[the_ad_group id=”107″]

ለሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ሲሰጥ የቈየው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጠና ተጠናቀቀ

July 10, 2023
ተመራዊ ተማሪዎች ከመምህራኖቻቸው ጋር
ተመራዊ ተማሪዎች ከመምህራኖቻቸው ጋር

“Biblical Education By Extension (BEE World)” እና በዳላስ ያለችው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን በአጋርነት ሲያሠለጥኗቸው የነበሩትን ዐሥራ ሰባት የመጀመሪ ዙር ተማሪዎችን አስመረቁ።

ሥልጠናው የተሰጠው ከተለያዩ ቤተ እምነት ለመጡ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ሲሆን፣ ሠልጣኞቹ በአገልግሎት ስፍራቸው ሳሉ አገልግሎታቸውን በተሻለ መልኩ ማካሄድ እንዲችሉ የሚያስችሏቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሥነ መለኮታዊ ኮርሶች እንዲያገኙ የሚያስችሏቸው ናቸው ተብሏል። ሥልጠናው ላለፉት ሦስት ዓመታት በአዳማ ከተማ ሲሰጥ የቈየ ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ወደ አካባቢያቸው በመሄድ በዐሥራ ስድስት ቡድኖች ውስጥ ያሉ 256 ተማርዎችን በማሠልጠን ላይ መሆናቸው ተገልጿል። 

“BEE World” መቀመጫውን በአሜሪካን አገር ያደረገ ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም ሲሆን፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ላሉና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጠና ላላገኙ አገልጋዮች በፓስቶራል ሚኒስትሪ ዲፕሎማ፣ በቲዮሎጂና ቸርች ሊደርሺፕ አሶሺዬት ዲግሪ እንዲሁም በቲዮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጥ አገልግሎት ነው። 

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያ በዳላስ ከBEE World ጋር በአጋርነት ሲሰጡ የቆዩት ሥልጠና፣ በቀጣይነት በደብረ ብርሃን ከተማ የሚሰጥ ሲሆን፣ ከአካባቢው የሚመጡ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በሠልጠናው ተካፋይ እንደሚሆኑ ለሕንጸት የተደረሰው መረጃ ያስረዳል።

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Latest News

ስለ ቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠና ተሰጠ

“የቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት” የተሰኘ የግማሽ ቀን ሥልጠና ለተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች ተሰጠ። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በላቭ ኤንድ ኬር ማዕከል የተካሄደ ነበር። 

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.