[the_ad_group id=”107″]

“ፈለገ ብርሃኑ” የተሰኘው መጽሐፍ በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ ውይይት ተደረገበት

November 18, 2015
“ፈለገ ብርሃኑ” የተሰኘው መጽሐፍ በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ ውይይት ተደረገበት

“ፈለገ ብርሃኑ” የተሰኘው መጽሐፍ በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት በሚካሄደው ወርኀዊ የመጽሐፍ ግምገማ መርኀ ግብር ላይ ቀርቦ ውይይት ተደረገበት፡፡ እሑድ ኅዳር 5 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኀረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አደራሽ በተደረገው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የመጽሐፉ ጸሐፊ ተገግኝቶ ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ለውይይት መነሻ የሚሆን ሐሳብ አቀርበው የነበሩት መጋቢ በቀለ ወልደ ኪዳን ሲሆኑ፣ ስለ መጽሐፉ አቀራረብ፣ ስለ ጸሐፊው፣ ስለ ባለ ታሪኩ እንዲሁም በመጽሐፉ ቅርጽ ላይ ዳሰሳቸውን አቀርበዋል፡፡

“ፈለገ ብርሃኑ” ግለ ታሪክ የመጽሐፍ ዘውግ ሲሆን፣ የታሪኩ ባለቤት በሆኑትና በኢትዮጵያ ብርሃነ ወንጌል መጥምቃውያን ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም “ኤክሌሺያ ተነሽ” በተሰኘው የአገልግሎት ማኅበር በሚታወቁት በዶ/ር ብርሃኑ ሀብቴ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ ግለ ሰቡ ለክርስቶስ ወንጌል የነበራቸውን መሰጠትና ፍቅር የሚያሳይ ሲሆን፣ የልጅነት ታሪካቸውን፣ እንዴት ወደ ጌታ እንደ መጡና በቀደሙት ዘመናት ስለ ነበራቸው የአገልግሎት ዘመን፣ ስለ ቤተ ሰብ ሕይወታቸው፣ወዘተ. የሚያወጋ መጽሐፍ ነው፡፡

በዕለቱ በተደረገው ውይይት ላይ የባለ ታሪኩ የትዳር ጓደኛ እና ሁለት ልጆቻቸው የተገኙ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ ግለ ሰቡን የሚያውቁና የቅርብ ወዳጅ ከነበሩ መካከል የተገኙ ሰው ስለ ባለ ታሪኩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በቀጣዩ ወር፣ ታኅሣሥ 3 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. ለውይይት የሚቀርበው መጽሐፍ በኀይል ከበደ የተጻፈውና “ፌሽታ እና ጉርሻ” የተሰኘው “ትርጉምና ወጥ ቁርጥራጭ ወጎች፣ መጣጥፎች፣ አጫጭር ልብወለድና እውነታኛ ታሪኮች”ን የያዘ  መጽሐፍ መሆኑ በዕለቱ ተነግሯል፡፡

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Latest News

ስለ ቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠና ተሰጠ

“የቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት” የተሰኘ የግማሽ ቀን ሥልጠና ለተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች ተሰጠ። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በላቭ ኤንድ ኬር ማዕከል የተካሄደ ነበር። 

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.