[the_ad_group id=”107″]

ሕይወትን በ “ታላቁ እኔ ነኝ” ላይ መጣል

በዚህ ዓለም በታወከችበት የCOVID-19 ወረርሽኝ ጤና ቀውስ፣ እንደ ክርስቲያን ተስፋ የምናደርገው ልዑል እግዚአብሔርን ነው። እርሱ በፈጣሪነቱ፣ ፍጥረትን ሁሉ፣ የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ በሥልጣኑ ቃል ደግፎ ይዟል። ዓለም በእርሱ ሉዓላዊነት ውስጥ እንጂ፣ በነገሥታትና ዐዋቂዎች እጅ አይደለችም። የእኛንም ሆነ የዓለምን ታሪክ በልጓም የያዘን ጌታ ነው የምናመልከው። እርሱ በመገረምም ሆነ በድንጋጤ አይያዝም፤ ነገንም በሥጋት ወይም በተስፋ አይጠብቅም! በማንም አይደገፍም፤ ለሥራውና ውሳኔው ትክክለኛነት ማንንም አያስፈቅድም፤ ማስተዋሉ ፍጹም ስለ ሆነ፣ ምክርም ከማንም አይጠይቅም፤ ዕውቀት አይጨመርለትም፤ አልገባኝም አሰረዱኝ አይልም፤ ነገሮች ሳይጀመሩ ፍጻሜያቸውን ያውቃልና!

ታዲያ በዚህ አምላክ ልባችን ካላረፈ፣ በማን ያርፋል? “ዕረፉ” የሚለው የዕብራይስጥ ቃል “ራፋኽ (רפה – râphâh) የሚያሳያን፣ ራስን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ሁሉን ገዢነት አሳልፎ መስጠት፣ በእርሱ ላይ መውደቅ፣ የትም ከማያደርስ አድካሚ የራስ ጥረት ከመባከን፣ ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ መደገፍ፣ መልስ የሌለውን የጊዜውን ጥያቄ ለእርሱ መተው፣ መውጫ የሌለው የሚመስለውን የጊዜውን የመከራ ሽክርክሪት ከመታገል ይልቅ፣ “እግዚአብሔር መውጫ አለው” ብሎ ማረፍ፣ ከእጃችን ወጥቷል፣ አብቅቶለታል ያልነውን ጉዳይ ከመጨነቅ ይልቅ፣ ከልዑሉ ዐይኖች አልተሰወሩም ብሎ በእርሱ ላይ ጥሎ ማረፍ … በአጠቃላይ ሕይወትን ሁሉ በእርሱ፣ “በታላቁ እኔ – THE GREAT I AM” ላይ ማሳረፍን ያመለክታል!

በዚህ ዓለም ዐቀፍ የጤና መታወክና የመኖር ዋስትና በተናጋበት ወቅት፦

  • ከመጨነቅ ይልቅ፣ በመጸለይ፤
  • እንደ ባለ አእምሮ በማሰብ፣ የጤና ባለሙያዎችን ምክር በመስማትና የመንግሥትን ትእዛዝ በማክበር የሚቻለውን ጥንቃቄ ለራስም፣ ለሌችም ማድረግ፤
  • እርስ በእርስ በርኅራኄ ዐይን መመልከት፣ በተለይም ደካሞችን፣ ሕሙማንና የተቸገሩትን ማሰብ፤
  • የሚመጣውን የእግዚአብሔርን መንግሥት በጽናትና በትዕግሥት እንደሚጠባበቅ የክርስቶስ ማኅበረ ሰብ የቆምንበት መሠረት መፈተሽ (በርግጥ ይህን ሁልጊዜ ማድረግ አለብን፤ ሆኖም እንደዚህ ዐይነት ዓለምን ግራ የሚያጋቡ ቀውሶች ደግሞ፣ የበለጠ እንድናስብ የሚያደርጉ የማንቂያ ደውል እንደሆኑ ልናስብ ይገባል)፤
  • ከእግዚአብሔርም ጋር ሆነ እርስ በእርስ ያለንን የግንኙነት ጤነንት መፈተሽ፤ ሕይወት ዐጭርና የፍጻሜዋም መንገድ አይታወቅምና፤
  • የወንጌልን የመጨረሻ ተስፋ ሰጪነት እንደገና በትኩረት ማሰብና የመኖራችንና የተልእኳችንን ዋና ምክንያት እንደገና መቃኘት፤
  • “ዕረፉ፣ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ” ባለው ጌታ ማረፍ!

የሃይድልበርግ የሃይማኖት ማስተማርያ መግቢያውን ልተውላችሁ፦

That I am not my own,
but belong with body and soul,
both in life and in death,
to my faithful Saviour Jesus Christ.
(Heidelberg Catechism)

ጌታ እግዚአብሔር በያለንበት፣ አገራችንንም በምሕረቱና በጥበቃው ይሸፍን፤ የተጎዱ አገራትንም ያስብ። አሜን!

Girma Bekele (Ph.D.)

ለምን ተወለደ?

የጌታችንን ልደት በምናስብበት በዚህ ሰሞን፣ “ተወለደ” የሚለው ቃል የተሸከመው ነገረ መለኮታዊ ጭብጥ እጅግ የገዘፈና ፋይዳው ያየለ መሆኑን ሳምሶን ጥላሁን እንደሚከተለው ያብራራል።

ተጨማሪ ያንብቡ

ርብቃ – የእስራኤል እናት

በዚህች አጭር መጣጥፍ እስራኤልን እስራኤል ስላደረገች እናት ለማየት እንሞክራለን። እስራኤላውያን ጠንካራ ሕዝቦች ናቸው። በየቀኑ በዜና ስለ እነሱ ሳንሰማ ማደር አንችልም። አባታቸው ያዕቆብ እግዚአብሔር በሚገርም መልኩ መርጦ የታላቅ ወንድሙ የዔሳው የበላይ ያደረው የእግዚአብሔር ሰው ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.