[the_ad_group id=”107″]

ምልከታ

“በዚያ ያለውን እንድታደራጅ ተውሁህ!”

“አሁን ላይ፣ መከራው በኦርቶዶክስ እንደበዛባት፣ አንዳንዱንም መከራ በጋራ የተቀበልነው መሆኑን ሳስተውል፤ እንዲሁም እነርሱ (ኦርቶዶክሶቹ) እኛን የሚያሳድዱበት አጋጣሚ መኖሩን ስመለከት ለመደጋገፍ ዐብሮ መደራጀቱ ሊገፋበት እንደሚገባ ታይቶኛል።” የሚሉት ባንቱ ገብረ ማርያም፣ የግል ጕዟቸውን ባስቃኙበት በዚህ ጽሑፋቸው፣ ወንጌላውያንና ኦርቶዶክሳውያን ለመደጋገፍ አንድ ላይ የመደራጀታቸውን አስፈላጊነት ከተሞክሯቸው በመጥቀስ ይመክራሉ።

Read More »

እኵያ ወይም ደባል የሌለው ኦርቶዶክሳዊ እምነት

ዶ/ር ግርማ በቀለ በዚህ ጽሑፋቸው፣ ወንጌላውያን በጊዜ ሂደት እየተለማመዷቸው የመጡት ባሕላዊ እምነቶች ከወንጌል እምነት በተቃርኖ ያሉ ናቸው ሲል ይሞግታሉ። “የክርስቶስ ብቸኛ ቤዛዊ ሥራ ዋጅቶናል ስንል፣ ከኀጢአትና ባዕድ አምልኮ ጋር ትሥሥር ካለው ከየትኛውም ባሕል ጭምር ማለታችን ነው። . . . ይኸው እውነት በኢሬቻ ብቻ ላይ ሳይሆን፣ በሲዳማው ፍቼ ጨምበላላ፣ በወላይታው ጊፋታ፣ በሀዲያው ያሆዴ እንዲሁም በሌሎች ባሕላዊ በዓላት ላይ ባሉት ዕይታዎች ላይም አግባብነት አለው።” ይላሉ።

Read More »

አለንጋ እና ልጓም

“በአግባቡ የተገራ ፈረስ ለባለቤቱ ክብር ያመጣል። ወደ ጦር ሜዳ ቢያደርስም፣ ዋንጫ ቢያሸንፍም፣ ታርሶበት ቢያመርትም፣ ግልቢያ ቢያሳምርም ትርፉና ክብሩ ለባለቤቱ ነው! . . . ሰው እንደ ፈረስ ነው። ያለ አለንጋና ያለ ልጓም አይኖርም። ልከኛው ባለአለንጋ ግን እግዚአብሔር ነው። ሲሻውም ልጓም ይሆናል።” ጳውሎስ ፈቃዱ።

Read More »

“እግዚአብሔር፣ ያልተቀደሰች ቤተ ክርስቲያንን ፈጽሞውኑ መኖርያው አያደርግም” – ቻርልስ ሀደን ስፐርጀን

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)፣ የታዋቂውን እንግሊዛዊ የወንጌል ሰባኪና አስተማሪ ቻርልስ ሀደን ስፐርጀንን ግለ ታሪክ መነሻ አድርገው ባቀረቡት በዚህ ጽሑፍ፣ ስፐርጅን ያለፈበትን አስቸጋሪ የሕይወት ትግል፣ ስለ ወንጌል ንጽሕና ሲል የተጋፈጣቸውን ዕቡያን እንዲሁም፣ በጽናት የተደመደመውን የድል ሕይወት ያስቃኙናል።

Read More »

“ስለ ዘፈን” የሚለው የዘሪቱ ጽሑፍ

“ስለ ዘፈን” የተሰኘው የዘሪቱ ከበደ ጽሑፍ በሕንጸት ድረ ገጽ ላይ መነበቡን ተከትሎ፣ የተለያዩ ዐሳቦች ሲንሸራሸሩ ሰንብተዋል። ዘሪቱ ያነሣቻቸውን ሙግቶች በመደገፍም ሆነ በመቃወም ዐሳባቸውን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ላይ ካቀረቡት መካከል፣ ተስፋዬ ሮበሌ (ዶ/ር) አንዱ ናቸው። ዶ/ር ተስፋዬ በአራት ክፍል አዘጋጅተው በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ያስነበቡትን ጽሑፍ፣ በሕንጸት ድረ ገጽ ላይ እንዲነበብ በጠየቁት መሠረት የላኩልንን ጽሑፍ እንደሚከተለው አቀርበነዋል።

Read More »

የክርስቶስ ሞት ፋይዳዎች

ባትሴባህ ሰይፉ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ያለውን ፋይዳ፣ በዐምስት አንኳር ነጥቦች የምታስቃኝበትን ምጥን ጽሑፍ ያንብቡ።

Read More »

ስለ ዘፈን

ዘሪቱ ከበደ በሕንጸት ድረ ገጽ ላይ ለንባብ ባቀረበችው በዚህ ጽሑፍ፣ በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ እስከ አሁን በዘለቀው የዘፈን ጕዳይ ላይ ብያኔዋን ትሰጣለች። “ይህን ጕዳይ ሳነሣ ለዘፈን ጥብቅና ልቈም ፈልጌ አይደለም። ይሁን እንጂ፣ እውነትን መናገርም ሆነ መነጋገር አስፈላጊ እንደ ሆነ ደግሞ አምናለሁ።” የምትለው ዘሪቱ፣ ወደ ጌታ የመጣችበትን ሂደትና የተለማመደችውን መንፈሳዊ ሕይወት እያስቃኘች፣ አማኝ ማኅበረ ሰቡ በርእሰ ጕዳዩ ላይ ሊኖረው ስለሚገባ ግንዛቤ ዐሳቧን ታካፍላለች፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ናቸው ያለቻቸው ማስረጃዎቿንም ታቀርባለች። በዚህ ብቻ አታበቃም፤ በሙዚቃ ጥበብ ውስጥ መዝለቅ የሚሹ ክርስቲያን ወገኖች ሊኖራቸው ስለሚገባ መንፈሳዊ አመለካከትና መውሰድ ስለሚጠበቅባቸው ጥንቃቄ የምክር ቃል ታካፍላለች።

Read More »

መከራው እስካለ

“ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስደት ላይ እንደ ሆነች እየታየኝ ነው። መከራው ግን ስውር ነው። . . . ስደትን የወንጌላውያን ብቻ አድርጌ ሳስብ መኖሬና ቀድሞ ዘመን ‘ባደረገችው ነገር እግዚአብሔር እያስተማራት ይሆን እንዴ?’ የሚለው መልስ የማይፈልግ ጥያቄዬ ነበር። ይሁን እንጂ፣ እየሆነባት ያለው ከስደት ጋር አንድ መሆኑን በጭላንጭልም ቢሆን . . . እየተረዳሁት ነው።” ባንቱ ገብረ ማርያም

Read More »

በግ አንበሳው:- የኢየሱስ ክርስቶስ ልዕቀት 

አማረ ታቦር፣ “Seeing and Savoring Jesus Christ” ከተሰኘው የጆን ፓይፐር (መጋቢ) መጽሐፍ እየቀነጨበ ከሚያቀርበው ተከታታይ ጽሑፍ መካከል፣ “በግ’አንበሳው” ሲል ወደ አማርኛ የመለሰውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ውሕድ ማንነት የተብራራበትን ግሩም መልእክት ያንብቡ።

Read More »

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ክብር ነው

አማረ ታቦር፣ “Seeing and Savoring Jesus Christ” ከተሰኘው የመጋቢ ጆን ፓይፐር መጽሐፍ እየቀነጨበ የሚያቀርበውን ንባብ ሦስተኛ ክፍል እዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል። በዚህኛው የትርጉም ክፍል፣ ስለ ጌታችን ኢየሱስ መለኮትነት ሐተታ የተሰጠበት ሲሆን፣ ይህም መለኮታዊ ማንነት በስሞቹ መንጸባረቁን ያስቃኛል።


Read More »

ኢትዮጵያ የ“አረማዊ ደሴት”?


የእሬቻ በዓል በክርስቲያኑ ማኅበረ ሰብ መካከል መነጋገሪያ ሆኖ እንደ ሰነበተ ተከብሮ ዐልፏል። በዓሉ ተከብሮ ይለፍ እንጂ፣ መነጋገሪያነቱ አልቆመም፤ ምናልባትም ለመጭዎቹ ዘመናት እንዲሁ መነጋገሪያ እንደ ሆነ ይቀጥል ይሆናል። ባንቱ ገብረ ማርያም፣ “ኢትዮጵያ የ ‘አረማዊ ደሴት’?” ሲሉ የሰየሙት ይህ ጽሑፍ፣ በሮም ግዛት ዘመን የነበሩት ክርስቲያኖች፣ እንዲህ ላለው የአደባባይ በዓል የሰጡትን ምላሽ በታሪክ መነፅር እያስቃኙ፣ ለዛሬ ክርስቲያኖች መልእክት ያቀብላሉ። የባንቱ ገብረ ማርያም ጽሑፍ፣ የእሬቻ በዓልን በሚመለከት ለሚካሄደው ውይይት መፋፋት የራሱ ፋይዳ አለው በሚል እንደሚከተለው ለንባብ በቅቷል።

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.