[the_ad_group id=”107″]

የ2016 ዓ.ም የ”ሕንጸት የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት” ተከናወነ

ዓመታዊው የ”ሕንጸት የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት” ቅዳሜ የካቲት 23፥ 2016 ዓ.ም. በሳፋየር አዲስ ሆቴል ተከናወነ። መርሓ ግብሩ በ2015 ዓ.ም. በክርስቲያን ወንጌል አማኝ ጸሓፍያን ተጽፈው ከተዘጋጁና ለመጨረሻው ዙር በዕጩነት ከቀረቡት መካከል፣ በተመረጡ ዳኞች እንዲሁም በሕዝብ ድምፅ ላይ በመመሥረት አሸናፊዎች ይፋ የሆኑበት ነበር።

Read More »

ዊክሊፍ ኢትዮጵያ ዐሥረኛ ዓመቱን አከበረ

ዊክሊፍ ኢትዮጵያ የተመሠረተበትን ዐሥረኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ። ጥር 25 እና 26 2016 ዓ.ም. በተካሄዱ የተለያዩ ዝግጅቶች የተከበረው የተቋሙ የምሥረታ በዓል፣ አራት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕሞች የተመረቁበት እንዲሁም የዋና ጽ/ቤቱ ሕንጻ የተመረቀበት ነበር።

Read More »

የሰላም አማራጭ ማኅበረ ሰብ መሆን ስለሚቻልበት መንገድ አመላካች ሴሚናር ተካሄደ

በሕንጸት ከርስቲያናዊ ማኅበር እና ዊክሊፍ ኢትዮጵያ አዘጋጅነት፣ ወንጌላውያን አማኞች ኢትዮጵያ እያለፈችበት ባለው የሰላም ዕጦት ሊያበረክቱት ስለሚችሉት አስተዋጽዖ የሚጠቁም ሴሚናር ተዘጋጀ።

Read More »

የቤተ ክርስቲያን የመድረክ አገልግሎት ከባድ ፈተና ላይ መውደቁ ተነገረ

የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የመድረክ አገልግሎቶች ከፍተኛ የሆነ ችግር እንደ ገጠማቸው ተገለጸ። ይህ የተገለጸው፣ በአዲሰ አበባ ያሉ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት መሪዎች በተገኙበት ሴሚናር ላይ ነው። ሴሚናሩ የተካሄደው ማክሰኞ ጥቅምት 27 ቀን፥ 2016 ዓ.ም.፣ በኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቸርች (IEC) ነው። በውይይት መድረኩ ላይ ከሦስት መቶ በላይ የሚሆኑ የአጥቢያ መሪዎች ተገኝተዋል።

Read More »

የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በዘመናችን – ክፍል ሦስት

Under construction በተሰኘው የሕንጸት ዝግጅት፣ “የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በዘመናችን” በሚል ርእስ፣ እምነተአብ፣ ኢብሳ፣ ሙላቷ እና የአምላክ ያደረጉት ውይይት የመጨረሻው ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል። በዚህ ክፍል ቤተ ክርስቲያን የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በተመለከተ ሊኖራት ስለሚገባውን ምላሽ ተዳስሷል። ዐብራችሁን ቆዩ።

Read More »

የማቴዎስ ወንጌል አስተንትኖ – ተካልኝ ዱጉማ (ዶ/ር) 

“ጸሓፍት” በተሰኘው ዝግጅት፣ ሕንጸት በዊክሊፍ ኢትዮጵያ የትርጕም አማካሪ እንዲሁም የሥነ መለኮት አጥኚ ከሆነው ተካልኝ ዱጉማ (ዶ/ር) ጋር “የማቴዎስ ወንጌል” በተሰኘው የአስተንትኖ መጽሐፉ ዙሪያ ቈይታ አድርጓል፤ ይመልከቱ።

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.