[the_ad_group id=”107″]

“ጉርሻ እና ፌሽታ” የተሰኘው የኃይል ከበደ መጽሐፍ ለውይይት ቀረበ

December 16, 2015
ከግራ ወደ ቀኝ ደራሲው ኃይል ከበደ፣ ዳዊት ጸጋዬ አወያይ፣ አስናቀ እንድሪያስ የውይይት ጽሑፍ አቅራቢ
ከግራ ወደ ቀኝ ደራሲው ኃይል ከበደ፣ ዳዊት ጸጋዬ አወያይ፣ አስናቀ እንድሪያስ የውይይት ጽሑፍ አቅራቢ

በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት በየወሩ የሚካሄደው የመጽሐፍ ውይይት ባለፈው እሑድ ታኅሣሥ 3 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. ተካሄደ፡፡ ለውይይት የቀረበው መጽሐፍ በኃይል ከበደ የተጻፈው “ጉርሻ እና ፌሽታ” የተሰኘው መጽሐፍ ሲሆን፣ የውይይት ሐሳብ አቅራቢው ደግሞ አቶ አስናቀ እንድሪያስ ነው፡፡

ገምጋሚው አቶ አስናቀ እንዳለው መጽሐፉ የተለያዩ ሥነ ጽሑፋዊ ዘውጎችን በአንድ ላይ አካቶ የያዘ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው የገለጸ ሲሆን፣ በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱት ታሪኮች ገልጽ በሆነ ቋንቋ የቀሩቡና ወደ ሰው ልብ ለመድረስ ቅርብ መሆናቸው ጠንካራ ጎናቸው መሆኑን ጠቁሟል፡፡ በተያያዘም ቢሻሻሉ ያላቸውን ነጥቦች አስቀምጧል፡፡

የመጽሐፉ ጸሐፊ በተገኙበት በተካሄደው በዚሁ ወርኀዊ መርሓ ግብር ላይ፣ በመጽሐፉ ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ከገምጋሚውና ከታዳሚያን ለተነሡት ጥያቄዎችና አስተያየቶች አቶ ኃይል ከበደ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም ከእርምት ጥቆማዎቹ መካከል የሚቀበሏቸው እንደሚኖሩ ተናግረዋል፡፡

በመጪው ጥር 1 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. ለውይይት የሚቀርበው መጽሐፍ “Mere Christianity” በሚል ርእስ በC. S. Lewis የተጻፈውና “ክርስትና ለጠያቂ አእምሮ” ተብሎ በአዲስ አሰፋ የተተረጐመው መጽሐፍ መሆኑ በዕለቱ ተገልጿል፡፡

Hintset

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Latest News

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.