
የ2015 ዓ.ም. ሕንጸት የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት በፎቶ
በሕንጸት የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት ላይ ከተወሰዱ ፎቶዎች መካከል (ፎቶ በገናዬ ዕሸቱ)
[the_ad_group id=”107″]
ይህ የተገለጸው ሙስና በአማኝ ማኅበረ ሰቡ ላይ እያሳደረ ያለው ጫና ለመመዘን በሚል ሕንጸት ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ላይ ነው። የዳሰሳ ጥናቱ ከጷጕሜ 2014 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 2015 ዓ.ም. ድረስ፣ በበይነ መረብ (online) አማካኝነት በተሳታፊዎች ምላሽ ሲሰጥበት ቈይቷል። በዚህም 194 (አንድ መቶ ዘጠና አራት) ተሳታፊዎች ለመጠይቁ ምላሽ ሰጥተዋል።
በዳሰሳ ጥናቱ ላይ ከተሳተፉት ግማሽ ያህሉ (49.5 ከመቶ)፣ የወንጌላውያን ክርስትና አማኝ የሆኑት ከልጅነት ዕድሜያቸው ጀምሮ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ 26.3 ከመቶ የሚሆኑት ከ20 ዓመት በላይ፣ 17 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከ10 ዓመት በላይ በአማኝነት የቈዩ ናቸው።
91.2 ከመቶ የሚሆኑት የመጠይቁ መላሾች፣ በኢትዮጵያ የሙስና ደረጃው እየባሰበት እንዳለ የሚያምኑ ናቸው። ለዚህም ምክንያት አድርገው ከጠቈሟቸው ሰበቦች መካከል፣ የሞራል ውድቀት ትልቁን ስፍራ የሚይዝ ሲሆን፣ ሕግ የማስከበር ሥርዐቱ በቂ አለመሆኑና ሙስናን የሚበረታታ ባሕል መኖሩ ምክንያት ናቸው ተብሏል።
ለመጠይቅቱ ምላሽ ከሰጡ መካከል 87.1 ከመቶ የሚያህሉት ለሙስና ተጋልጠው እንደሚያውቁ ገልጸዋል። ከእነዚህም ውስጥ 95 ከመቶ በላይ የሚሆኑት እንዲህ ያለው ሁኔታ የገጠማቸው በመንግሥታዊ ተቋማት ውስጥ መሆኑን አመልክተዋል። ከመንግሥት ተቋማት በተጨማሪ፣ ከፍተኛ ሙስና ወይም የአስተዳደር ብልሹነት እንዳለባቸው የተጠቀሱት፣ የፋይናንስ ተቋማትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መሆናቸው በዳሰሳው ተመላክቷል።
የመጠይቁ መላሾች ጒቦ እንዲሰጡ ቢገደዱ፣ እንዴት ባለ ሁኔታ ጒቦ ሊሰጡ እንደሚችሉ ሲጠየቁ፣ ግማሽ ያህል የሚሆኑት (51.5 ከመቶ) በምንም ዐይነት ሁኔታ ጒቦ እንደማይሰጡ የገለጹ ሲሆን፣ የተቀሩት (48.5 ከመቶ) በምንም ሁኔታ ውስጥ ጒቦ ሊሰጡ እንደሚችሉ አመላክተዋል።
ጕቦ ሊሰጡ እንደሚችሉ ከገለጹት መካከል፣ 73.4 ከመቶ የሚሆኑት “አጣብቂኝ ውስጥ የሚከትት አስቸጋሪ ሁኔታ ሲገጥም” ብቻ ሊሰጡ እንደሚችሉ የተናገሩ ናቸው። 57.4 ከመቶዎቹ፣ “ከእንግልትና መጉላላት ለመዳን”፣ 30.1 ከመቶዎቹ “የዜግነት መብት የሆኑ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት”፣ 6.4 ከመቶዎቹ ደግሞ “ተጨማሪ ጥቅም ወይም ትርፍ ለማግኘት” ጒቦ ሊሰጡ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
“አጣብቂኝ ውስጥ የሚከትት አስቸጋሪ ሁኔታ ሲገጥም” ጕቦ ሊሰጡ እንደሚችሉ ምላሽ የሰጡ ከመጠይቁ ተሳታፊዎች መካከል 92.8 ከመቶ የሚሆኑት ከ10 ዓመት በላይ በወንጌላውያን ክርስትና እምነት ውስጥ የቈዩ ናቸው።
የዳሰሳ ጥናቱ በሕንጸት የጥናትና ምርምር የአገልግሎት ክፍል አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ የዳሰሳ ጥናቱን ሙሉ ሪፖርት የሚከተልውን ሊንክ ተጭነው ማግኘት ይችላሉ።
በሕንጸት የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት ላይ ከተወሰዱ ፎቶዎች መካከል (ፎቶ በገናዬ ዕሸቱ)
የሥላሴያውያን መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ያሳተመው “አዲስ ኪዳንና መጽሐፈ መዝሙር” የተሰኘ መጽሐፍ ቅዱስ ተመረቀ።
ከተመሠረተ ሃያ ዐምስት ዓመታትን ያስቈጠረው የኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት፣ ዛሬ ኅዳር 23 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በትምህርት ቤቱ መሰብሰቢያ አድራሽ የኢዮቤልዩ በዓሉን መዝጊያ ሥነ ሥርዐት አካሄዷል።
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.
Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.
Add comment