[the_ad_group id=”107″]
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ኅብረት አራት ነቢያትንና ቤተ እምነቶቻቸውን በአጋር አባልነት መቀበሉ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሥቶበታል። ሕንጸት ጉዳዩን የተከታተሉትን ሰዎች አነጋግሮ የሚከተለውን አቅርቧል።
በዚህ ልዩ ዕትም፣ ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው እስክንድር ነጋ የሕንጸት ዕንግዳ ሆኖ ቀርቧል። አገራችን ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችና ዴሞክራሲ የሚከበሩባት አገር እንድትሆን መሥዋዕትነትን የጠየቀ ትግል አድርገዋል ከሚባሉት ግለ ሰቦች መካከል አንዱ እስክንድር ነው። በዚህም፥ ከዘጠኝ ጊዜያት በላይ ደጋግሞ ለእስር የተዳረገው እስክንድር፣ በአጠቃላይ ከዘጠኝ ዓመታት በላይ በእስር አሳልፏል።
አገራችን ኢትዮጵያ በለውጥ ሂደት ላይ እንዳለች በብዙዎች ዘንድ መግባባት አለ። የተጀመረው ለውጥ የሚፈለገው ቦታ ላይ እንዲደርስ ሁሉንም የኅበረተ ሰብ ክፍል ማሳተፍ እንደሚያስፈልግ አሁንም በብዙዎች ዘንድ እምነት አለ። የወንጌላውያን አማኞች የኅብረተ ሰቡ አካል እንደመሆናችን ለአገራችን ሰላም፣ ፍትሕ እንዲሁም ብልጽግና የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። እስከ አሁን በነበረን አገራዊ ተሳትፎ ‘ብዙ ትኩረት አልሰጣችሁም’ ተብለን የምንወቀሰው እኛ ወንጌላውያን፣ ለዚህ ወቀሳ አዎንታዊ ምላሽ የምንሰጥበት ጊዜ ላይ እንዳለን ይሰማናል።
የሥነ መለኮት ጥናት በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያን አጭር ዕድሜ ያለው ነው፡፡ የዕድሜው ዕጥረት ከወንጌላውያን ክርስትና አጀማመር ጋር የራሱ ቁርኝት አለው፡፡ የአብያተ ክርስቲያናቱ የቆይታ ዘመን በአንጻራዊነት ከታየ አጭር የሚባል ነውና፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በርካታ ቤተ ክርስቲያናት፣ አጋር ቤተ ክርስቲያናትና ግለ ሰቦች የመጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤቶችን መክፈት ጀምረዋል፡፡ በመሠረቱ ይህን መሰሉ ጥረት ሊበረታታ ይገባል እንላለን፡፡ ይሁን እንጂ ጥረቱን ማበረታታት እንዳለ ሆኖ ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ እነዚህ ጉዳዮች በዋናነት ከትምህርት ጥራት ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡
በየዕለቱ በመገናኛ ብዙኀን የምንሰማው የጦርነት እና የግጭት ወሬ የምንኖርባትን ዓለም በሰቆቃ የተሞላች አድርጓታል፡፡ ጥላቻውና በቀለኝነቱም ከቀን ወደ ቀን እያየለ የሚመጣ እንጂ የሚበርድ አይመስልም፡፡
ለወንጌል ሥራ ስላለው ጠቃሜታ ብዙ የተባለለት የብዙኀን መገናኛ በእኛ አገር የአቅሙን ያህል እንዳልተጠቀምንበት ለብዙዎች የተሰወረ አይደለም፡፡ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች አንድም ከግንዛቤ ጉድለት፣ አንድም ደግሞ ከፍላጎት ማጣት የተነሣ ቸል ያሉት ይህ የአገልግሎት ዘርፍ አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊነቱ ጎልቶ እየታየ መጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ዕድገት የብዙ ነገሮች ድምር ውጤት ነው፡፡ ወንጌላዊቷ ቤተ ክርስቲያን ስትተከል፣ ስታብብና ስትጎመራ፣ ፍሬም ማፍራት ስትጀምር የዕርሻው ባለ ቤት እግዚአብሔር አብሯት ነበር፡፡ ከታየው ዕድገት ጀርባ የቤተ ክርስቲያን ራስ የሆነው ጌታ ክርስቶስ በሰጣቸው ጸጋ ብዙ የደከሙ ታማኝ አገልጋዮቹ ነበሩ፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን እዚህ እንድትደርስ ማዕረግ ያላቸውም ይሁኑ፣ ስም ያልወጣላቸው፣ ታሪክ የዘከራቸውም ይሁኑ እርሱ አንድዬ ብቻ የተመለከታቸው ብዙ የወንጌል አማኞች አሉ፡፡ እነሱ የከፈሉት ዋጋ በላይ በሰማይ፣ በከበረው መዝገብ ሰፍሯል፡፡ በዚህ ሁሉ ግን የመንግሥቱ ንጉሥ፣ የቤቱ ጌታ፣ የሥራው አለቃ እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን!
ሕንጸት፡- አእምሮ፣ አንጎል፣ ጭንቅላት ስንል ምን ማለታችን ነው? ዶ/ር ምሕረት፡- እንግዲህ አእምሮ በእንግሊዘኛው “mind” የምንለው ነው፤ አንጎል ደግሞ “brain” የምንለው ነገር ነው። ጭንቅላት በአጠቃላይ የሁለቱ
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.