[the_ad_group id=”107″]

ከሁለቱም ጎራ አይደለሁም፤ መሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን

March 9, 2023
Screen Shot 2023-03-09 at 3.39.29 PM

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ፣ በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ የጥር ወር የመጽሐፍ ግምገማ መርሓ ግብር ላይ ቀርቦ በነበረውና፣ “የተከዳው እውነት” በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ስሟ ያለ አግባብ መነሣቱን በመግለጽ፣ ዕርማት እንዲወሰድ ጠይቃለች። የቤተ ክርስቲያናቱ ደብዳቤ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ቀን 24/06/2015
ቁጥር መክቤክ 01/587/2015

ለሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ
አዲስ አበባ

ጕዳዩ፦ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የተነገረውን የተሳሳተ አገላለጽ እንዲታረም ስለመጠየቅ

የሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በተለያዩ ግለ ሰቦች የተጻፉና ለሕዝብ ይጠቅማሉ የተባሉ መጽሐፎችን በመገምገም ጸሐፊዎችንና አንባቢዎች በጥሩ አመለካከት እንዲታነጹ በማድረግ የተቀደሰ ስራ የሚሰራ እንደሆነ ይታወቃል። ለዚህ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ በርቱ ማለት እንፈልጋለን።

በዚሁ የመጽሐፍ ክበብ በጥር ወር ላይ፣ “የተከዳ እውነት” በሚል በቀረበውና በመጋቢ ስሜ ታደሰ የተጻፈ መጽሐፍ ግምገማ ላይ የተገኙት የመጽሐፉ ጸሐፊ “መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ካልቪናዊ ቤተክርስቲያን ነች” በማለት በምንም ዓይነት ሁኔታ የማይወክላትን የራሳቸውን እይታ የቤተክርስቲያኗ እምነትና ልምምድ አድርገው ተናግረዋል።

የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንድም ቀን እኛ ካልቪን ነን ወይም አርሚን ነን ብላ አስተምራ አታውቅም። ከሁለቱም ጎራ ባትሆንም አመጣጧ ከአናባፕቲስት ስትሆን ሰዎች ለመዳን ክርስቶስ ኢየሱስን ማመን እንዳለባቸው/እንደሚጠበቅባቸው/፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ለሁሉም ሰው እንጂ ለተወሰኑ ምርጦች ብቻ እንዳልሆነ፣ ሰው የተሰጠውን በወንጌል የማመን ዕድል ሊጠቀም ወይም ላይጠቀም እንደሚችል፣ ሰው የተዘጋጀለትን የዘላለም ክብር ለማግኘት መጽናት እንደሚገባው የእግዚአብሔርም ጸጋ ለዚህ እንደሚረዳው ታምናለች ታስተምራለች።

ስለዚህ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ካልቪናዊት ነች የሚለው የተሳሳተ ፍረጃ በቀረበበት የሕንጸት መድረክ ላይ የተሳሳተ ገለጻ እንደሆነ ታውቆ ማስተካከያ እንዲደረግ እየጠየቅን የትምህርትና ስልጠና መምሪያ በቅርበት እንዲከታተል ግልባጭ ተደርጎለታል።

ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር

ደሳለኝ አበበ ኢጆ (ፓስተር)
ፕሬዚዳንት

2 comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Latest News

ሕንጸት እና ሕይወት ቲቪ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር፣ ለዕይታ የሚያቀርባቸው የቪዲዮ ዝግጅቶቹ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት በሚቀርበውና፣ በቅርቡ መደበኛ ሥርጭቱን በጀመረው የሕይወት ቲቪ ላይ እንዲተላለፍ የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር አደረገ።

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.