“አካላዊ አስተሳሰብ” በሚል ርእስ የተጻፈው የአቢይ ታደለ (ኪያ) መጽሐፍ መስከረም 25 ቀን፥ 2012 ዓ.ም. በሐርመኒ ሆቴል ተመረቀ።
ጸሐፊው ባደረገው ንግግር አማኞች በክርስቶስ ውስጥ የተለያየ አካል ቢሆኑም፣ የተለያየ ሥራ እንዳላቸውና አንዱ አካል ለአንዱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።
አቢይ በመጽሐፉ ዝግጅት ወቅት በተለያየ ሁኔታ ያገዙትን እና በሕይወቱ ውስጥ አሻራ ያሳረፉትን ወገኖች አመስግኗል።
መጽሐፉ አንድ መቶ ሰማኒያ ገጾች ያሉት ሲሆን፣ በአንድ መቶ አምሳ ብር ይሸጣል።