[the_ad_group id=”107″]

የእግዚአብሔር ሕዝብ

እግዚአብሔር ሕዝብ አለው፤ ከሰዎች መካከል ለይቶ የእኔ የሚለው፣ ወድዶ ያዳነው ሕዝብ አለው። ይህ ሕዝብ ማን ነው? እንዴትና በየት የእግዚአብሔር ቤተ ሰብ ወደ መሆን መጣ? የሰማያትና የዓለማትን ፈጣሪ “አባ፣ አባት” ብሎ የሚጠራበት ድፍረትና ከእርሱም ጋር ፊት ለፊት የሚነጋገርበትን መብት በምን አገኘ? በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች መካከል በምን ተለይቶ ይታወቃል? የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ አምላክ ወድዶ ለክብሩ የለየው ሕዝብ የቱ ነው? አምላኩና አባቱ በሰማይ የሆነው ይህ ሕዝብ፣ በዚህ ምድር ሲኖር ዐላማው ምንድን ነው? የዚህስ ሕዝብ መጨረሻ ምንድን ነው? እነዚህን ጥያቄዎች እየመለስን፣ ስለ ሕዝቡ በሦስት ተከታታይ ክፍል እናነብባለን።

ልዩ ሕዝብ

በምንኖርባት ዓለም  የሰው ልጆችን በየጎራው የከፋፈሉና አቧድነው ያቀፉ ልዩነቶች እንዳሉ የታወቀ ነው። የጾታ፣ የዘር፣ የቆዳ ቀለም፣ የብሔራዊነት፣ የሃይማኖት ተቋማትና የማኅበራዊ መደብ (የኑሮ ደረጃ) የመሳሰሉ ብዙ ልዩነቶች በመካከላችን አሉ። እኛም እነዚህን ልዩነቶች ለጋራ ጥቅም እንደሆነልን በጎ ነገር ከማየትና ከዚያ ከማትረፍ ይልቅ፣ የመከፋፈያና የመጠፋፊያ ምክንያት አድርገን፣ ሆነን በተገኘናቸውና ለመሆናችን አንዳችም አስተዋጽዖ በሌለን ልዩነቶች ሳይቀር ስንናናቅና ስንጠላላ፣ ሰው የመሆናችንን ክብር አብዝተን ስንበድል እንገኛለን።   

ሰዎች ሁሉ እኵል የሆነ ሰብአዊ ክብር ያለን፣ በፈጠረንና በወደደን አምሳል የተፈጠርን ነን (ዘፍጥረት 5፥2-3)። ሰዎች ሁሉ በመጀመሪያ ከአንድ ወገን፣ ከአንድ ቤት የተገኘን የአንድ እናትና አባት ልጆች ነን። ልዩነቶቻችንም በመካከላችን የሰውነት ዋጋን የሚያበላልጡ እንዲሆኑ ሳይሆን፣ በማንኛውም ተሽለን በተገኘንበት ነገር ለሌሎች እንድንተርፍ፣ ጎድሎን በተገኘ ምንም ነገር ከሌሎች እንድንጠቀም ለጋራ ልማትና መያያዝ የታሰበ ነበር። ልዩነቶቻችን ለበላይነትም ሆነ ለበታችነት ስሜት ምክንያት አድርገን መመልከትና ከዚያም ዕይታ የተነሣ፣ ሰው ከመሆናችን ዋጋና ክብር በታች በሆነ መገፋፋትና መቃረን መንገድ ውስጥ የምንራመድ መሆናችን የሚገባ አይደለም፤ የተፈጠርነው ለዐብሮነት፣ የፈጠረንን ለመምሰልና እርሱንም እንደ አምላክ ዐውቀን እንድንገዛለት ነውና (ሚክያስ 6፥8)።

ልዩነቶቻችን ለበጎ በመካከላችን ቢኖሩም፣ በምደራችን ላይ ያለው አንድ እውነተኛ ልዩነትና ሁለት ዘላለማዊ ጎራ ብቻ ነው። ከዚህ ልዩነት ውጪ ሁሉም ልዩነት ከምታልፈው ዓለም ጋር ዐብሮ የሚያልፍ ምድራዊ ልዩነት ነው። ይህም ልዩነት ፈጣሪያችን እግዚአብሔር፣ የሚታዘዙትን ከሌሎች ሊለይ በመረጠው መንገድና በአዘጋጀው ሕይወት ላይ በሚገኙና በማይገኙ መካከል ያለው ልዩነት ነው። በሕያዋንና በሙታን መካከል ያለው ልዩነት፣ ወደ ብርሃን በመጡትና አሁንም በጨለማ ባሉት መካከል ያለ ልዩነት፣ ከእግዚአብሔር ጋር በታረቁትና አሁንም በጥል ባሉት መካከል ያለ ልዩነት፣ የእግዚአብሔር ልጆች በሆኑትና ባልሆኑት መካከል ያለው ልዩነት ነው። ይህም፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመንና ባለማመን መካከል ያለ ወሳኝ ልዩነት ነው። ልዩነትን በዚህ ሊያደርግ የእግዚአብሔር አብ መልካም ፈቃድ ሆኗል። ኢየሱስ ክርስቶስ ልዩነት ነው። ልጁያለውሕይወትአለው፤የእግዚአብሔርልጅየሌለውሕይወትየለውም።(1 ዮሐንስ 5፥12) 

በኢየሱሰ ክርስቶስ በማመን የእግዚአብሔር የሆነው ሕያው ሕዝብም፣ ልዩነት የሆነለትን የእግዚአብሔርን ዐብሮነት ዋጋ እየሰጠ እንደ አምላኩ ፈቃድ፣ ለአምላኩ ክብር ሰማያዊ ማንነትን በሰዎች ሁሉ ፊት እያንጸባረቀ የሚኖር እንጂ፣ ዓለምን በመምሰል ዋጋ የተከፈለበትን የልዩነት ብርሃን ቀብሮና ደብዝዞ የሚኖር ሕዝብ አይደለም (ሮሜ 12፥2፤ ማቴዎስ 5፥16)። 

ከክርስቶስ ጋር የነበሩትና የተከተሉት፣ የእርሱ መሆናቸውን የመሰከረው በንግግርና በግብር እርሱን መስለው መገኘታቸው ነው።

ከክርስቶስ ጋር የነበሩትና የተከተሉት፣ የእርሱ መሆናቸውን የመሰከረው በንግግርና በግብር እርሱን መስለው መገኘታቸው ነው። “ክርስቲያን” የሚለውን ስያሜም ያገኙት ከዓለም ተለይተው ባገኟቸው ተመልካቾች እንጂ፣ ለራሳቸው ያወጡት ወይም ጌታ እንዲጠሩበት የሰጣቸው የሃይማኖት ስም አልነበረም (የሐሥ 11፥27)። ኢየሱስ ክርስቶስ ያወረሳቸው ሕይወቱን እንጂ፥ መጠሪያ ስምን አልነበረምና። ስምን አውርሷቸው ከሆነም፣ ያወረሳቸው የሚያድነውን የራሱን ስም ብቻ ነው፤ ኢየሱስ የሚለውን ልዩነት ፈጣሪ ስም (የሐሥ 4፥12)። በዚህም ዘመን በክርስቶስ የእግዚአብሔር የሆነው ሕዝብ ሊታወቅ የሚገባው ከዓለም ተለይቶ በሚታይ፣ ክርስቶስን የመምሰል ሕይወት ነው፤ በርግጥ የእርሱ የሆኑትም በዚህ ይታወቃሉ (ማቴዎስ 7፥20)። 

ይህ ልዩ ሕዝብ በምድራዊ ልዩነቶቹ እንደገና ሊያዝና ሊከፋፈል የሚገባው ሕዝብም አይደለም። በክርስቶስ ከዓለም በተለየው ሕዝብ መካከል እንደ እግዚአብሔር ጥበብና መልካም ፈቃድ የሆነ “ልየታ” እንጂ ልዩነት የለውም። ሁሉም ከጨለማ ወደ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ አዲስ ፍጥረት ሆኗል። ሁሉም ከእግዚአብሔር እንደ ተሰጠው ማንነት ለጋራ ጥቅም የድርሻውን የሚወጣ፣ ከመካከልም በተለየ ዋጋ የሚቈጠር ሳይኖር፣ ሁሉም በእምነት ባገኘው የልጅነት ክብር በእኵል የሚተያይና በትሕትና የሚቀባበል ሕዝብ ነው።

ይህ ልዩ ሕዝብ በምድራዊ ልዩነቶቹ እንደገና ሊያዝና ሊከፋፈል የሚገባው ሕዝብም አይደለም። በክርስቶስ ከዓለም በተለየው ሕዝብ መካከል እንደ እግዚአብሔር ጥበብና መልካም ፈቃድ የሆነ “ልየታ” እንጂ ልዩነት የለውም። ሁሉም ከጨለማ ወደ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ አዲስ ፍጥረት ሆኗል።

ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር ልጆችናችሁ፤ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁላችሁ ክርስቶስን ለብሳችሁታልና። በአይሁድና በግሪክ፣ በባሪያና በነጻ ሰው፣ በወንድና በሴት መካከል ልዩነት የለም፤ ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ናችሁ።(ገላቲያ 3፥26-28)፤ ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፏል፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአል (2ቆሮንቶስ 5፥17)።

በፍጥረት የሰው ልጆች ሁሉ እኩል ሰብአዊው ክብር ያላቸው ቢሆንም፣ ልዩነት በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ይህ ሕዝብ ከነገድ፣ ከቋንቋ፣ ከወገን ሁሉ በእርሱ መሥዋዕትነት ተዋጅቶ ለእግዚብሔር ክብር ሊሆን ተለይቷል። ይህም ሕዝብ ሕያው ለሆነው አምላክ የሚገዛ፣ ለዘላለም የሚኖር ሕያው ሕዝብ ነው። 

ይህ ሕዝብ ዋጋ የተከፈለለት፣ አምላክ ሰው የሆለት፤ መለኮት የተጎሳቆለለት ሕዝብ ነው። መጽሐፉንትወስድዘንድማኅተሞቹንምትፈታዘንድይገባሃል፤ታርደሃልና፣በደምህምለእግዚአብሔርከነገድሁሉከቋንቋምሁሉ፣ከወገንምሁሉ፣ከሕዝብምሁሉ፣ሰዎችንዋጅተህለአምላካችንመንግሥትናካህናትይሆኑዘንድአደረግሃቸው፤በምድርምላይይነግሣሉእያሉአዲስቅኔንይዘምራሉ።(ራእይ 5፥9-10) 

ይህ ሕዝብ በአምላኩ የተደረገለትን አስደናቂ የማዳን ሥራ እየተረከና፣ እየዘከረ የሚኖር ሕዝብ ነው። 

ይህ ሕዝብ የእግዚአብሔር ወንጌል ባለ ዐደራ፣ የክርስቶስ ኢየሱሰ እንደ ራሴ የሆነ ሕዝብ ነው። በምድር ሊመላለስበት በተሰጡት ቀናትም ስለ ኢየሱስ የሚኖርና የሚሠራ፣ ክብርንም ሽልማትንም ዐደራ ከሰጠው ጌታ ብቻ የሚጠብቅ፣ ከወደደውና ካዳነው አምላክ ጋር ስለ መንግሥቱ ዐላማ ዐብሮ የሚሠራ፣ የዚህን ዓለም ዋጋና ክብር የናቀ ሕዝብ ነው። 

ይህ ሕዝብ በአምላኩ የተደረገለትን አስደናቂ የማዳን ሥራ እየተረከና፣ እየዘከረ የሚኖር ሕዝብ ነው። ይህንም እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል፣ ሊያምኑትና ሊቀበሉት የፈቀዱትን ሁሉ የመንግሥቱ ዜጎች፣ የቤቱ ልጆች ለማድረግ ያለውን ዐላማ፣ መልካም የሆነውን የወንጌል ዜና ለሰው ልጆች ሁሉ በማብሰር ሥራ የሚተጋ ሕዝብ ነው። 

ይህ ሕዝብ በየዕለቱ ከዚህ ምድር ሥርዐት፣ ከሥጋው ፈቃድና ከጨለማው ዓለም ጋር በእግዚአብሔር ቃል እውነትና በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እየተፋለመ የሚኖር ተዋጊ ሕዝብ ነው። የዓለምን ብልጭልጭና የዲያብሎስን ሽንገላ እንዲያጠምደው ሳይፈቅድ፣ ዐይኑን በኢየሱስና በኢየሱስ ላይ ብቻ ተክሎ ዜጋ የሆነበትን መንግሥት በመንፈሳዊ ተጋድሎ የሚያስከብርና የሚያሰፋ ወታደር ሕዝብ ነው። 

ይህ ሕዝብ ስለ ተሰጠው ተስፋና ስለ አምላኩም ፍቅር ሲል፣ በዚህኛው ዓለም ጥበብ ፊት እንደ ሞኝና እንደ ከሠሰረ ሰው የሚቈጠርበትን ንቀትና፣ ስለ እውነትና ስለ ጽድቅ ሲል የሚደርስበትን ልዩ ልዩ መከራ በመታገሥ፣ በሁሉ እያመሰገነ፣ በሥጋው እያነባ በመንፈሱ ሐሴት የሚያደርግ ነው። 

ይህ ሕዝብ ስለ ተሰጠው ተስፋና ስለ አምላኩም ፍቅር ሲል፣ በዚህኛው ዓለም ጥበብ ፊት እንደ ሞኝና እንደ ከሠሰረ ሰው የሚቈጠርበትን ንቀትና፣ ስለ እውነትና ስለ ጽድቅ ሲል የሚደርስበትን ልዩ ልዩ መከራ በመታገሥ፣ በሁሉ እያመሰገነ፣ በሥጋው እያነባ በመንፈሱ ሐሴት የሚያደርግ ነው (ሮሜ 8፥18)። የሰማይን ፍቃድ ማድረግ መብልና መጠጡ የሆነለት፣ ከተፈጥሮ በላይ የሆነና ከተፈጥሮ በላይ የሆነን ብዙ ድንቅና ተኣምር በእግዚአብሔር መንፈስ ኀይልና በኢየሱስ ስም የሚያደርግ ኀያል ሕዝብ ነው። 

ከተፈጥሮ በላይ፣ በእግዚአብሔር ኀይል በኵል በዚህ ሕዝብ ላይ የሚገለጠው የተኣምራት ሁሉ ተኣምር፣ የፍቅር ምንጭ የሆነውን አምላክ በመውደድ ጀምሮ፣ ጠላትን እስከ መውደድ ድርስ የሚዘልቀው የክርስቶስ ፍቅር ኀይል መገለጥ ነው። ይህም ፍቅር ሌሎችን እንደ ራስ በማየትና እንዲሆንብን የማንወድደውን በሌሎች ላይ ባለማድረግ፣ በትዕግሥት፣ በየዋህነት (መሥዋዕትነት)፣ በአክብሮት፣ ሌሎች ከእኛ እንደሚሻሉ በትሕትና በመቍጠር፣ በደልን ሁሉ ይቅር በማለትና በመሳሰሉት የሚገለጥ ነው (ዮሐንስ 13፥35፤ ማቴዎስ 5፥43-48)።

በእርሱ ሁሉን ጠቅልሏልና አስቀድሞ እንዲጠብቀው እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጠውም ሕግ ፍቅር ነው። እንደ ትእዛዙም እግዚአብሔር አምላካችንን ለመውደድ በተሰጠንና ከእርሱ ጋር ኅብረትን በምናደርግ ጊዜ፣ ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን መውደድ የምንችልበትን ንጹሕ (uncorrupted) ፍቅር እንቀበላለን። የእግዚአብሔር ፍቅር ከሌለን፣ እንኳን ሌሎችን ራሳችንን የምንወድድበት ፍቅር አይኖረንም፤ እንዴት እንደምንወድድም አናውቅም (ማቴዎስ 22፥37-40፤ ሮሜ 5፥5፤ 1ኛ ዮሐንስ 4፥8)።

የእግዚአብሔር ሕዝብ በምድር ላይ ከሚመላለሱ ሰዎች ሁሉ የሚወድድና የሚዋደድ በመሆኑ፣ ተለይቶ የሚታወቅ ሕዝብ ነው፤ እውነተኛ መገለጫውም ይህ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ (supernatural) ፍቅር ነው። ያለ ምክንያት ከወደደውና ወድዶ ካዳነው፣ ከአምላኩ የወረሰው ከሁኔታ በላይ የሆነ ፍቅር። በጨለማ የተያዘውን ዓለም ክፋት እያጋለጠ የሚኖረውም በዚህ ፍቅር በመመላለስ ነው።

የእግዚአብሔር ሕዝብ በምድር ላይ ከሚመላለሱ ሰዎች ሁሉ የሚወድድና የሚዋደድ በመሆኑ፣ ተለይቶ የሚታወቅ ሕዝብ ነው፤ እውነተኛ መገለጫውም ይህ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ (supernatural) ፍቅር ነው።

በፍቅር የሚመላለሰው ይህ ሕዝብ፣ ‘ሁሉን ወዳድ ነው’ ስንል፣ ‘በሁሉ ተስማሚ፣ ሁሉን ተቀባይ ነው’ ማለታችን አይደለም። የእግዚአብሔር ፍቅር ጻድቅ ፍቅር ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር እውነትና በእውነትም ደስ የሚለው ፍቅር ነው።  የእግዚአብሔር ፍቅር ፍትሕን አጥርቶ ያያል እንጂ በፍርዱ አይወግንም። የእግዚአብሔር ፍቅር ይምራል፤ ደግሞም ያስተምራል። የእግዚአብሔር ፍቅር ይራራል፤ ደግሞም ይጋፈጣል። የእግዚአብሔር ፍቅር ይታገሣል፤ ደግሞም ይገሥጻል። የእግዚአብሔር ፍቅር አይሸነግልም። የእግዚብሔር ፍቅር አይፈራም። የእግዚአብሔር ፍቅር አይዋሽም።

ይህ ሕዝብ ሁሉን ይወድዳል፣ ብርሃኑንም በሰው ሁሉ ፊት ያበራል ስንል፣ በሰዎች ሁሉ ይወደደል ማለታችንም አይደለም።  ይህ ሕዝብ ይዞ የሚዞረው የክርስቶስ መዓዛ፣ ሰዎችን በሚድኑትና በሚጠፉት መካከል ለሁለት የሚከፍል መዓዛ ነው። የእግዚአብሔር ሕዝብ ለጌታ ሊሆኑ ለተገባቸው ልዩ መስህብ ያለው ተወዳጅ ሕዝብ፣ እንዲጠፉ ለሚሆኑት ደግሞ የሚገፋ፣ የተጠላ ሕዝብ ነው (2ኛ ቆሮንቶስ 2፥15-16፤ ዮሐንስ 15፥18-21)።

ቴክኖሎጂ እና ክርስትና

ስለ ቴክኖሎጂ ሲነሣ በአብዛኛው ወደ ሰው አእምሮ አስቀድሞ የሚከሰተው የቴክኖሎጂ ፈጠራ ኮምፒውተር፣ ገመድ አልባ (ተንቀሳቃሽ) ስልክ ወይም በይነ መረብ (Internet) ነው፡፡ ነገር ግን የቴክኖሎጂ ፈጠራ ዘርፍ ብዙ ሲሆን፣ ለምሳሌ አውቶሞቢል፣ ባቡር፣ አውሮፕላን፣ ራዲዮ፣ ቴሌቭዥን፣ መገናኛ አውታሮች፣ ኅትመት እና ሌሎችም… ናቸው፡፡ ዛሬ የምንነጋገርበት ጉዳይ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በክርስትና ላይ ያሳረፉትን እና እያሳረፉ ያሉትን በጎ ተጽዕኖ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

የልየታ መንፈስ ጥሪ!

ንጉሤ ቡልቻ በዚህ ጽሑፋቸው፣ ምስቅልቅል ለበዛበት የአማኞች አምልኳዊ ገቢር መፍትሔ እንዲመጣ፣ “የልየታ መንፈስ” ይፈስስ ዘንድ ለአምላክ ተማጽኖ፣ ለምእመናንም ምክሮች ይለግሳሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ

መሪነትም እንደ ውበት

ለመሆኑ፣ የየቤተ ክርስቲያኑ መሪዎች አንድን የአመራር ዘይቤ በሚመሯት ቤተ ክርስቲያን በሥራ ላይ እንዲውል ካደረጉ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች እንዳሰቡት የአመራር ዘይቤውን ውጤታማነት ማየት ቢቸግራቸው ምን ማድረግ ይችላሉ?

ተጨማሪ ያንብቡ

7 comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

  • በኢየሱስ በኩል አንፅቶ “ልዩ ሕዝብ” (ቅዱስ ስለ ሆነ ቅዱስ) ያደረገን እግዚአብሔር ይመስገን። አንቺም እንዳመለከትሽው፣ “ልዩ” ስለ እኛ አይደለም። ከሌሎች የተሻልን አያደርገንም። ጥያቄው፦ ልዩ መሆናችን (በፍቅራችን በቅድስናችን) ኢየሱስን ያሳያል ወይ ነው። ፍቅርን ከቅድስና መ_ለ_የት፣ ከቅድስናም ከፍቅርም መ_ለ_የት ነው። የምንታየው፣ የም_ን_ሰ_ማው እኛው ከሆንን፣ ኢየሱስ ካልሆነ፣ ምን ዋጋ አለው? በየቶክ ሾው፣ ከየመድረኩ የሚታየውን/የሚደመጠውን ያዩ፦ እነዚህ ጴንጤዎች/ወንጌል አማኞች አቤት እንዴት ኢየሱስን ይመስላሉ ይላሉ? ወንጌል ያመንነውን፣ ልክ እንደ አሜሪካኖች ወገኖቻቸን ከቤተ መንግሥት ጉያ ሥር ተሸጉጠን ደጅ ስንጠና ስናመኻኝ ስንሞጋገስ የማይስማሙንን ስንጣላ ሲያዩ ምን ይላሉ?

    የአሜሪካ ወንጌላውያን ከፖለቲከኞች ጋር መመሳጠራቸው ቤተ ክርስቲያንን ዋጋ እያስከፈላት ነው። ዋጋው ምንድነው? ዋጋው አለመታመን ነው። እውነት ከሆነው ጋር አለመቆም ነው፤ መከፋፈል ነው። ዋጋው ከሐሰት ከአመፅ ከጥላቻ ከፍቅረ ንዋይ ጋር መደመር ነው። “ብልጽግና እና ታላቅነት”ን መንፈሳዊ ለሚያደርግ “ተዘርግቶ ቢተኛ አልጋው አጭር ነው፤ ሰውነቱን መሸፈን ቢወድድ መጎናጸፊያው ጠባብ ነው።” እውነት/ፍቅር/ቅድስና የለም፣ አንድነትም የለም! ለኢየሱስ ተከታዮች፣ ጥሪአቸው ኅልውናቸውና ክብራቸው በእውነት ላይ አለመደራደራቸው ነው። እውነት የለም፣ ሕይወትም የለም! የአሜሪካ ወንጌላውያን አቋም ግን የኢየሱስን ስም እያስነቀፈ፣ ብዙዎችን ከቤቱ እያፈለሰ ነው። የሚፈልሱት ሲጠየቁ፣ ምክንያታቸው በዋናነት፣ “ግብዝነት” ነው፤ ሁለት ፊት ማሳየት ማለት ነው። ምስክርነታቸው አይታመንም ነው። አካሄዳችን የአሜሪካ ገበያተኛነትን፣ እየኮረጀ ኢየሱስን በሚያስነቅፍ ጎዳና ላይ ነው። የተንጋደደውን ባማሩ በሚያቆላምጡ የቃላት ናዳ ማቃናት አንችልም!

    እግዚአብሔር ዝም ብሎ ያያል ማለት አይደለም። በዚህም ውስጥ እንኳ ሥራውን አይሠራም ማለትም አይደለም። አንድ ነገር ግን ግልጽ ነው፦ ስለ ስሙ ሲል፣ በቀጠረው መንገድ፣ በቀጠረው ሰዓት ቤቱን ያጠራል። እርሱ ልዩ አምላክ፣ አምሳያ የሌለው ነው። ወደ እርሱ ከመመለስ፣ እርሱን ከመምሰል ውጭ አማራጭ የለንም።

  • በልዑል እግዚአብሔር የጌታችን የመድሐኒታችን የክርስቶስ ኢየሱስ ፀጋው እና ቸርነቱ ፍቅሩ የሆነልሽ ውዷ እህቴ በነገር ሁሉ ተባረኪ እለት እለት የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ እና ማፅናናቱ ይሁንልሽ።

  • በልዑል እግዚአብሔር የጌታችን የመድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋው እና ቸርነቱ ፍቅሩ የሆነልሽ ውዷ እህቴ በነገር ሁሉ ተባረኪ እለት እለት የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ እና ማፅናናቱ ይሁንልሽ።

  • በስማም! እንዴት ጥልቅና ደስ የሚል ልብን የሚያረሰርስ፣ መንፈስን የሚያድስ ጽሑፍ ነው። የሰማይ አምላክ ይባርክሽ። ማስተዋልሽን ይጨምርልሽ። (መዝጊያው እውካባቢ ስለ ፍቅር የተጻፈው ላይ ፩ኛ ቆሮ – ምዕራፍ ፲፫ ቢጠቀስ ጥሩ ነው) – በብዙ ተባረኪ። በክርስቶስ ንጹሕ ፍቅር!

  • I thank Almighty God of Abriham, Isaac and Jacob for revealing his amazing Grace up on U and enabled u to believe live and witness His only begotten Son Lord Christ Jesus!!!

    Dear sister in Christ Zeritu Kebede, As you already know U are living Sacrifice for King Jesus and U are pleasing vessel infront of Him.
    God Bless You More!
    Let him keep you out reach of this wicked World, devil and lusts!!!
    Love You So Much In Christ!!!
    I am glad to see ur commitment to serve Kingdom of God!!!

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.