[the_ad_group id=”107″]

January 14, 2019

“ፓሩሲያ” በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ውይይት ተካሄደ

“ፓሩሲያ” በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ውይይት ተካሄደ

“ፓሩሲያ፦ የኢየሱስ መምጣትና የዓለም መጨረሻ ምልክት (ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ገጽታ)” የተሰኘው የመጋቢ ኤልያስ ኪቲላ መጽሐፍ እሑድ ጥር 5 ቀን፥ 2011 ዓ.ም.፣ በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተካሄደበት። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት በሚካሄደው በዚህ ወርሓዊ የመጽሐፍ ግምገማ ላይ የተለያዩ ታዳሚያን የተገኙ ሲሆን፣ አስተያየታቸውና ጥያቄዎቻቸውንም ለጸሐፊው አቅርበዋል።

ስለ መጨረሻው ዘመንና ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣት ማብራሪያ የሚያቀርበው ይህ መጽሐፍ፣ በዋናነት “ቅድመ ሺህ ዓመት” የተሰኘውን የመጨረሻው ዘመን አመልካከት የሚያቀነቅን እንደ ሆነ በሐያሲው ተነግሯል። ሒሱን ያቀረበው የሥነ መለኮት ተማሪው ሄኖክ አፈወርቅ፣ መጽሐፉ ካሉት በጎ ጎኖች በተጨማሪ፣ ይዞት በተነሣው የሙግት ነጥብ ላይ ሊያተኩርባቸው ይገባል ያላቸውን ጭብጦች አስቃኝቷል። ጸሐፊው ከገምጋሚውም ሆነ ከአንባቢያን ለተነሡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ የቀረቡላቸውን አስተያየቶችም ከሞላ ጎደል እንደሚቀበሉ ገልጸዋል።

ቀጣዩ መርሓ ግብር የካቲት 3 ቀን፥ 2011 ዓ.ም. የሚካሄድ ሲሆን፣ ለውይይት የሚቀርበው መጽሐፍ “ከሚሽግዳ እስከ ዓለም ዳርቻ” የተሰኘውና በዶ/ር ተስፋ ጽዮን ደለለው ሕይወት ላይ የሚያተኩር ግለ ታሪክ ይሆናል።

Latest News

ለችግረኛ ቤተ ሰቦች የሚሆን የአንድ ወር ቀለብ ሰፈራ ሊደረግ ነው

የኮቪድ – 19 ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው የሥራና የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት፣ የከፋ ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላሉ ተብለው ለሚታሰቡ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች ለአንድ ወር ቀለብ የሚሆን ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያስችል ቅስቀሳ ተጀመረ።

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.