[the_ad_group id=”107″]

ለማነጽ እንሠራለን!

ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር፣ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ስለ ወንጌሉ እውነት እንዲሁም እርሱ ስለ መሠረታት ቤተ ክርስቲያን ግድ የሚላቸው ሰዎች ተሰባስበው ያቋቋሙት መንፈሳዊ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ በምድራችን ላይ ያለችው ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን፣ ክርስቶስን መስላ እንድታድግ በሚደረገው የማነጽ ሂደት ውስጥ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ያለመ ነው፡፡ ስያሜውም ይህንኑ የሚገልጽ ነው፤ “ሕንጸት” የግዕዝ ቃል ሲሆን፣ “ማነጽ” ወይም “መገንባት” የሚለውን ፍቺ ይይዛል፡፡

ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር በተግባራቱ በኩል ተፈጽሞ ማየት የሚፈልገው ራእይ አለው፤ ይህም፡- “የወንጌላዊያን ክርስቲያን ማኅበረ ሰብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ ክርስቲያናዊ አስተምህሮ እና ሥነ ምግባር ላይ ታንጾ፣ የወንጌል ተልእኮውን ሲወጣ ማየት፡፡” የሚል ነው፡፡

ሕንጸት መጽሔት ማኅበሩ ራእዩን ለማሳካት ከሚጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ ነው፡፡ ሕንጸት መጽሔት በይዘትም ሆነ በቅርጽ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡ ይህንን ስንል ሥራችን እንከን አልባ ነው ማለታችን አይደለም፤ ይልቁን በተሻለ ደረጃ ለማገልገል ብዙ እንደሚቀረን እናምናለን፡፡ የመጽሔቱ ስያሜ እንደሚጠቁመው፣ የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ብቻ እግዚአብሔር የሰጠንን ጉልበትና ጊዜ እንደምንጠቀም ተስፋ እናደርጋለን፡፡

ማኅበሩ እውን እንዲሆን በርካታ ሰዎችና ተቋማት ዐይነቱ የተለያየ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ልንሠራ ያሰብነውን በነገርናቸው ጊዜ በራእያችን በማመን አብሮነታቸውን የገለጹልንንና ሐሳባቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን የሰጡንን ወገኖቻችንን ልናመሰግን እንወዳለን፡፡

ለሕንጸት አንባቢያንን በአጠቃላይ የምንለው ቢኖር፣ የምንጽፈውን በማንበብ ሐሳባችሁንና አስተያየታችሁን እንድታካፍሉን በአክብሮት እየጠየቅን፣ እውነት ያለበትን፣ ቅንነት የሞላበትንና ለእግዚአብሔርና ለመንግሥቱ የሚሆነውን ምክር ሁሉ እንደምንሰማ ርግጠኞች በመሆን ነው፡፡ እናገለግለው ዘንድ ዕድል የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን!

ቅዱስ መንፈስም ይለያል!

በደግም ቀን ሆነ በክፉዉም ዘመናት ክርስቶስን እና እውነተኛ ትምህርቱን የሚገልጠው መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ሊሆን ይገባል ስንል በብዙ ምክንያቶች ነው። አንድም ዙሪያችን በብዙ እንቅስቃሴዎች የተሞላ በመሆኑ በተፈጥሮውም ሆነ በመንፈሳዊው ዓለም ብቻችንን አይደለንምንና ነው። አንድም በአንዱ መንፈስ ቅዱስ የማይገዛ ሕይወት፣ ትምህርት እና አገልግሎት ለሌሎች ብዙ መንፈሶች ጥቃት ስለሚጋለጥ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ

ጥልቅ ዐሳቢው ጳጳስ

ስመ ጥር ካደረጉትና ዝናን ካጎናጸፉት መጻሕፍቱ መካከል፣ “ኑዛዜ” የተሰኘውን ጥራዝ ሳይጠቅስ የሚያልፍ ጸሐፊ አለ ለማለት ያስቸግራል፤ “ጌታ ሆይ፤ ለራስህ ስትል ስለ ፈጠርከን ልባችን በአንተ ላይ እስኪያርፍ ድረስ የትም ይባክናል” የተሰኘውና ተደጋግሞ የሚነሣው ኀይለ ቃልም ከዚሁ መጽሐፍ ነው ተመዞ የወጣው።

ተጨማሪ ያንብቡ

ክርስትና ወደ ኢትዮያ መቼ ገባ?

“የተላኩ” በተሰኘው ዐምድ፣ ገናዬ ዕሸቱ ከምታስነብባቸው ተከታታይ ጽሑፎች ሁለተኛው የሆነው ይህ ጽሑፍ፣ ወንጌል ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል ተብሎ የሚታመንባቸውን ዘመናትና የአገባብ ሒደቶች ቀረብ አድርጋ ታስቃኘናለች።

ተጨማሪ ያንብቡ

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.