በቤዛ ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት በዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄደው “ተነሽ አፍሪካ” ኮንፈረንስ፣ ከጥር 29 እስከ የካቲት 3፥ 2011 ዓ.ም. በቤተ ክርስቲያኒቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተለያዩ መርሓ ግብሮች እንደሚካሄድ ተነገረ ። የዘንድሮ መሪ ቃል “ማንነታችንን፣ ሥርዐቶቻችንን እና ምድራችንን ለመዋጀት ጊዜው አሁን ነው” የተሰኘ ነው።
ከተለያዩ የዓለም ክፍል ተሳታፊዎች የሚታደሙበት ይህ ዓመታዊ ስብሰባ፣ በዐቢይነት በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚደረግበት ነው። ዘንድሮ ዐሥረኛ የምሥረታ በዓሉን ያከበራል የተበለው “ተነሽ አፍሪካ”፣ የአፍሪካ ኅብረት መደበኛ የመሪዎች ስብሰባን ተከትሎ የሚዘጋጅ እንደ ሆነ ለማወቅ ተችሏል።