
የመጽሐፍ ቅኝት:- በዚያን ጊዜ
ርእስ፡- በዚያን ጊዜ (ሁለተኛ ዕትም)
ጸሐፊ፡- ተስፋዬ ጋቢሶ
የታተመበት ዓመት፡- 2002 ዓ.ም.
አሳታሚ፡- የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲንያን
[the_ad_group id=”107″]
በአንዳንድ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም ሚኒስትሪ መሪዎችና አገልጋዮች ዙሪያ ያሉትን ድክመቶች አስመልከቶ ለየት ባለ ግልጽነትና ʻአሁንስ በዛʼ ብለው የተነሡ ይሆኑ? በሚያሰኙ ብዕሮች የተጻፉ የሚመስሉ ጠንከር ያሉ መልእክቶች በመጽሔቶች አማካይነት ብቅ ብቅ እያሉ ነው። ደስ ይላል።
በመንፈሳዊ ካባ ሥር በእግዚአብሔር ሕዝብና ቤት ላይ፣ በራሱ በእግዚአብሔር (በመንፈስ ቅዱስ) ስም ሽፋን የራስን ጥቅም ማጋበስ ያስተዛዝባል ተብሎ የሚታለፍበት ጊዜ ሊያከትም ይሆን? ያሰኛል። “ቤቱ ባለቤት አለው፤ እግዚአብሔር ሁሉን ይቆጣጠራል፤ እኔ ኦዲተር አይደለሁም” ወዘተ… ሲል የኖረው ቅን አማኝ አንዳንድ አገልጋዮችና መሪዎች ሲፈጽሙት የኖሩትን አሳፋሪና አሳዛኝ ተግባር በቃ ለማለት መንደርደር የጀመረ ይመስላል። ጽዋ ሲሞላ የሚሆነው እንደሱ ነው።
ጽዋ ሲሞላ ነገር እንደ ቀድሞው አልሆን ይላል። ጽዋ ሲሞላ በመንፈሳዊ ቃላት ጋጋታ ምዕመንን ማደናዘዝና በመሰል መንገድ እየሸነገሉ መቀጠል የማይታሰብ ይሆናል። ጽዋ ሲሞላ የችግሩ አካል የችግሩ ፈቺ ካልሆንኩ እያለ የሚጫወተው የመንታ ገጸ ባሕርይ አጃጃይ ትወና ይነቃበትና ያከትማል።
አጥፊ ከጥፋቱ ካልተመለሰ ጽዋ የመሙላቱም ሆነ ምዕመኑ ጥያቄ የማንሣቱ ነገር ደግሞ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር አይቀሬ ነው። አንዳንድ ሰባኪዎች ላይ እንደሚስተዋለው ለራሳቸው የግል ዓላማ መዳረሻ ለማድረግ የእግዚአብሔርን ቃል አጣምመው ለመስበክ ካልፈሩ፤ አስተማሪዎች የከበረውን የሕይወት ቃል ዓላማ “ስለ ብር እና ወርቅ ነው” በማለት በአደባባይ የይሉኝታ የሐሰት ትምህርትን ከማስፋፋት ካልተቆጠቡና ወደ ሕዝቡ ኪስ መዝለቂያ አድርገው ሊጠቀሙበት ከደፈሩ፤ እውነተኛ ነቢያት እንዳሉ ሁሉ አንዳንድ “ነቢያት ነን” ባዮች የሰሚውን መሻት እየሰለሉ፣ በመረጃ ላይ እየተመሠረቱ፣ የአካባቢ ሁኔታዎችን እያንተራሱ ከእግዚአብሔር ያልሰሙትንና ያልተቀበሉትን ከእርሱ በማስመሰል የሐሰት ትንቢትን ከዘሩና ለዚህም ስጦታ ከተቀበሉ፤ “መዝገብህ በሰማይ ነው፤ ምድራዊው ከንቱና አላፊ ነው በምድር መዝገብ አትሰብስብ” ብለው በሰበኩትና መክሊቱን በተቀበሉት ሕዝብ መካከል እነሱ የደለበ አካውንት እንዲሁም የቅንጦት መኪናዎችና ቤቶች ባለቤቶች ሲሆኑና ከንቱ ያሉትን ምድራዊ ሸቀጥ ለማጋበስ እንቅልፍ ሲያጡ ጽዋ እየሞላ ይሄዳል፤ ምዕመኑም “ለምን? እንዴት?” ማለቱን ይቀጥላል።
በግንቦት ወር 2006 ዓ.ም. ቁጥር 002 ሕንጸት መጽሔት “ልዩ ወንጌል” በሚል ርእስ ሥር በወጣው ጽሑፍ፣ ጸሐፊው ያነሡት የሚከተለው መሠረታዊ ጥያቄ ለዚህ እውነታ አመላካች ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
“ከጥቂት ዓመታት በፊት ድኽነት ያንገላታቸው የነበሩ ʻአገልጋዮችʼ ነጥቀውም ሆነ ገንጥለው በከፈቱት ቤተ ክርስቲያን መሪ በሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ በከተማችን ካሉ ባለጠጎች ጋር ሊያስደምራቸው የሚችል ሀብትን እንዴት ሊያገኙ ቻሉ?”
ይህ ጥያቄ በውል የገባኝ አንዳንድ ወንጌላውያን ሰባኪዎች ጥቅስ ካነበቡልን በኋላ ወደ ገለጻ ሲገቡ እንደሚያደርጉት እንደሚከተለው ካስቀመጥኩት በኋላ ነው።
1ኛ. አገልጋዮች ናቸው (ነጋዴዎች ወይም በሌላ ሥራ የሚተዳደሩ አይደሉም)፤
2ኛ. ከጥቂት ዓመታት በፊት ምንም አልነበራቸውም (አገልግሎት ከመጀመራቸው በፊት ወይም ሲጀምሩ ቤሳ ቤስቲን አልነበራቸውም)፤
3ኛ. ስለሆነም ድኽነት ያንገላታቸው ነበር፤
4ኛ. ወይ ነጥቀው ወይ ገንጥለው ቤተ ክርስቲያን ከፈቱ (ራሳቸው ምዕመን አፍርተው ሳይሆን የሌሎችን አብያተ ክርስቲያናትን ምዕመን ወይ በቅሚያ ወይ በፍልሚያ ወሰዱ)፤
5ኛ. ራሳቸውን አገልጋይ ወይም መሪ አድርገው ሾሙ (ራሳቸውን ፓስተር፣ ወንጌላዊ፣ ወዘተ… ብለው ሰየሙ ወይም በጥቅም ተባባሪዎቻቸው አማካይነት ተሰየሙ)፤ 6ኛ. በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ከበርቴዎች ሆኑ (በቀላሉ፣ በፍጥነት ሀብት አጋበሱ)፤
7ኛ. የሀብታቸው ብዛት በከተማችን ካሉ ከበርቴዎች ጋር ያስደምራቸዋል (ቱጃሮች ሆኑ)፤
8ኛ. እንዲህ ያለውን ሀብት እንዴት ሊያገኙ ቻሉ? . . . እኛ እንጃ!
ይህ የጸሐፊው ብቻ ጥያቄ አይመስለኝም … የእርስዎ፣ ያንተ፣ ያንቺ፣ የእኔ፣ የእኛ የሁላችንስ ጥያቄ አይደለምን? እናንተ ጉዳዩ የሚመለከታችሁ አገልጋዮቻችንና የቤተ ክርስቲያንና የሚኒስትሪ መሪዎች እስቲ መልሱልን፤ ʻእውነት እንዲህ ያለ ሀብት አላችሁ? ካላችሁ እንዴት ልታገኙ ቻላችሁ?ʼ በርግጥ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያለተጠያቂነት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያለአግባብ ማንቀሳቀስ እንዲህ ቀሏችኋል ማለት ነው? ይህ በሚሊዮኖች የሚቆጠር አማኝ ሕዝብ ጥያቄ ሊሆን እንደሚችልስ ዐስባችሁ ታውቃላችሁ? ሁሉም ይቅርና የአገልጋዮች ስም በበጎም ሆነ በክፉ ሲነሣ እናገለግለዋለን የምንለውና ያዳነን የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ስም እንዲሁም የአማኙ ሁሉ ስም አብሮ መነሣቱን እውን አጥታችሁት ነው? እናም አማኙ ወገናችሁ “ለምን?” ብሎ ቢጠይቃችሁ ሊበዛበት ነው?
ጥያቄዎቹ ጥልቅና በሁሉ ላይ የተወረወሩ አይደሉም። ወደ አንዳንድ ምናልባትም ቁጥራቸው ጥቂት ወደ ሆነ ወንጌላውያን መሪዎችና አገልጋዮች ብቻ ያነጣጠሩ ናቸው። ብዙ በጎ ሥራና ፍሬ እንዲሁም መልካም ሕይወት ያላቸው አገልጋዮችና መሪዎች አሉና! ስለ እነርሱ እግዚአብሔር ይመስገን። እናከብራቸዋለን። እነሱንና መልካም አርአያነታቸውን ስናስብ የወደቀ ልባችን ይጽናናል። እነሱንና የነሱ የሆኑትን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካቸው።
ለመሆኑ በአንዳንዶች ዘንድ የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ የሕዝብ ሀብት መሆኑ ታውቆ አግባብ ባለው፣ ሕጋዊና ሙያዊ በሆነ መንገድ ሒሳብን በወቅቱ ኦዲት የማድረግ አሠራር አለ? ቀድሞውንስ የሒሳብ አያያዙ ለብክነትና ለስርቆት በማያጋልጥ መልኩ ሥርዐት ተዘርግቶለታል?
የፋይናንስ እንቅስቃሴው ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መንገድ የሚካሄድ ነው? በቤተ ክርስቲያንና በሚኒስትሪዎች ስም ያለ አግባብ ገንዘብ ሲበዘበዝስ የሚመለከታቸውና ኀላፊነቱ ያለባቸው ክፍሎችስ የሚያደርጉት ምንድነው? ከናካቴው ኀላፊነትና ተጠያቂነትስ አለ? እነዚህና መሰል ጥያቄዎችን ተገቢ መልስ ሳንሰጣቸው አድበስብሰን ብናልፍ በእግዚአብሔርም በሰውም፣ ምናልባትም በሕግም ፊት ተጠያቂ ያደርጉን ይሆናል።
መልሱ ደግሞ እንዲህ መሰሉ ሐሳብና ጥያቄ በተነሣ ቁጥር “የኤልዛቤል፣ የሐማ፣ የአማሌቅ፣ የእከሌ መንፈስ ነው” የሚል ማደናገሪያ ሊሆን አይችልም። መልሱ “ይህ የጠላት ሥራ ነው፤ ይህ የወንድሞች ከሳሽ የዲያቢሎስ ሥራ ነው፤ ይህን የሚሉት የመንፈስ ቅዱስን ሥራ የሚቃወሙ ናቸው” የሚል ማምታታትም ሊሆን አይችልም። ወይም ደግሞ “ሞትም ሕይወትም በምላስ እጅ ናቸው” እያሉና መሰል ጥቅሶችን ያለ ቦታቸው እየሰነቀሩ ሰዎችን ገለልተኛ ለማድረግና ለማለዘብ መሞከርም መልስ ሊሆን አይችልም። ይህ ዘዴ የሠራበት ጊዜ ኖሮ ሊሆን ይችላል። ጽዋ ሲሞላ ግን ይህን ማድረግ በራሱ ጥያቄውን እያከረረው ከመሄድ በቀር መፍትሔ አይሆንም። አንድ አባባል አለ፤ ማን እንዳለው አሁን አላስታውስም፤ የድሮው የአሜሪካ ፕሬዚደንት አብርሃም ሊንከን ሳይሆኑ አይቀርም። “አንድን ሰው ሁልጊዜ ማታለል ይቻላል። ሁሉንም ሰው አንድ ጊዜ ማታለል ይቻል ይሆናል። ሁሉንም ሰው ሁልጊዜ ማታለል ግን የማይቻል ነው።”
ስለዚህ መልሱ እውነትን ተቀብሎ ፍሬ ባለው ንስሐ ራስን ከራስ ጋር፣ ከሕዝቡና ከእግዚአብሔር ጋር ማስታረቅ ነው። መልሱ የሕዝቡንና የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ ለባለቤቱ መመለስ ነው፤ ለወደፊቱ ደግሞ እጅን መሰብሰብ ነው። መልሱ እንደሚሰብኩት ለጽድቅና ለእውነት መኖር ነው። “እውነትም አርነት ያወጣል” እንዲል ቃሉ።
አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሆኜ ያነበብኩትን አንድ ትውስታዬን አካፍያችሁ እንለያይ። እባቡ በጠርሙስ ሙሉ የነበረውን ወተት እየጠጣ ወተቱ በጎደለና በወረደ ቁጥር አካሉ ወደ ጠርሙሱ እየገባ ይሄድና በጠርሙሱ ውስጥ የነበረውን ወተት ጠጥቶ ይጨርሳል። አሁን ከጠርሙሱ ውስጥ ተመልሶ ለመውጣት ይሞክራል። ይሄኔ ግቢ ነፍስ ውጪ ነፍስ ይሆናል። ቀጭን የነበረውና አሁን ግን ወተቱን ጠጥቶ የተነፋፋው እባብ ከጠርሙሱ ውስጥ ተመልሶ ለመውጣት የነበረው ምርጫ አንድ ብቻ ነበር፤ ወተቱን መልሶ መትፋት። ይሄ ለእባብ ነው። ሰው ሲሆን ደግሞ “ለምን እንዲህ አደረግህ? ያላግባብ የማይገባህን ወስደሃል … ኀጢአት ነው … ወንጀል ነው” ማለትንና መባባልን ሊያስከትል ይችላል።
ይህን መሰሉ ኪሳራና ውድቀት ደግሞ ማንም የማይደሰትበት የአማኞች ሁሉ የልብ ስብራት ነው። የወንጌል አደራን የሰጠንን ታላቁን ጌታ በአክብሮት፣ በፍርሃትና በታማኝነት እናገለግለው ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳን።
Share this article:
ርእስ፡- በዚያን ጊዜ (ሁለተኛ ዕትም)
ጸሐፊ፡- ተስፋዬ ጋቢሶ
የታተመበት ዓመት፡- 2002 ዓ.ም.
አሳታሚ፡- የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲንያን
ለወንጌል ሥራ ስላለው ጠቃሜታ ብዙ የተባለለት የብዙኀን መገናኛ በእኛ አገር የአቅሙን ያህል እንዳልተጠቀምንበት ለብዙዎች የተሰወረ አይደለም፡፡ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች አንድም ከግንዛቤ ጉድለት፣ አንድም ደግሞ ከፍላጎት ማጣት የተነሣ ቸል ያሉት ይህ የአገልግሎት ዘርፍ አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊነቱ ጎልቶ እየታየ መጥቷል፡፡
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.
Add comment