[the_ad_group id=”107″]

“ክርስቲያናዊ ፌስቲቫል” ሊዘጋጅ ነው ተባለ

December 16, 2015
“ክርስቲያናዊ ፌስቲቫል” ሊዘጋጅ ነው ተባለ

በመጽሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን – ዛየን ቻፕል አዘጋጅነት “የክርስቲያን ፌስቲቫል ኢትዮጵያ 2008” የተሰኘ ዝግጅት ከታኅሣሥ 15 እስከ 17 2008 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪየም ቅጥር ግቢ ውስጥ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ፌስቲቫሉን ሠላሳ ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ታኅሣሥ 1 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. በሳሮ ማሪያ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደ ተገለጸው፣ የዝግጅቱ ቀዳሚ ዐላማ “ወንጌልን ለትውልድ ለማድረስ የዳበረ፣ ሁለንተናዊ አቅም ያለው እና የተጣመረ ማኅበረ ሰብ መፍጠር” መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም የክርስቲያን ድርጅቶችና የንግድ ተቋማት ትሥሥርን ማጎልበት ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር መሆኑን የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ማቲያስ ሠረቀ ብርሃን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

ፌስቲቫሉ ስለሚኖሩት መርሓ ግብሮች ዝርዝር ማብራሪያ የሰጡት የአዘጋጅ ቡድን አባል የሆኑት አቶ ዮሴፍ ጥላሁን ናቸው፡፡ አብያተ ክርስቲያናት፣ የተለያዩ ግብረ ሠናይ ድርጅቶችና የንግድ ተቋማት ራእያቸውን፣ አገልግሎታቸውንና ምርታቸውን የሚያስተዋውቁበት ዐውደ ርእይ፣ የክርስቲያን ነጋዴዎች የእርስ በእርስ የንግድ ውይይት፣ ለሕፃናት እና ወጣቶች የሚሆኑ አዝናኝና አስተማሪ ዝግጅቶች፣ ዝማሬዎችና የቃለ እግዚአብሔር ስብከቶች እንደሚኖሩ አቶ ዮሴፍ በመግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን በ1988 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የተቋቋመችና በአዲስ አበባ ሰባት የሚደርሱ አጥቢያዎች እንዲሁም ከአትዮጵያ ውጪ ሁለት እንዷላት የፌስቲቫሉ አዘጋጅ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ዋና መጋቢ የሆኑት መጋቢ ካሌብ ተድላ ገልጸዋል፡፡

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Latest News

ስለ ቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠና ተሰጠ

“የቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት” የተሰኘ የግማሽ ቀን ሥልጠና ለተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች ተሰጠ። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በላቭ ኤንድ ኬር ማዕከል የተካሄደ ነበር። 

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.