ግንኙነት በርግጥ እርሱ ሰዎች ሁሉ ይድኑ ዘንድ ያለውን ብርቱ መሻት የሚመሰክር ነው። 

ይኖርበት ከነበረው ኀይማኖታዊ ከበሬታ የተነሣ ኢየሱስን በግልጽ ሊያገኘው ያልተመቸውን ሰው፣ እውነትን አጥርቶ እንዲረዳ በሚመቸው ሁኔታ ለማግኘት እንቢተኛ አልሆነም፤ ይድን ዘንድ ዳግም ሊወለድ እንደሚገባው ሊገልጥለት ወድዶ አገኘው እንጂ።

እስራኤልን በቅኝ ገዝተው የነበሩት የሮማውያን መቶ አለቃ የነበረውን ሰው፣ አገልጋዩን እንዲፈውስለት በጠየቀው ጊዜ፣ ‘የወገኖቼ ጨቋኝ ነህ’ በማለት ምሕረትን አልነፈገውም፤ በእምነቱ ተደንቆ የተማጽኖውን ፈውስ ሰጠው እንጂ።

ኢየሱስ እንደ አይሁድ ሥርዐት፣ እንደ ሕግም ንጹሕ ያልነበሩትን አልተጠየፈም። ለምጣሙን መፈወስ እንዳያረክሰው አልሠጋም፤ ይድን ዘንድ ወድዶ ዳሰሰው እንጂ። ልብሱን ዳስሳ የተፈወሰችውን ደም የሚፈስሳትንም ሴት፣ “ንጹሕ ሳትሆኚ እንዴት ትነኪኛለሽ”ብሎ አልተቆጣም፤ እርሱን የሚያስደንቀው እምነት፣ መሻቱም መማር ነበረና እምነቷን አድንቆ በሰላም ትሄድ ዘንድ ሸኛት እንጂ።

እርሱ ሰው የፈረደባቸውን የሚምር፣ የማይፈለጉትን የሚፈልግ፣ የተገለሉትን የሚቀበል፣ የተናቁትን የሚያከብር፣ ሰው የሚጠየፋቸውን የሚዳስስ፣ ሁሉ የሞላቸው ለሚመስሉት የሚራራ፣ ለሚጠይቁት ሳይታክት የሚመልስ፣ በምንም ሁኔታ የሰዎችን መዳን የሚያስቀድም፣ ለሰው ልጆች ሁሉ የራሱን ሕይወት በፍቅር የሚገልጥ አዳኝ ነው።

እግዚአብሔር ማዳንን ይወድዳል። ይድን ዘንድ የማይፈልገው ሰው የለም፤ የማዳኑ በር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሚመጡ ሁሉ የተከፈተ ነው፤ የምሕረት ዕድሉ ለዓለም ሁሉ ነው።

ደቀ መዛሙርቱ ይሆኑ ዘንድ በእምነት የበቁትን ወይም በቤተ መቅድስ የነበሩትን አልመረጠም፤ እዚህ ግባ የማይባሉትን ታናናሾች መርጦ ታላቅ የሆነውን የእርሱን ነገር አደረገባቸው እንጂ። እርሱ ደኅና ነን የሚሉተን ጎሽ ሊል ሳይሆን፣ ኀጢአተኞችን ሊያድን፣ በትሑታን ታዛዦቹም የአባቱን ክብር ሊገልጥ መጣ። ሄዳችሁ፣ ʻከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወድዳለሁ፤የሚለውን ቃል ትርጕም አጢኑ፤ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና።(ማቴዎስ 9፥13)፤ “…እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ (1 ቆሮንቶስ 1፥27)፤ ኀጢአተኞችን ሊያድን ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው …” (1 ጢሞቴዎስ 1፥15)።

እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ፣ ፈጣሪ አምላክ እግዚአብሔር ወልድ መሆኑን አምነን ለተቀበልነውና የእግዚአብሔር ልጅነትን መብት በእምነት ወራሽ በመሆን ከታዛዥ ሕዝቡ ለምንቈጠረው፣ የሰጠን ዐደራ ልክ እንዲሁ በማድረግ እንመስለው ዘንድ ነው።  ምሕረትና የሰዎችን መዳን ቅድሚያ የምንሰጠውና ከምንታይበት ዕይታና ከግል ክብራችን ይልቅ፣ እጅግ የምንፈልገው እንዲሆን ምሳሌን ትቶልናል። በትሕትናና ከግብዝነት በራቀ መንፈስ መልካሙን የምሕረት ዜና ለዓለም ሁሉ ያለ ልዩነት እናደርስ ዘንድ ነው ትእዛዙ። እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። (ማርቆስ 16፥15)።

እኛም ሕዝቡ፣ ዓለም ሳይፈጠር ለብቻው የነበረውን ክብር በፍቅርና በመሥዋዕትነት ዐብረን እንድንወርስ የሰጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሕርይ ተካፈይ ሆነናልና፣ በዚያው መንፈስ ይህን ሕይወት ያለ ስስት እናካፍላለን። ‘በእምነት እኅትና ወንድሞቻችን ሁኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤት ኑ!’ እያልን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች እንድንሆን ባበቃን በመንፈሱ ኀይል አንዱንና ብቸኛውን የመዳን ስም ለፍጥረት ሁሉ እናውጃለን። ጌታን ተቀበሉ እያልን እንጣራለን። “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች ሁሉ የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (የሐሥ 4፥12)።

የእግዚአብሔርን ክብር ማየትና መጠማት:- የኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻው ግብ

አማረ ታቦር Seeing and Savoring Jesus Christ ከተሰኘው የጆን ፓይፐር መጽሐፍ በተከታታይ ከሚያቀርባቸው ጽሑፎች መካከል፣ ይህ “የእግዚአብሔርን ክብር ማየትና መጠማት፦ የኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻው ግብ” ሲል ወደ አማርኛ የመለሰው ይገኝበታል።

ተጨማሪ ያንብቡ

ወርኀ ጽጌ ወስደት

“ወርኀ ጽጌ ወስደት” የተሰኘው ይህ ጽሑፍ፣ በወንጌላውያኑ ዘንድ ብዙ ትኩረት ስለማይሰጠውና ጌታ ኢየሱስ በሕጻንነቱ ወራት ከእናቱ ማርያምና ከዮሴፍ ጋር ወደ ግብፅ የተሰደደበትን ታሪክ መነሻ በማድረግ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሁነቱ ያለውን ትርክት ያስቃኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ

4 comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

  • “ኢየሱስ ክርስቶስ የሰዎች ሁሉ ጥልቅ የነፍስ ፍለጋ ነው” አባባልሽ ጥሩ ነው። ዘር፣ ቋንቋ፣ ዘመን፣ እድሜ፣ ፆታ ሳይለይ ሰው የተባለ ሁሉ ጥልቅ ፍለጋ አለው። ፍለጋው ኢየሱስ መሆኑን አያውቅ ይሆናል። ኢየሱስ የሚባል እንዳለ ሰምቶ አያውቅ ይሆናል። ስለ ኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ፣ ከኃጢአት እስራት ስለ መፈታት የምሥራች ሲነገረው፣ አንቺም እንዳልሽው፣ ያ በብልጽግና፣ በእውቀት ውስጥ ሲፈላልገው የኖረው ለካንስ ኢየሱስን ኖሯል! ከሞት እንደ መነሣት ነው! ሲነሣ ብቻ ነው ሞቶ እንደ ነበረ የሚገነዘበው! ታስሬ ነበር ተፈታሁ! ሞቼ ነበር፣ ተነሣሁ ይላል! ተራውን ያውጃል! “የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች እንድንሆን ባበቃን በመንፈሱ ኀይል አንዱንና ብቸኛውን የመዳን ስም ለፍጥረት ሁሉ እናውጃለን!”

    ትንሽ ጥያቄ አለቺኝ፦ ፎቶው ላይ ከሚታየው እጅ፣ የላይኛው ጠየም ቢል እግዚአብሔር ይቀየም ይሆን? ፡)

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.