[the_ad_group id=”107″]

በደራሲ ኀይል ከበደ እና ሥራዎቹ ላይ ውይይት ተካሄደ

November 12, 2018
በደራሲ ኀይል ከበደ እና ሥራዎቹ ላይ ውይይት ተካሄደ

“ኦደሲ፦ በዲፕሬሽን ሸለቆ ውስጥ ረጅሙ ጉዞ” የተሰኘው መጽሐፍ ውይይት ሊካሄድበት ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ሲሆን፣ ኀይል ከበደ ከአንድ ሳምንት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት በማለፉ ምክንያት መደበኛውን ግምገማ ማድረግ አልተቻለም። በምትኩም፣ ደራሲውንና ሥራዎቹን የሚያወሳ ዝግጅት ተዘጋጅቶ ነበር።

የሥነ ልቦና ባለሙያው አዲስ ዓለማየሁ፣ “ኦደሲ፦ በዲፕሬሽን ሸለቆ ውስጥ ረጅሙ ጉዞ” የተሰኘውን መጽሐፍ ከሥነ ልቦና አንጻር የቃኘው ሲሆን፣ በዚህ ውስጥ ደራሲው ያለፈባቸውን ውጣ ውረዶች በመጽሐፉ ውስጥ መመልከቱን አመላክቷል። ይህም ብቻ ሳይሆን መጽሐፉ ለአንባቢያን ያለውን ጉልሕ ፋይዳ በማስገንዘብ፣ በመከራ ውስጥ የሚያልፉ ሰዎች ከኀይል ሕይወት ብዙ ቁም ነገር ሊማሩ እንደሚችሉ ጠቁሟል።

ኀይል ከበደ ከዚህ ቀደም ስለጻፋቸው መጻሕፍት ዝርዝር ገለጻ ያቀረበው መጋቢ ስሜ ታደሰ ነበር። መጋቢ ስሜ፣ ኀይልን በቅርበት እንደሚያውቀውና ሥራዎቹ የደራሲውን የዕይታ አድማስና ምጥቀት እንደሚገልጹ አስረድቷል። ይህም ብቻ ሳይሆን፣ ከአስቸጋሪ የሕይወት ጉዞው ተሞክሮ በመውሰድ ለሌሎች መኖር የቻለ ሰው ነው ሲልም አወድሷል።

ከሁለት ወረቀት አቅራቢዎች በተጨማሪ፣ የቤተ ሰቡ አባል የሆኑት አቶ ዳዊት ገብረ ጻድቅ እና እኅቱ ምሥጢረ ከበደ እንዲሁም፣ አብሮ አደግ ወዳጁ ዶ/ር ታከለ ገረሱ ስለ ኀይል ንግግር አድርገዋል። የደራሲውን ሥራ ያነበቡና በቤተ ክርስቲያን አብረው ያገለግሉ የነበሩ ሌሎች ታዳሚያንም ስለ ደራሲው ጽናትና ስለ ሥራዎቹ ፋይዳ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

Hintset

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Latest News

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.