“ለዓለም እንጸልይ” የተሰኘ መጽሐፍ ዓርብ፣ የካቲት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ተመረቀ። መጽሐፉ ስለ ዓለም አገራት ዝርዝር መረጃን በመስጠት፣ ለአገራቱ ጸሎት እንዲደረግ የሚያስችል መመሪያን ያካተተ ነው።
መጽሐፉ ኦፕሬሽን ወርልድ ከተሰኘው የጄሰን ማንድሪክ መጽሐፍ (7ኛ ዕትም) ተውጣጥቶ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በኤስ አይ ኤም ሥነ ጽሑፍ አስተርጓሚነትና አሳታሚነት ለንባብ የቀረበ ነው። መጽሐፉን ወደ አማርኛ የመለሰችው ሔርሜላ ሰሎሞን ስትሆን፣ አርትኦቱን ዘነበ ገብረሐና ሠርቶታል።
በምረቃ ሥነ ሥርዐቱ ላይ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፣ የሥነ መለኮት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም በጸሎትና በሉላዊ ተልዕኮ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ አገልጋዮች መገኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል።