በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ከሰባ ዓመታት በላይ በወንጌል ሰባኪነታቸው የሚታወቁት ኪዳሞ ሜቻቶ በተወለዱ በ92 ዓመታቸው ትላንት ከሰዓት በኋላ አረፉ። ወ/ዊ ኪዳሞ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ በአጠቅላዩ የወንጌል አማኝ ዘንድ የሚከበሩ የወንጌል አገልጋይ ናቸው። የቀብር ሥነ ሥርዐታቸው ሐሙስ፣ ጥቅምት 6 2011 ዓ.ም. በ8 ሰዓት፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን የቀብር ሥፍራ እንደሚፈጸም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር ለቤተ ሰቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል