[the_ad_group id=”107″]

ሕንጸትን በገንዘብ ይደግፉ!

አገልግሎታችን ራእዩን እንዲያሳካ የእርስዎ ድጋፍ ትልቅ ትርጕም አለው። የክርስቶስን ወንጌል አብረውን ለማገልገል ስለወደዱ እናመሰግናለን!

ለማነጽ እንሠራለን!

ለሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር የሚያደርጉትን የገንዘብ ድጋፍ በሚከተሉት የባንክ አድራሻዎች መላክ ይችላሉ፦

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
(Commercial Bank of Ethiopia)

ሒሳብ ቁጥር፦ 1000084820947

ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ
(Berhan International Bank)

ሒሳብ ቁጥር፦ 2600010008243

በውጭ አገር ነዋሪ ከሆኑ፥

ሕንጸት መጽሔት

ሕንጸት መጽሔት የሚኖረው ይዘት ከአሳታሚው እምነትና ፍልስፍና የሚመነጭ ነው፡፡ መጽሔቱ በወንጌል አማኝ ማኅበረ ሰቡ ዘንድ ትልቅ ተነባቢነትና ተኣማኒነት ያለው፣ አገልግሎቱም ዘመን ዘለቅ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም፣ ተቀባይነትና ዘላቂ ዕድሜ ያለው አገልግሎት ለመስጠት በሥራ ልዕቀት የሚያምን፣ ከክርስትና እምነት ጋር የሚጣጣም የጋዜጠኝነት ተግባራትን የሚጠቀም፣ የአማኝ ማኅበረ ሰቡን ውስጣዊም ሆኑ ውጫዊ ተግዳሮቶች በድፍረትና በጥበብ የሚያነሣ፣ ለአመክንዮ ትልቅ ስፍራን የሚሰጥና አማኝ ማኅበረ ሰቡን በዚህ መንገድ ለመቅረጽ እንዲሁም የአማኝ ማኅበረ ሰቡ ድምፅ የመሆን ግብ ሰንቆ የሚዘጋጅ ነው፡፡

ጥናት እና ምርምር

ይህ የአገልግሎት ክፍል የሚተገብረው፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናትን በሚመለከቱ ማናቸውም ጉዳዮች ላይ የምርምርና የጥናት ሥራዎችን ማከናውን ነው። ማኅበሩ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ውስጥ የተሰማሩ ወገኖችን በማሳተፍ፣ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ጥናቶችና ምርምሮች እንዲደረጉ ያመቻቻል፤ የተደረጉ ጥናቶችና ውጤቶቻቸውን ለሚመለከታቸው አካልት ያቀርባል፤ ያሳትማል።

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ

የሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ፣ በክርስቲያን ማኅበረ ሰቡ ዘንድ የንባብና የውይይት ባሕል እንዲዳበርና ብርቱ ጸሐፊያን እንዲጎለብቱ በሚል በወር አንድ ጊዜ የሚደረግ የመጽሐፍ ግምገማ/ውይይት ያካሄዳል፡፡

የእምነት መግለጫ

ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር ከዚህ በታች በተጠቀሱ የክርስትና አእማድ የእምነት አቋሞች ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ አገልግሎቱም በእነዚህ መሠረታውያን የእምነት አናቅጽ ውስጥ በተካተቱ አስተምህሮዎች የተገራ ነው፡፡

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.