[the_ad_group id=”107″]

17ኛው የአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ትምህርታዊ ጉባኤ ተካሄደ

April 3, 2018
17ኛው የአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ትምህርታዊ ጉባኤ ተካሄደ

ዐሥራ ሰባተኛው የፍረሜንቲየስ ሌክቸር በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድሕረ ምረቃ የሥነ መለኮት ት/ቤት ከመጋቢት 18 እስከ 21 2010 ዓ.ም. ተካሄደ።

“Divine Perfection and the Reality of God’s Self-Disclosure” በሚል ኀይለ ቃል ላይ ትምህርታዊ ገለጻ ያደረጉት በሴንት አንድሪው ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲ ሥር በሚገኘው ሴንት ሜሪ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት፥ ፕሮፌሰር አለን ቶራንስ ናቸው። በሦስቱ ቀናትም፥ “The continuing of priesthood of Christ and its implication, The priesthood of Christ and our understanding of God, The priesthood of Christ and christian ethics” በተሰኙ ንዑስ ርእሶች ገለጻ አድርገዋል።

በትምህርታዊ ገለጻው ላይ የተሳተፉ መምህራንና ተማሪዎች፥ ፕሮፌሰር ቶራንስ ስለ ክርስቶስ የክህነት አገልግሎት ሰፊ ግንዛቤ እንዳስጨበጧቸው ለሕንጸት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት በፍረሜንቲየስ ወይም በአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ስም የሰየመው ይህ ዓመታዊ ዝግጅት፥ በሥነ መለኮቱ ዓለም ምርምርና ጥናት ያደረጉ ምሁራንን በመጋበዝ በኢትዮጵያ ላሉ የነገረ መለኮት ተመራማሪዎችና ተማሪዎች እንዲሁም ፍላጎቱ ላላቸው ግለ ሰቦች ዕውቀትና ልምድ ለማካፈል በሚል የሚዘጋጅ ዓመታዊ ጉባኤ ነው። አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (ፍረሜንቲየስ) ክርስትናን ወደ ኢትዮጵያ ይዘው ከመጡና የመንግሥቱ ሃይማኖት እንዲሆን አስተዋጽኦ ካደረጉት መካከል እንደሆኑ ይታመናል።

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Latest News

ስለ ቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠና ተሰጠ

“የቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት” የተሰኘ የግማሽ ቀን ሥልጠና ለተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች ተሰጠ። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በላቭ ኤንድ ኬር ማዕከል የተካሄደ ነበር። 

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.