ለሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ሲሰጥ የቈየው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጠና ተጠናቀቀ
“Biblical Education By Extension (BEE World)” እና በዳላስ ያለችው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን በአጋርነት ሲያሠለጥኗቸው የነበሩትን ዐሥራ ሰባት የመጀመሪ ዙር ተማሪዎችን አስመረቁ።
[the_ad_group id=”107″]
የኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት ዶ/ር ምስጋና ማቴዎስን የተቋሙ አራተኛ ዳይሬክተር አድርጎ ሾመ፡፡ ታኅሣሥ 19 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. በት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው ሥነ ሥርዐት ላይ፣ “ኤግስት”ን በባለ ቤትነት የሚያስተዳድሩት የቤተ እምነት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የሥነ መለኮት ትምህርት ቤቱን ላለፉት ስምንት ዓመታት የመሩት ዶ/ር ደስታ ሄሊሶ የአገልግሎት ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው ነው አዲስ ዳይሬክተር መሾም ያስፈለገው፡፡ ዶ/ር ደስታ ተቋሙን በመሩባቸው ባለፉት ስምንት ዓመታት ት/ቤቱን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረሳቸውን በዕለቱ ተናጋሪ የነበሩ ግለ ሰቦች አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን፣ ስኬቶቻቸውን በማወደስ ምስጋና እና ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚደንት እና የኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ዋቅስዩም ኢዶሳ ባደረጉት ንግግር፣ ትምህርት ቤቱ በተሰናባቹ ዳይሬክተር አመራር ለደረሰበት አስተማማኝና የተረጋጋ ዕድገት ምስክር መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ “አራተኛውን የኤግስት ዳይሬክተር ስንሾም ወደ አዲስ ምእራፍ እየገባን ነው ያሉት” ዶ/ር ዋቅስዩም፣ የተቋሙን ዕድገት ለማስቀጠል ባለ ድርሻ አካላት ሙሉ ከአዲሱ አመራር ጎን እንደሚቆሙ ጠቁመዋል፡፡
ዶ/ር ደስታ ሄሊሶ በበኩላቸው፣ በእርሳቸው የአገልግሎት ዘመን ለተሠሩት ሥራዎችና ለመጣው ስኬት በቅደሚያ እግዚአብሔርን ቀጥሎም፣ የሥራ ባልደረቦቻቸውን፣ የቦርድ አመራር አባላትን እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ያሉ የተቋሙ ወዳጆችን አመስግነዋል፡፡
አዲሱ ተሿሚ ዶ/ር ምስጋና ማቴዎስ በሥነ መለኮት ትምህርት ዲፕሎማ እና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪየም፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ኖርዌይ አገር በሚገኘው “School of Mission and Theology – Stavanger” በ“Biblical Studies” አግኝተዋል፡፡ በማስከተልም በታላቋ ብሪታኒያ በሚገኘው “University of Gloucestershire” የPGD ትምህርታቸውን በ“Biblical Studies” ካጠኑ በኋላ፣ ከተመሳሳይ ተቋም የPhD ዲግሪያቸውን በ“Theology” አግኝተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ “Postdoctoral” ጥናታቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ዶ/ር ምስጋና ከአዲሱ የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ለመጪዎቹ አራት ዓመታት ት/ቤቱን በዳይሬክተርናት እንደሚመሩ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤትን የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እና የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በዋና የባለ ቤትነት የሚያስተዳድሩት ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት አነስተኛ ውክልና አለው፡፡ ዐሥራ ስምንት ዓመታት ያስቆጠረውን ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት የውጪ አገር ዜጋ የሆኑት ዶ/ር ፒተር ኮተሬል ሲሆኑ፣ እሳቸውን ተክተው ዶ/ር ደበላ ቢሪ ት/ቤቱን መርተዋል፡፡ እ.አ.አ. በ2007 ከዶ/ር ቢሪ ኀላፊነቱን የተረከቡትና ያለፉትን ስምንት ዓመታት የመሩት ዶ/ር ስታ ሄሊሶ ነበሩ፡፡
“Biblical Education By Extension (BEE World)” እና በዳላስ ያለችው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን በአጋርነት ሲያሠለጥኗቸው የነበሩትን ዐሥራ ሰባት የመጀመሪ ዙር ተማሪዎችን አስመረቁ።
የሕንጸት መጽሐፍ ክበብ ላለፉት ዐሥርት ዓመታት ሲያከናውናቸው የነበረውን ተግባር ለመዘከር የ10ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ሰኔ 4 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. ልዩ በሆነ መርሓ ግብር አከበረ። ክብረ
“የቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት” የተሰኘ የግማሽ ቀን ሥልጠና ለተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች ተሰጠ። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በላቭ ኤንድ ኬር ማዕከል የተካሄደ ነበር።
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.

Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.
Add comment