[the_ad_group id=”107″]

“የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊ አመጣጥ” በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ውይይት ተካሄደ

December 16, 2018
“የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊ አመጣጥ” በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ውይይት ተካሄደ

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ፣ በመምህር ያሬድ ሽፈራው የተጻፈውንና “የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊ አመጣጥ” (ቅጽ 1) የተሰኘውን መጽሐፍ፣ እሑድ ታኅሣሥ 7 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ጸሐፊው በተገኙበት ለውይይት አቀረበ።

ለውይይት መነሻ  ሐሳብ ያቀረቡት የሥነ መለኮት አጥኚና መምህር የሆኑት አቶ ዮናስ አስፋው ናቸው። አቶ ዮናስ በሒሳቸው እንዳመለከቱት መጽሐፉ ባነሣው ጭብጥ በዐይነቱ የመጀመሪያ ሊባል የሚችል እንደ ሆነ አብራርተዋል። በተለይም፣ ከስድሳ ስድስቱ የብሉይና ዐዲስ ኪዳን መጻሕፍት በተጨማሪነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተቀንነዋል ስለሚባሉት “አእዋልድ መጻሕፍት” በቂ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥራ በጸሐፊው መሠራቱን መስክረዋል። ጸሐፊው ከሐያሲውና ከአንባቢዎቻቸው ለተነሡላቸው አስተያየቶችና ጥያቄዎች መልስ ያሉትን የሰጡ ሲሆን፣ ቢያሻሽሉት ይበጃል በሚል የቀረቡላቸውን ጥቆማዎች ከሞላ ጎደል መቀባላቸውን ተናግረዋል።

በቀጣይ መርሓ ግብር ለውይይት የሚቀርበው መጽሐፍ በመጋቢ ኤልያስ ኪቲላ የተጻፈውና “ፓሩሲያ፦ የኢየሱስ መምጣትና የዓለም መጨረሻ ምልክት (የእግዚአብሔር መንግሥት ገጽታ)” የተሰኘው መጽሐፍ ሲሆን፣ ጥር 5 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት በዘጠኝ ሰዓት የሚገመገም መሆኑ ተገልጿል።

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Latest News

ስለ ቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠና ተሰጠ

“የቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት” የተሰኘ የግማሽ ቀን ሥልጠና ለተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች ተሰጠ። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በላቭ ኤንድ ኬር ማዕከል የተካሄደ ነበር። 

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.