[the_ad_group id=”107″]

April 11, 2016

“አምልኮና ሀልዎተ እግዚአብሔር” የተሰኘው መጽሐፍ ውይይት ተካሄደበት

“አምልኮና ሀልዎተ እግዚአብሔር” የተሰኘው መጽሐፍ ውይይት ተካሄደበት

“አምልኮና ሀልዎተ እግዚአብሔር” በሚል በእንዳልካቸው ሐዋዝ የተጻፈው መጽሐፍ እሑድ ሚያዚያ 2 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. በ9 ሰዓት በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ትምህርት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተካሄደበት፡፡

ለውይይት መነሻ ጽሑፍ ያቀረበው አቶ አዳነ አስናቀ ሲሆን፣ መጽሐፉ ከይዘትም ሆነ ከቅርጽ አንጻር ሊሻሻል ይገባል ያላቸውን ክፍተቶች፣ ብርቱ ናቸው ካላቸው ሐሳቦች ጋር አያይዞ አቅርቧል፡፡ ይህንን ተከትሎም ታዳሚያን ለጸሐፊው በርካታ ጥያቄዎችንና አስተያቶችን አቀርበዋል፡፡

የመጽሐፉ ጸሐፊ እንዳልካቸው ሐዋዝ ከገምጋሚውና ከታዳሚያን ለተነሡለት ጥያቄዎች መልስ ይሆናል ያለውን የሰጠ ሲሆን፣ ከግምገማውም ሆነ ከታዳሚያን ከቀረቡለት አስተያየቶች ጠቃሚ ትምህርት ማግኘቱንና ወደፊት መጽሐፉ ለዳግም ኅትመት ሲቀርብ የሚያስተካክላቸው ነገሮች እንዳሉት ጭምር ተናግሯል፡፡

በመጪው ግንቦት 7 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. ለውይይት የሚቀርበው መጽሐፍ በመጋቢ ስሜ ታደሰ የተጻፈውና “ምን ሠርተን እንለፍ?” የተሰኘው መጽሐፍ መሆኑ በዕለቱ ተገልጿል፡፡

Latest News

ለችግረኛ ቤተ ሰቦች የሚሆን የአንድ ወር ቀለብ ሰፈራ ሊደረግ ነው

የኮቪድ – 19 ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው የሥራና የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት፣ የከፋ ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላሉ ተብለው ለሚታሰቡ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች ለአንድ ወር ቀለብ የሚሆን ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያስችል ቅስቀሳ ተጀመረ።

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.