[the_ad_group id=”107″]

የሕንጸት መጽሐፍ ክበብ 10ኛ ዓመት ተከበረ

June 15, 2023
cover

የሕንጸት መጽሐፍ ክበብ ላለፉት ዐሥርት ዓመታት ሲያከናውናቸው የነበረውን ተግባር ለመዘከር የ10ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ሰኔ 4 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. ልዩ በሆነ መርሓ ግብር አከበረ። ክብረ በዓሉ በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ የተከናወነ ሲሆን፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመጽሐፍ ክበቡ አባላት እና የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር ቤተ ሰቦች ተገኝተዋል።

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ፣ ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል “የውይይትና ሥልጠና መድረኮችን ማዘጋጀት በተሰኘው የአገልግሎት ክፍል ሥር የሚካተት ሲሆን፣ የንባብ ባሕል እንዲዳብር የበኵሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በክብረ በዓሉ እንደተወሳውም ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ “ቤሪያ” በተሰኘ ስያሜ በ2004 ዓ.ም. ወርኀዊ በሆነ መርሓ ግብር መጻሕፍትን በመገምገም የዐሳቡ ጠንሳሽ በሆነው ዳዊት ጸጋዬ የተጀመረ ነበር። በ2005 ዓ.ም. ተቋማዊ በሆነ መልኩ በሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር ሥር የሚካሄድ ቋሚ መርሓ ግብር በመሆን መቀጠል ችሏል።

በክብረ በዓሉ የመጽሐፍ ክበቡ የዐሥር ዓመታት ቈይታ በፎቶ ኤግዚቢሽን እና በጽሑፎች የተወሳ ሲሆን፣ የመጽሐፍ ክበቡ ታዳሚያን ስለ መጽሐፍ ክበቡ ምልከታቸውን እና የወደ ፊት ምኞታቸውን አጋርተዋል። በመርሓ ግብሩ ማጠቃለያ፣ ባለፉት ዐሥርት ዓመታት ለመጽሐፍ ክበቡ ልዩ ልዩ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት እና ግለ ሰቦች የምስክር ወረቀት የተበረከተ ሲሆን፣ ለመጽሐፍ ክበቡ መመሥረት ጕልሕ ሚና ለነበረው ዳዊት ጸጋዬ እጅግ ላቅ ያለ ዕውቅና ተሰጥቷል።

ይህ መርሓ ግብር፣ ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር ከተመሠረተ 10ኛ ዓመቱን መያዙን አስመልክቶ ከሚያከናውናቸው ዝግጅቶች መካከል የመጀመሪያው ነው።

1 comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

  • የአስር አመት ጉዞን ማሰብ እና ለዚህ ለመብቃት ምክንያት የሆነውን ጌታ ማመስገን ደስ ይላል::ሕንጸት ከትናንት በበለጠ ብዙ ተጋድሎ የሚጠይቁ አመታት ከፊቷ እንዳሉ እረዳለሁ ለዚህ ደግሞ መፍትሔው አብረን በመቆም መጽናት ነው::

Latest News

ስለ ቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠና ተሰጠ

“የቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት” የተሰኘ የግማሽ ቀን ሥልጠና ለተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች ተሰጠ። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በላቭ ኤንድ ኬር ማዕከል የተካሄደ ነበር። 

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.