[the_ad_group id=”107″]

ለችግረኛ ቤተ ሰቦች የሚሆን የአንድ ወር ቀለብ ሰፈራ ሊደረግ ነው

March 27, 2020
ለችግረኛ ቤተ ሰቦች የሚሆን የአንድ ወር ቀለብ ሰፈራ ሊደረግ ነው

የኮቪድ – 19 ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው የሥራና የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት፣ የከፋ ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላሉ ተብለው ለሚታሰቡ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች ለአንድ ወር ቀለብ የሚሆን ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያስችል ቅስቀሳ ተጀመረ።

በጥቂት ግለ ሰቦች አነሣሽነት የተጀመረውና “በጋራ ለመቆም ጊዜው አሁን ነው!” በሚል መሪ ቃል የቀለብ ሰፈራ ድጋፍ በይፋ የሚጀመረው፣ ከነገ መጋቢት 19 ቀን፥ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እንደ ሆነ ታውቋል። በዐይነት ለሚቀርቡ የምግብ ዐይነቶች መቀበያነት እንዲያገለግሉ አራት የድጋፍ መቀበያ ጣቢያዎች መለየታቸው ለሕንጸት የተለካው መረጃ ያመለክታል። 

በዚሁ መሠረት፣ ምሥራቅ መሠረተ ክርስቶስ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፣ አዲስ አበባ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን፣ X-Hub ቢሮ እንዲሁም ከቤት እስከ ከተማ ማዕከል የድጋፍ መቀበያ ጣቢያዎች በመሆኑ በቀጣዮቹ ቀናት አገልግሎት እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

ከእነዚህ በተጨማሪ መንግሥት ለዚሁ አገልግሎት እንዲውሉ በለያቸው ሁለት ተጨማሪ ጣቢያዎች ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻልም ነው ተያይዞ የተጠቀሰው። እነዚህም የሀገር ፍቅር ቲያትር እና የኤግዚቢሽን ማዕከል ናቸው ተብሏል።

ለሕንጸት የተላከው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በዐይነት እንዲቀርብ የሚጠበቀው የምግብ ዝርዝርና መጠን የሚከተለው ይሆናል፦

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Latest News

ስለ ቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠና ተሰጠ

“የቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት” የተሰኘ የግማሽ ቀን ሥልጠና ለተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች ተሰጠ። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በላቭ ኤንድ ኬር ማዕከል የተካሄደ ነበር። 

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.