[the_ad_group id=”107″]

“365 ቀናት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ በየዕለቱ” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ቀረበ

September 5, 2022
photo_2022-09-05 19.39.27

“365 ቀናት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ በየዕለቱ” የተሰኘና በዐይነቱ ልዩ የሆነ የጥሞና መጽሐፍ ለንባብ ቀረበ። በነገረ መለኮት መምህሩ እንዳሻው ነጋሽ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ፣ እሑድ ነሐሴ 29 ቀን፥ 2014 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

መጽሐፉ ለኅትመት የበቃው፣ ከመስከረም 1 ቀን፥ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ፣ እስከ አሁን በዘለቀውና የፊታችን ቅዳሜ ጷጕሜ 5 ቀን፥ 2014 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቅ በሚጠበቀው ዕለታዊ ጥሞና ላይ ይቀርቡ የነበሩና የሚቀርቡ ትምህርቶች በአንድ ላይ የተካተቱበት ነው።

ጸሐፊው እንዳሻው ነጋሽ በከፈተው የቴሌግራም ቻናል በኩል፣ ለዓመቱ ያወጣውን ዕለታዊ የንባብ መርሓ ግብር ተከትለው፣ ዐብረው ያነብቡ የነበሩ በሺሕዎች የሚቈጠሩ ሰዎች የተሳተፉበት መሆኑ በምረቃ ሥነ ሥርዐት ላይ ተጠቅሷል። መጽሐፉ፣ በየዕለቱ የሚነበቡ ሦስት ምዕራፎችን፣ የምዕራፎቹን ዕጣሬ፣ ከንባብ የተገኙ ትምህርቶችንና የጸሎት ርእሶችን የያዘ ነው። ስድስት መቶ ሰማኒያ አራት ገጾች ያሉት ይህ መጽሐፍ፣ አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን ወጥ በሆነ መልኩ እንዲያነብቡ ከማስቻሉም በላይ፣ ያነበቡትን እንዲያሰላስሉና በሕይወታቸው ተግባራዊ እንዲያደርጉት የሚያግዝ መሆኑ ተነግሮለታል። መጽሐፉ፣ በዐምስት መቶ ብር ለሽያጭ ቀርቧል።

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Latest News

ስለ ቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠና ተሰጠ

“የቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት” የተሰኘ የግማሽ ቀን ሥልጠና ለተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች ተሰጠ። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በላቭ ኤንድ ኬር ማዕከል የተካሄደ ነበር። 

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.